ETHIO12.COM

ወደ ትግራይ ክልል ሊያስገባ የነበረው አደገኛ ዕፅ ተያዘ

አሸባሪው ህወሓት ቡድን ዕፁን ሊያስተላልፍ የነበረው እንደለመደው የትግራይ ወጣቶችን በዕፅ አደንዝዞ ወደ ጦርነት ለመማገድ እንደነበረ በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎቹ ተናግረዋል።

አሸባሪው የሕወሃት ቡድን ከአዲስ አበባ እስከ ሚሌ ኔትወርክ በመዘርጋት በአፋር ክልል በኩል ወደ ትግራይ ክልል ሊያስገባው የነበረ በርካታ ኩንታል አደገኛ ዕፅ በህብረተሰቡ ጥቆማ እና በፖሊስ ብርቱ ክትትል ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም መያዙን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

በሕወሃት የሽብር ቡድን አባልነት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በሚጠየቁበት ጊዜ አደገኛ ዕፁን የእርዳታ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም ወደ ትግራይ ክልል ለማስገባት እንደሆነ ተናግረው ዕፁን ለመቀበል የተዘጋጀ ቡድን እንዳለም ጠቁመዋል።

ሁለት ተጠርጣሪዎች በሰሌዳ ቁጥር አ.አ ኮድ 3-A40101AA ቶዮታ ዶልፊን ተሽከርካሪ ላይ አደገኛ ዕፁን ጭነው ሲያጓጉዙ በህብረተሰቡ በተሰጠው ጥቆማ መሰረት ከሌሎች የፀጥታና ደህንነት አካላት ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅሷል።

ከአደገኛ ዕፁ በተጨማሪ ለእኩይ ዓላማ ማስፈፀሚያ ሊውል የነበረ 2 ሚሊዮን 370 ሺህ ብር መያዙንም ገልጿል።

በሕወሃት የሽብር ቡድን አባልነት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በሚጠየቁበት ጊዜ አደገኛ ዕፁን የእርዳታ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም ወደ ትግራይ ክልል ለማስገባት እንደሆነ ተናግረው ዕፁን ለመቀበል የተዘጋጀ ቡድን እንዳለም ጠቁመዋል።

ፖሊስም ይህንን ቡድን በቁጥጥር ስር ለማዋል በክትትል ላይ መሆኑን አስታውቋል።

ይህ የሽብር ቡድን ዕፁን ሊያስተላልፍ የነበረው እንደለመደው የትግራይ ወጣቶችን በዕፅ አደንዝዞ ወደ ጦርነት ለመማገድ እንደነበረ በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎቹ ተናግረዋል።

ይህ አደገኛ ዕፅ የተያዘው በህዝቡ ጥቆማና ቀና ትብብር በመሆኑ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ላቅ ያለ ምስጋናውን እያቀረበ በየትኛውም ደረጃ የሚወጠኑ መሰል የወንጀል ተግባራትን ለመቆጣጠር ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር ተገቢውን ቅንጅት በማድረግ የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

(ኢዜአ)

Exit mobile version