የዛላ አምበሳ ድምበር ሲከፈት፣ የታፈኑ ነጻ የወጡ ዘንድ አትሩ ሲነሳ የተወሰደ ምስል ነው። ይህ በጎ ጅማሬ ሳይቆይ ዳግም በሩ ተዘጋ። በርካታ ፎርጂድ ናቅፋ ኤርትራን ሞላት፣ ሌሎችም መተማመንን የሚሸረሽሩ ጉዳዮች ተፈጠሩና ተስፋው ጠወለገ።

በሺራሮ የሚገኙ የሰብአዊ ድርጅቶች መረጃን ያሰባሰበውንና ሮይተርስ” አየሁት” ያለው የተባበሩት መንግስታት ቡሌቶች የኤርትራ ሃይሎች 23 ዙሮች የተኩስ ጥቃት መፈጸማቸውን ያትታል። ጥቃቱም ጥቂት የተፈናቀሉ ቤተሰቦች የሚኖሩበትን ትምህርት ቤት እንደመታ ይገልጻል። ይህን ጥቃት ሪፖርት ካደረጉት ሰነዶች መካከል አንዱ የ14 ዓመቷ ልጅ መገደሏን፣ በትንሹ 18 ሰዎች መቁሰላቸውንና 12 ቤቶች መጎዳታቸውን አመልክቷል። ይህን ጥቃት ተከትሎ የትህነግ ሃይሎች ባደረጉት መልሶ ማጥቃት ከ300 በላይ የኤርትራ ሰራዊት አባላትና አዛዦች መገደላቸውን መሳሪያም መማረኩን ሮይተርስ አቶ ጌታቸውን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። እንደ ሮይተርስ ከሆነ የትህነግ ሃይል ሲነካ አጻፋ መልሷል። ለዚህም ምስክሮቹ የዕርዳታ ድርጅቶች ናቸው።

አሜርካ የምስራቅ አፍሪቃ ልዩ መልዕክተኛ አድርጋቸው የነበሩት ፌልትስማን ” ትህነግ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ አይወደድም” ሲሉ በመጨረሻው ቃለ ምልልሳቸው ማረጋገጣቸውና እያፈገፈገ ሃይሉን አደራጅቶ ወረራውን በአጭር ቀናት ተቀልብሶ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ሃይሎች ጦርነቱን በሽንፈት ማጠናቀቃቸው ይታወስል።

“አውቀን ነው ከያዝነው ቦታ የለቀቅነው” በማለት ያስታወቀው የነጻ አውጪው ሃይል ” አሜሪካ ነበር አዲስ አበባ ግቡ ያለችን” ሲል ለሽንፈቱ ምክንያት አቅርቧል። አሜሪካም በውጭ ጉዳይዋ በኩል ” ፈጽሞ አላልኩም” ስትል የላሞኛችሁ ምላሽ ብትሰጥም፣ አቶ ጌታቸው የሴራውን ጥቅልል ውጤት ይፋ ማድረጋቸው ከፌልትስ ማን የመጨረሻ ቃል ጋር በመስማማቱ አቶ ጌታቸው ምን አልባትም በዓመቱ አንድ ትልቅ እውነት መናገራችወና ይኸው ንግግራቸው “በምስክርነት ሰነድ ሊቀመጥላቸው ይገባል” ያሉም ነበሩ።

“ከነ ሙሉ ሃይሌ ወደ ትግራይ ተመልሻለሁ” ያለው ትህነግ አፍታም ሳይቆይ በወጣት ክንፉ አማካይነት ” ከ300 መቶ ሺህ በላይ ወታቶች የት እንደገቡ አይታወቅም” ሲል ማስታወቁ ከትህነግ በኩል የደረሰውን የጉዳት መተን የሚያመላክት፣ በኢትዮጵያም በኩል ሰፊ መስዋዕት መከፈሉ እንደ አገር አሳፋሪ፣ ጥቁር የታሪክ ጠባሳ ሆኗል። ይሁን እንጂ መነሻው ሁሉ በሰሜኑ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸመ የክህደት ጭፍጨፋ በመሆኑ ሙሉ ተጠያቂነቱ የክህደት ቢላውን ባነሳው ወገን ላይ እንደሆነ አብዛኞች ይስማማሉ።

አቶ ኦባንግ ከሚመሩት ለሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ እንደሆነ የሚነገርለት የአዲስቲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ solidarity movement for a new ethiopia (SMNE) ይህ ጽሁፍ እስከታተመበት ቀን ድረስ በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የተፈጸመውን የክህደት ግፍ በዝምታ ያለፈና፣ ዝም ለማለቱ በቂ ምክንያት ያላቀረበ፣ በወጉም በሚዲያ ያላስታውቀና ያልተጠየቀ መሆኑንን በመገረም የሚያወሱ፣ የትህነግ ሃይሎች በመከላከያ ላይ የፈጸሙትን የክህደት ወንጀል ከኢትዮጵያ በተቃራኒ የቆሙና ውገናቸውን በገሃድ ያሳዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ሚዲያዎች ሳይቀሩ ያመኑት ጉዳይ ነው። በዚህም መነሻ ለጦርነቱ መነሳት ትህነግ ምክንያት ስለመሆኑ መከራከሪያ አይቀርብም።

በዚህ የጭንቅ ቀን ነው ኤርትራ ከክህደት እርምጃው ተርፎና በሃይሉ ከበባውን ሰብሮ ወደ ኤርትራ ምድር የዘለቀውን የኢትዮጵያ መከላከያ በማልበስ፣ በማብላት፣ በማጠጣትና ከለላ በመሆን ታላቅ ውለታ የፈጸመችው። የኤርትራ የውቅቱ በጎ ተግባርና ምላሽ ” ከኤርትራ ጋር ወዳጅ ባንሆን ኖሮ ምን ይውጠን ነበር” በሚል በገሃድ መንግስትና ሕዝብ የአክብሮት ምላሽ ሰጥተዋል።

ከዳግም ወረራው መቀልበስ በሁዋላ አፋርን ድጋሚ ይዞ የነበረው ትህነግ የኢትዮጵያን መንግስት የተናተል የተኩስ አቁም እርምጃ ባለማክበር ቢከሰስም ” እርዳታ በደንብ ከገባልኝ ለቅቄ እወጣለሁ” ሲል ቆይቶ አፋርን ለቆ መውታቱን አስታውቋል። አሁንም ግን አንዳንድ ቦታዎች ላይ እንዳለ ይነገራል።

በከፈተኛ መጠን በአየርን በየብስ እርድታ እየገባለት ያለው የትግራይ ክልል ላለፉት ሶስት ሳምንታት ፊቱን ወደ ኤርትራ አዙሯል። ኤርትራ በገሃድ የሩሲያ ደጋፊ መሆኗን፣ የቀይ ባህርንም ለሩሲያ የጦር ኮሪዶርነት መፍቀዷ ያላስደሰታት አሜሪካ ከቀድሞ ጀምሮ በፕሬዚዳንት ኢሳያስ ላይ ካላት ጥላቻ ጋር ተዳምሮ ትህነግ ልዩ የቤት ስራ እንደተሰጠው፣ ለዚህም የሎጂስቲክ ችግር እንዳይገጥመው እርዳታ እንዲጎርፍለት መደረጉን አንዳን ወገኖች እየተናገሩ ባለበት ወቅት ነው የጦርነቱ ወሬ ገሃድ የሆነው።

የትህነግ ልሳን የሆኑት አቶ ጌታቸው ይፋ እንዳደረጉት በትህነግ ሃይሎችና በኤርትራ መካከል ጦርነት ተካሂዷል። ጦርነቱ መካሄዱን ኢትዮጵያም እንደምታውቅ አረጋግጣለች። ኤርትራ ግን ለጊዜው ያለችው ነገር የለም። አቶ ጌታቸው በትዊተር ገጻቸው የጦርነቱን መካሄድ ሳይሆን ያጎሉት ጉዳይ “የኤርትራ ኃይሎች ቀጠናውን ወደማያባራ ግጭት እየወሰዱት ነው” የሚለውና ትህነግን ከተዘነጋበት የምስራቅ አፍሪቃ አጀንዳ የመክተት ነው። ይህን ሲያተነክሩ “ይህም ወደ ሰላም ሊደረግ የሚችል ጉዞን የሚያሰናክል ነው” በማለት የቀጠናው የሰላም ጠንቅ የኤርትራ መንግስት እንደሆነ ገልጸዋል።

ወረራው ከተቀለበሰ በሁዋላ ” ከማን ጋር ነው የምንደራደረው? ጦርነቱ በሳምንታት ያልቃል” ባሉበት ሚዲያ ሌተና ጀኤነራል ጻድቃን ” የኤርትራን መንግስት እንዲነቀል ድጋፍ ሊደረግ የገባል” ሲሉ ካሰራጩትና ዶክተር ደብረጽዮን ” አግዙን፣ ኤርትራ ውስጥ ያለው መንግስት መወገድ አለበት” ሲሉ ጥሪ ባቀረቡበት ወቅት ዋና ምክንያት የሆነው ” ሻዕቢያ የአፍሪቃ ቀንድ ስጋት ነው” የሚለው ጉዳይ ነው።

“የትግራይ መከላከያ ሃይል” ተብሎ የተሰየመውን ሰራዊት በማግዘፍና በቀጣናው የአሜሪካናን የአውሮፓን ጥቅም የሚያስከበር ልዩ አቅም እንዳለው ተደርጎ በተለያዩ ወገኖች ሲቀርብ የነበረውን ቅስቀሳ ” አስተማማኝ ሃይል ስትገነባ ትከበራለህ” በሚል የፖለቲካ ሚዛን ደጋግመው የሚናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ የተገነባው ከደርግ ውድቀት በሁዋላ በምሁራን፣ በዲሲፒሊን፣ በኢትዮጵያዊነትና እጅግ በዘመነ መሳሪያ የደረጀ መሆኑ እየተመሰከረ ነው። ለዚህም ይመስላል ትህነግ እጀምረዋለሁ የሚለውን ጦርነት ያልገፋበት የሚል ጉዳይም እየተነሳ ነው።

በኤርትራ በኩል ጦርነቱ ከተጀመረ እስከ ቀብር ድረስ እንደሚሄድ ኢሳያስ ማስተንቀቃቸውን ኤርትራ ፕሬስ አመልክቷል። የኤርትራ ፕሬስ ከሶስት ሳምንት በፊት እንዳለው ኤርትራን ለማጥቃት ከታሰበ የትህነግን ሃይል የመደምሰስ አቅም ኤርትራ በተጠንቀቅ ማቆሟን አመልክቷል። ይህ በተባለ አጭር ጊዜ የትህነግ ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ቅዳሜና ዕሁድ የኤርትራ ሠራዊት በሽራሮ በኩል ጥቃት ከፍቶ እንደነበር አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ተንኳሹ የትህነግ ሃይል እንደሆነና በውጤቱም ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት አታውቋል። ኤርትራ ዝምታን መርጣለች።የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ንለገሰ ቱሉን ጠቅሶ ለአል ዐይን አማርኛ እንደጻፈው ትህነግ የኤርትራ ጦር ጥቃት ከፈተ በሚል የሚያሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው። አቶ ጌታቸው ግን ከቅዳሜና እሁድ ተከስቷል ካሉት ግጭት በተጨማሪ ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ. ም የኤርትራ 57ኛ እና 21ኛ ክፍለ ጦሮች ወደ ትግራይ ክልል በመዝለቅ ጥቃት መሰንዘሩን አስታውቀዋል።

አዲአዋላ አካባቢ በነበረ ውጊያ የህወሃት ታጣቂዎች ጥቃቱን እንደመከቱ ፣ የትህነግ ኃይሎች መልሶ ማጥቃት መፈጸማቸውንና የኤርትራ ወታደሮች  መገደላቸውና መቁሰላቸውን እንዲሁም “በርካታ” ያሏቸው የጦር መሣሪያዎችን መማረክ እንደቻሉ ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ይህ በነጻና ገለልተኛ ሃይል አልተረጋገጠም።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ለቢቢሲ በሰጡት ምላሽ በአሁኑ ጊዜ “በኤርትራ በኩል ጦርነት ይከፈታል የሚል እምነት የለንም” ብለዋል። ጨምረውም የህወሓት ኃይሎች ለጦርነት እየተዘጋጁ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለአል-ዐይን ሲናገሩ ግን ትንኮሳ ያደረገው ህወሃት እንደሆነና የተመቱትም ራሳቸው የህወሃት ታጣቂዎች መሆናቸውን ነው ያስታወቁት። ሚኒስትሩ በኤርትራና በህወሃት መካከል ግጭት እንዲፈጠር ያደረገው ህወሃት መሆኑን ገልጸው በዚህ ሁኔታ ህወሃቶች “ሬሳ እንኳን ማንሳት አልቻሉም፤ በጣም ብዙ ሰው ወድሞባቸዋል” ብለዋል።

ሚያዚያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የትግራይ ኃይሎች ከኤርትራ ጋር አዋሳኝ በሆኑት የራማና ባድመ አካባቢዎች ጦርነት አካሂደው እንደነበር ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ ክፍሎችን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። ጥቃቱ በራማና ባድመ አካባቢ ባለው የኤርትራ ጦር ላይ የተሰነዘረ ሲሆን፣ አስቀድሞ መረጃ የደረሳቸው የኤርትራ ሃይሎች ሆን ብለው በማፈግፈግ ቀለበት ውስጥ ከተው በትህነግ ሃይሎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸው በወቅቱ ተዘግቧል። የትህነግ ወገኖች ግን ጥቃቱ ከኤርትራ ወገን መሆኑንን አመልከተው ኪሳራ ማድረሳቸውን ገልጸውም ነበር።

ይህን የጦርነት ግጭት ኢትዮጵያ ትግራይ አካሏ በመሆኗ እንዴት ልታየው ነው? ሚናዋስ ምን ሊሆን ይችላል? የሚሉ ሰፊ መነጋገሪያ ጉዳዮች ቢኖሩም ለአል አይን ይህን አሳብ አስመክቶ ዶክተር ለገሰ ፣ህወሃት ትንኮሰውን የሚፈፅመው ሁለቱን ሀገራት ወደ ግጭት ለማስገባት እንደሆነ ጠቅሰው፣ “ኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ምንም ቢሆን ልዩነት አይፈጠርም። አይሳካም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የትህነግ ሰራዊት በአሜሪካ የአየር ላይ ምልከታ ” ጂፒኤስ” እገዛ ይደረግለት እንደነበር፣ በዚህም የኢትዮጵያ ሃይሎች አሰላለፍ፣ ብዛት፣ አቅጣጫ፣ የከባድ መሳሪያ አሰላለፍ በምስልና በሂሳብ እየተሰላ ይደርሰው እንደነበር በወቅቱ ይፋ ያደረጉ ወገኖች እንደሚሉት አሁንም ትህነግ ይህን ድጋፍ በማግኘት ኤርትራን ለማጥቃት መነሳቱን እየገለጹ ነው።

በፕሬዚዳንት ኢሳያስ ላይ ጥርሷን የነከሰችው አሜሪካ በሶማሌ መንግስት እንዲለውጥ ብታደርግም ሕዝብ ደስተኛ እንዳልሆነ የጀርመን ድምጽ እንግሊዘኛ ክፈለጊዜ የሞቃዲሾ ዘጋቢ ማመልከቱ የሚጠቁሙ ” አሜሪካ በሶማሌ እንዳደረገችው ኤርትራ ማድረግ አትችልም። የኤርትራ ህዝብም እሺ አይልም። ስለዚህ አሁን ያለው አማራጭ ትህነግን በማገዝ በወታደራዊ ሃይል ኢሳያስን ለማስወገድ መሞከር ነው” እነዚህ ክፍሎች ትህነግ ከአሜሪካ ሙሉ ድጋፍና እውቅና እንደተሰጠው ያምናሉ። ይህ ባይሆን ከቶውንም ትህነግ በራሱ አቅም ወደዚህ ጦርነት ለመግባት አይወስንም። አሁን ጥያቄ የሆነው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አቋም ነው።

በተለያዩ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ጫና የኢትዮጵያን መንግስት አንቃና አስገድዳ የያዘቸው አሜሪካ በመደረደሪያዋ ላይ ለጊዜው ያስቀመጠችውን ኤች አር 6600ን ጨምሮ ለዚህ ተግባር ለትተቀም እንደምትችል ይገመታል። ወደ ወልቃይትና አፋር “ከበባ ለመስበር” በሚል ሰፊ ዋጋ የከፈለው ትህነግ ከኤርትራ ጋር ሙሉ ውጊያ ከገባ ኢትዮጵያ በአሜሪካ ማስፈራሪያ ተቀፍድዳ ተመልካች ትሆና ይሆን?

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሃላፊ ሚኒስትሩ ” ተንኳሹ ትህነግ ነው። አላማውም ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማጋጨት ነው” ሲሉ የገለጹበት አግባብ ለጊዜው ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ምንም አይነት ነፋስ እንዲነፍስ አለመፈለጓን የሚያሳይ መስሏል። እንደውም የኢትዮጵያ መከላከያ በተጠንቀቅ በያለበት ልምምዱን እያደረገ እንዲቆይ መታዘዙ፣ መንግስትም ሆነ የሰራዊቱ አመራሮች በአጭር ጊዜና አነስተኛ መስዋዕት ጠላትን በማያዳግም አኳኋን መምታት የሚችልበት አቋም ላይ እንደሚገኝ ማስታወቃቸው ትርጉሙ ሌላ እንደሆነ የሚገልጹም አሉ።

በቅርብ ጊዜያት ብቻ በርዳታ ስም ወደ መቀለ ሲደረጉ የነበሩ በረራዎች ለትህነግ ሃይሎች በትከሻ ላይ የሚያዘውን የአየርና የታንክ ማቃጠያ መሳሪያ አቀብለው ይሆን? የሚለው ጥያቄ የበርካቶች ነው። ይህ አሜሪካ ሰራሽ በትከሻ የሚያዝ ቀላል ግን ዘመናዊ ጸረ አውሮፕላንና ታንክ፣ በዩክሬን ጦርነት ሩሲያን ያስቸገረ እንደሆነ እየተነገረለት ነው። ቀደም ሲል ” መቋቋም ያልቻልነው የድሮን ጥቃት ነው” ሲሉ የትህነግ አመራሮች ማስታወቃቸው ይታወሳል። እናም ስንቅ በብዛት እየገባለት ያለው የትህነግ ሃይል ይህን መሳሪያ አግኝቶ ከሆነ፣ በጂፒኤስ ከተረዳ ለኤርትራ ፈተና እንዳይሆን የሚል ስጋት አለ። ትህነግ ወደ አማራ ክልልና አፋር በእግረኛ ሃይሉ ዳግም ቢመጣ ህዝብ በጥፍሩም ሆነ በጥርሱ ስለሚዋደቅ እንደማይሞክረው የሚገልጹ ኢሳያስና አብይ አህመድ ለዚህ መላ ማፈላለግ ሊከብዳቸው እንደማይችል፣ ሩሲያም ኤርትራን በመሳሪያ ማደርጀቷ ሌላው ስጋቱ ከስጋት በላይ እንዳይሄድ የሚያደርግ እንደሆነ የሚጠቁሙም አሉ።

ትህነግ በራሱ መሪዎች ሊሰጥ፣ ሲሰጥ ይጋብኝ እንደማይጠይቅ አምኖ በፈረመው መሰረት የባድመን ጉዳይ በመቋጨት ለትግራይም፣ ለኤርትራም፣ ለተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ሰላም እንዲሰፍን ትልቁን ድርሻ ሊወጣ እንደሚችል፣ ከጊዜ በሁዋላ ህዝብ ድነበሩን አፍርሶ እንድነበረው እንደሚኖር ልምዳቸውን ገልጸው የሚናገሩ አሉ።

Advertisements
Advertisements


 • Ethiopia reaffirms support for One-China Policy
   Ministry of Foreign Affairs (MoFA) has announced that Ethiopia has been pursuing the One-China policy over the years and the government also holds that same policy in its relation with China. Talking to local media, MoFA Spokesperson Ambassador Meles Alem said that the One-China policy is […]
 • “Ethiopia will Continue Efforts for Peace, Stability in the Region, World”
   Defense Minister, Abraham Belay said that Ethiopia will continue its efforts in a strengthened manner towards ensuring peace and stability of the region and the world at large. Defense Minister, Abraham Belay has participated in the second China-Africa Peace and Security Forum of Ministerial meeting. In […]
 • T- TPLF continues theft of public assets
  The Terrorist TPLF has been actively practicing its old and inborn habits of embezzling public resources, Salsay Weyane Tigray, political party said. Party Communication Head Hailu Kebede said that the T- TPLF has been robbing different commodities that have been  delivered to Tigray state in the […]
 • Top Ethiopian Military Officials Visit Somalia
  Deployment Head of Ethiopian National Defense Force and Somali Region’s Temporary Security Command Post Coordinator visit South West State of Somalia, Baidoa.The military officials went there to discuss peace and security cooperation between Ethiopia and Somalia.The delegation was received by Commander of Sector Three, Brigadier General […]

Leave a Reply