Site icon ETHIO12.COM

“ቴዎድሮስ አድሃኖምና የትህነግ አሸባሪ ሃይሎች ማዕቀብ ሊጣልባቸውና በኢንተርፖል ተያዘው ህግ ፊት መቅረብ አለባቸው”

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖምን ጨምሮ የአሸባሪው ህወሃት አመራሮች ማዕቀብ እንዲጣልባቸውና በኢንተርፖል ተይዘው ለህግ ሊቀርቡ እንደሚገባ ዴንማርካዊው ጋዜጠኛ ራስመስ ሶምዴርሊስ ተናገረ።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ ስልጣናቸውን በሰብዓዊነት ሽፋን አሸባሪው ህወሃትን ለመደገፍ እየተጠቀሙበት መሆኑን ዓለም ሊገነዘብ እንደሚገባ ገልጿል።

መንግሥት ባሳለፍነው ጥር ወር ለዓለም ጤና ድርጅት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በጻፈው የቅሬታ ደብዳቤ ዋና ዳይሬክተሩ የተባበሩት መንግሥታትን የታማኝነትና ገለልተኝነት መርሆ በሚጥሱ ተግባራት ላይ መሰማራታቸውን ጠቅሶ ነበር።

ዶክተር ቴድሮስ ስልጣናቸውን ባልተገባና የድርጅቱን መርሆ በሚጻረር መልኩ በመጠቀም ለአሸባሪው ህወሃት ቴክኒካዊና የገንዘብ ድጋፍ ከማድረጋቸው ባለፈ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ እየሰሩ መሆኑን በቅሬታው መግለጹም አይዘነጋም።

ዋና ዳይሬክተሩ መንግሥት ለትግራይ ክልል ያልተገደበ ሰብዓዊ ርዳታ እንዲደርስ እያደረገ ያለውን ጥረት በመካድ የትግራይ ክልል ህዝብ ርዳታ እንዳያገኝ ተደርጓል ሲሉም ሀሰተኛ ክስ ሲያራግቡ ነበር።

ህወሃት ለሦስተኛ ጊዜ በአማራና በአፋር ክልል የጀመረውን ወረራ እንዳላየ ያለፉትና በሁለቱ ክልሎች የደረሰውን ግፍ ከምንም ሳይቆጥሩ አካባቢነታቸውን በይፋ በመግለፅ ለሽብር ቡድኑ ይፋዊ ድጋፋቸውን እያሳዩ ስለመሆኑ የተለያዩ ተንታኞች በመግለፅ ላይ ናቸው።

ዴንማርካዊው ጋዜጠኛ ራስመስ ሶምዴርሊስ ከኢዜአ ጋር ባደረገው ቆይታ፤ የዓለም ምግብ ፕሮግራም መንግሥት ለትግራይ ክልል ህዝብ የሚደርሰው ርዳታ እንዲሳለጥ ተገቢ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን እየገለጸ ዶክተር ቴድሮስ ከዚህ ሀቅ መውጣታቸውን ታዝቦ ተችቷል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ደይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም፤ ስልጣናቸውን በሰብዓዊነት ሽፋን መንግሥትን በሀሰት ለመወንጀልና የሽብር ቡድኑን ለመደገፍ እየተጠቀሙበት ነው ይላል ጋዜጠኛ ራስመስ።

“ዶክተር ቴድሮስ ስለትግራይ የሰብዓዊ ድጋፎች ሲያወሩ በተደጋጋሚ ይደመጣሉ፤ ሆኖም በአማራና አፋር ክልሎች በሽብር ቡድኑ በተፈጸሙ ግፎች ስለተጎዱ ሰዎች ግን አንድም ቃል ተንፍሰው አያውቁም” ሲል ግልጽ የሆነ አድሏዊነታቸውን ተችቷል።

“ዶክተር ቴድሮስ በጣም መሰሪና ክፉ ሰው ናቸው” ያለው ጋዜጠኛው፤ የፖለቲካ ዳራቸው በአምባገነንነትና ነውረኝነት የሚታወቅ በመሆኑ፤ አንድም ቀን ስለፖለቲካ አውርተው አያውቁም ይልቁንም ገመናቸውን ለመሸፈንና መልካም ሰው ለመምሰል አደናጋሪ ጥረቶችን ሲያደርጉ ይታያሉ ነው ያለው።

ሆኖም የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ አመራር መሆናቸውንና ህጻናትን ወደ ጦርነት እየማገደ ያለው የህወሃት የሽብር ቡድን አባል መሆናቸው ሊዘነጋ እንደማይገባ ጠቅሷል።

በመሆኑም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በዶክተር ቴድሮስ አድሃኖምና ሌሎችም የሽብር ቡድኑ አመራሮች ላይ ማዕቀብን ጨምሮ በኢንተር ፖል ተይዘው በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ መስራት አለበት ብሏል።

መንግሥት ችግሮች በሰላም እንዲፈቱ እያደረጋቸው ያሉ ተደጋጋሚ ጥረቶች የሚደነቁ ስለመሆናቸው በማንሳትም የመንግስትን ቁርጠኝነትና ትዕግስት ዓለም ሊገነዘበው እንደሚገባ ቃለ ምልልስ አድራጊውን ጠቅሶ የዘገበው ኢዜአ

Exit mobile version