Site icon ETHIO12.COM

“ዲዳው ዘመቻ” አሜሪካ የማዕቀብ ህጓን አጸደቀች

የዛሬ ዓመት ገደማ የቡድን ሰባት አባል ሃገራትና ሌሎች ለጋሽ ሃገራት በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ዙሪያ ውይይት አድርገው ነበር። የአሜሪካ ተራዶ ድርጅት ዩኤስአይዲ እንደመራው በተነገረለት ስብሰባ ጦርነት ቆሞ ድርድር እንዲደረገ ለማስገደድ የሚቻልበትን ተቀምሮ ነበርል። ይህ የሆነው ደግሞ ደብረሲናን አልፎ ወደ ደብረብርሃን አምርቷል የተባለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ሰራዊት በቀናት ውስጥ መሸነፉ ይፋ ከሆነ በሁዋላ ነው።

አሜሪካንን በመኮነን ወደ ስልታዊ ማፈግፈግ በማድረግ ወደ ትግራይ ማቅናታቸውን የትህነግ ሃይል አመራሮች በወቅቱ ገልጸው አለመሸነፋቸውን ማስታወቃቸው አይዘነጋም። ሙሉ ሃያላቸውም እንዳለ ሳይነካ አስፈላጊ ሲሆን ማጥቃት መሰንዘር እንደሚችል ገልጸው ነበር። ይህ በተገለጸ ሳምንታት ውስጥ የባይቶና ፓርቲ አመራርና የራሱ የትህነግ የወጣቶች ክንፍ ከመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶች ከጦርነቱ ማግስት የት እንደገቡ እንደማይታወቅ መረጃቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

ቁርጥ ያለ ዳታ ማስቀመጥ ባይቻልም የትህነግ ሃይሎች አማራና አፋርን ከወረሩ በሁዋላ በመልሶ ማጥቃት ዘመቻው ክፉኛ መጎዳታቸውን ከትህነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በቀር የሚክድ አካል የለም። በመከላከያና የአማራ እንዲሁም የአፋር ልዩ ሃይል በኩልም እንደ ትህነግ ባይሆንም ዋጋ መከፈሉም ይታወቃል።

ጋብ ብሎ የነበረው ጦርነት ዳግም ካገረሸ በሁዋላ እንደሚሰማው የትህነግ ሃይሎች እጅግ ከፍተኛ የተባለ ሰብአዊ ኪሳራ እንደደረሰባቸው በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚወጡ መረጃዎች እየመሰከሩ ነው። መንግስት ” ዲዳ” በሆነበትና ” መከትኩ” በሚለው በዚህ ጦርነት ትህንገ የሰው ማዕበል ማጉረፉን አቶ ጌታቸው ረዳ ጨምሮ አምነዋል። ” ይህ ማዕበል ወደፊት መግፋት ካልቻለ የት ገባ?” ሲሉ የሚጠይቁ “ዲዳው ጦርነት” ወደፊት ይፋ የሚሆኑ በርካታ ጉዶች እንዳሉት አመለካች እንደሆነ ይገልጻሉ።

ምን ዓይነት ድልና ውጤት እንዳገኘ ይፋ የማይናገረው መከላከያ የሚመራው ጥምር ሃይል በማይጸብሪ ግንባር ትህነግ ለአንድ ዓመት ይዟቸው የነበሩ ቦታዎችን አስለቅቆ ሽራሮን መዳረሱን የትህነግ ሃላፊዎች በይፋም ባይሆን እየገለጹ ነው። አዲግራትም መከበቧ እየተመለከተ ነው። በዳሎል አፋር በኩል በኤርትራ ዞሮ የገባው ሃይል ከመቀለ 50 ኪሎሜትር ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው።

ዲዳው ዘመቻ

አሁን አየተካሄደ ያለውን ጦርነት “ዲዳው ዘመቻ” ሲሉ የሰየሙ መኖራቸው ተሰምቷል። አነዚህ ሃይሎች በፌስቡክ ጫጫታና በግልብ እሳቤ የሚነሆልሉ አይመስሉም። “ዲዳ” ያሉት መንግስትን ነው። ምክንያታቸው ደግሞ የድል ዜና አያሰማም። “ተከበብኩ፣ ተወረርኩ፣ ተደበደብኩ ” በማለት የገጠሙትን ከሰማይና ከምድር እያመነዠገ ነው።

ከአክቲቪስቶና ከማህበራዊ መገናኛዎች ውጪ የመንግስት ሚዲያዎችም ሆኑ ኦፊሳሎች ምን እየሆነ እንደሆነ በይፋ መረጃ የማይሰጡበት ይህ ጦርነት ውጤቱ እየተገመገመ ያለው የትህነግ ሰዎች በሚሰጡት መግለጫ ብቻ ነው። “እናደባያለን፣ ከትግራይ ሃይሎች እርምጃ የሚተርፍ ሃይል የለም” በሚል የትህነግ ማሳሰቢያ የተጀመረው ጦርነት ” አማራ ፍቅር ነው፣ አሜሪካ ታግዘን፣ ዓለም ይደርስልን” ወደሚል ተማጽኖ መቀየሩ መሬት ላይ ያለውን ሃቅ አመላካች ሆኗል።

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ “በሰሜን ኢትዮጵያ ቀውስ ላይ ለመወያየት” ለሶስተኛ ጊዜ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡም ያደረጋቸው ይህ እውነት ነው። ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት በትግራይ ሰለፊያ ፎቶ ሲነሱ የነበሩት ማይክ ሐመርና ሌሎች ዲፕሎማቶች ስንቅ፣ ትጥቅ፣ መድሃኒት፣ ነዳጅና ሎጂስቲክ መሟላቱን ካረጋገጡ በሁዋላ ትህነግ ቆቦን ሲወር አልተነፈሱም ነበር። ትህነግ ወደ ወልደያ ሲነደረደር “ተው” ያለ አልነበረም። ዲዳው ጦርነት ቀጥሏል።

አሜሪካ ገጀራዋን ማንሳቷና የትህነግ ለቅሶ

በአምስት ግንባር ጥቃት እንደተከፈተበት ይፋ ያደረገው መንግስት መጠቃቱንና ጥቃቱን በበቂ ሁኔታ መመከቱን ከሚገልጸው ውጭ ዝርዝር አይናገርም። ትህነግም በአምስ አቅጣጫ ጥቃት ተሰነዘረብኝ ጥቃቱን ” የትግራይ ሃይሎች እየመከቱት ነው” ከማለት በዘለለ የጦርነቱን ውጤት አንድ ሁለት ብሎ እንደወትሮው አይገልጽም። ተከታዮቹና ሚዲያዎቹም በተመሳሳይ እንደወትሮው በማህበራዊ ገጾቻቸው የድል ብስራት ማሰማት ካቆሙ ከራርመዋል። ቆቦን መያዝቸውን ካስታወቁበት የደስታ ዜና በዘለለ አዲስ የድል ዜና ማግኘት አልቻሉም። ይልቁኑም “አማራ ወይም ሞት” የሚለው አዲሱ የትህነግ አቋም ግራ አግብቷቸዋል።

“አማራ ታሪካዊ ጠላትህ ነው፤ አጥፋው” እየተባለ በገሃድ ሲማር የኖረ ትውልድ በቅጽበት የትህነግ “ከአማራ ጋር በፍቅር ልሙት” ቅስቀሳ በርካቶችን ቢያስገርምም ለሚገባቸው ትህነግ አደገኛ ቁልቁለት ውስጥ መቀርቀሩን የሚያመላክት ስለመሆኑ በስፋት እየተተቸ ነው። “የትግራይ ሕዝብና የአማራ ህዝብ ድሮም ዛሬም አንድ ነው። ነገር ግን ትህነግ የእድሜ ልክ የአማራ ጠላት ነው። ትህነግ አማራን አስፈርጆ በሄደበትና በሚኖርበት ሁሉ እንዲታረድ ያደረገ፣ ለም ማህጽኖችን ያመከነ፣ በወልቃይትና ጠገዴ በሺ የሚቆጠሩ የአማራ ልጆችን የጨፈጨፈና ብጄኖሳይድ የሚጠየቅ ወንጀለኛ ድርጅት በመሆኑ ለሁለቱ ህዝብ አስታራቂ ሊሆን አይችልም። ይህ በአማራ አጽምና ደም መሳለቅ ነው” ሲሉ ጽፈዋል።

“በቅርቡ አማራ ክልል ላይ የሰራዊት ማዕበል ለቆ ወረራ ባካሄደበት ወቅት መዝረፍና ማጋዝ ያቃተውን በማውደም፣ ክልሉን አመድ አድርጎ፣ በጅምላ ገሎ፣ ከመነኩሴ እስከ ህጻን ደፍሮ፣ የአርሶ አደር ማሳ አውድሞ፣ እንሳሳትን አርዶና በጥይት ረሽኖ፣ የጓሮ ዛፋቸውን ሰባብሮ… ማዕድ ላይ መጸዳዳቱ አይረሳም” በማለት የትህነግን የአማራ ፍቅር ጥያቄ የኮነኑ “የተማረኩት የትህነግ ሃይሎች ያገኛችሁትን ዝረፉ አጥፉ ተብለን ነው የተላክነው” ማለታቸውን ለትህነግ ክፋት በአብነት አመላክተዋል። እናም “እስኪቀበር አይታመንም” ብለዋል።

ለዚህም ይመስላል በወልቃይት ግንባር ሕዝብ ነቅሎ ወረራውን ለመመከት ከጥምር ሃይሉ ጋር ጦር ሜዳ ከቷል። ይህ መሬት አንቀጥቅጥ የህዝብ ድጋፍ አፍታም ሳይቆይ በትህነግ ስር የነበሩ አካባቢዎችን የጥምር ሃይሉ እንዲቆጣጠር እንዳስቻለ ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎችና የቪዲዮ ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ። የስንቅ አይነት ሰንጋ፣ ሙክት፣ አነባበሮና ፍትፍት የሚቀርብለት የኢትዮጵያ ጥምር ሃይል በደጀኑ እየተመካ በየአቅጣጫው ወደፊት እየገሰገሰ መሆኑ ይፋ ሲሆን አሜሪካ ድምጿን ከፍ አድርጋ ጮሃለች። በሰቆጣና በወልደያ የሆነው ተመሳሳይ ነው። ከስንቅና ደጀኑ ድጋፍ ጋር ፋኖ፣ ልዩ ሃይልና መከላከያ የትህነግን ሃይል ቆራርጠው እየመከቱት ነው። የትህነግ አዋጊዎች “ነገሮች ተበላሽተዋል” የሚል መረጃ እስከመመላለስ መድረሳቸው ከተጠለፈ የአዋጊዎች ድምጽ ተሰምቷል። የዚህ ሁሉ ውጤት በመጨረሻ አሜሪካ መደርደሪያ ላይ አስቀምጣው የነበረውን በጦርነት ላይ የሚሳተፉ አካላት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የሚያዘውን ህግ ባይደን እንዲፈርሙበት ተደርጓል።

ይህ አሜሪካ ከአንድ ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ጉዳይ አውጥታው የነበረው ህግ የትህነግን የደሱልኝ ጥያቄ ተከትሎ መጽደቁ ጨዋታ በመናበብ የሚሰራ መሆኑንን የሚያመላክት እንደሆነ የሚያረጋግጥ ሆኗል። ሲኤን ኤን ከጀመረው ዘመቻ ጋር ተጋምዶ በጦርነት ያቃተውን ትህነግን ለማዳን እየተነደፈ ያለው ስልት ኢትዮጵያን በመጫን ጦርነቱን አቁማ ለትህነግ እንደቀድሞ ነዳጅ፣ ዕህል፣ መኪና፣ ብር፣ መድሃኒት በጥቅሉ ሎጂስቲክ እንድታሟላ የሚያስገድድ ነው።

አሜሪካ ይህን ህግ ከአንድ ዓመት በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት እንዲቆም የሚጠይቅ ህግ በሚል ያዘጋጀቸው እንደነበር ይታወሳል። በወቅቱ መንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም በማወጅ ሃሳቡን ቀልብሶ ነበር።

ይህ በርካቶችን ለተቅውሞ አስነስቶ የነበረ ህግ ከወጣበት ከፈረንጆቹ ቀን አቆጣጠር ከመስከረም 17 ጀምሮ ወደ ስራ እንዲገባ ባይደን ማዘዛቸውን ዋይት ሃውስ ይፋ አድርጓል። ህጉ ሲወጣ አሜሪካ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የኢትዮጵያን ፣ምስራቅ አፍሪካንና የአሜሪካንን ብሄራዊ ጥቅም ይጎዳል በሚል እንደሆነ ለሽፋን ገልጻ ነበር። በውጤቱም ጦርነቱ  እንዲቀጥል በሚያደርጉ፣ ለዜጎች እርዳታ እንዳይደርስ በሚያስተጓጉሉና ከዚሁ ጋር በተያያዘ ወደ ኢትዮጵያ በገቡ የውጭ ሀገራት አካላት ላይ ማዕቀብ እንደምትጥል አሜሪካ ያስጠነቀቀችው። መንግስት ምን ምላሽ እንደሰጠ እስካሁን አልተሰማም።

በፈረሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ከፍራንስ 24 ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ቆቦ በኢትዮጵያ ሃይሎች ቁጥጥር ስር ነበረች። አስተዳደሩም ስራውን እየሰራ ነበር። ኢትዮጵያ ጦርነቱን ብትጀምር እንዴት ትህነግ ቆቦን ይወር ነበር” ሲሉ ጦርነቱን ትህነግ ስለመጀመሩ በአምከንዮ ተናግረዋል። በተመሳሳይ በኬኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ” ማጥቃት ብንፈልግ እንኳ በቆቦ አይታሰብም።” ሲሉ በወታደራዊ ሳይንስ አመክኖዮ በቆቦ በኩል የኢትዮጵያ ሰራዊት ለማጥቃት እንደማያስብ አመልክተዋል። ትህነግ በበኩሉ ጦርነቱን የመንግስት ሃይሎች እንደጀመሩ አመልክቷል።

የትህነግ ጥሪ

የትህነግ ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጽዮን የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት “በኃይል ጣልቃ ገብቶ” ጦርነቱን እንዲያስቆም የተማጽኖ ደብዳቤ ጽፈዋል።

ደብረጺዮን ለወቅቱ የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንትና ለመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ በጻፉት ደብዳቤ፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ ሃይሎች መጠነ ሰፊ ጥቃት መሰንዘራቸው ገልጸዋል። (የወሩ የጸጥታው ምክር ቤት ሰብሳቢ ቻይና መሆኗ ይታወሳል)

ደብረጺዮን በደብዳቤያቸው የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በኃይል ጣልቃ ገብቶ የኤርትራ ሠራዊትን ከኢትዮጵያ ካላስወጣ፣ ግጭት ካላስቆመ፣ በክልሉ መሠረታዊ አገልግሎቶችን፣ ያልተገደበ ሰብዓዊ እርዳታ ካለስጀመረ “የትግራይ ሕዝብ በእነዚህ ሁለት ጨካኝ ሠራዊቶች ይጠፋል” ብለዋል።

ይህ ደብዳቤ ከመሳፉ በፊት ባለፈው ሰኞ ኢትዮጵያ የገቡት የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሃመር፣ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንደዚሁም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጋር ጦርነቱ በአስቸኳይ መቆም እንዳለበት እና በአፍሪካ ህብረት መሪነት ወደ ሰላም ድርድር ማምራት እንደሚያስፈልግ መወያያታቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል። የዩናይትድ ስቴትሱ ልዩ ልዑክ ለህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤልም ተመሳሳይ መልዕክት ማስተላለፋቸውን አመልክቷል። ምላሹን ግን አላስታወቁም።

Exit mobile version