Site icon ETHIO12.COM

በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከ1.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተሰባሰበ

መንግስት ያቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በኢፌዴሪ ሚሲዮኖች አስተባባሪነት በተከናወነ የሀብት ማሰባሰብ ሂደት በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከአንድ 5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተሰባሰበ።

ከተሰባሰበው ገንዘብ ውስጥ አንድ ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር፣ 59 ነጥብ 3 ሺህ ዩሮ እንዲሁም 53 ሺህ ፓውንድ የሚገኝበት ሲሆን፣ 35 ሺህ የአሜሪካን ዶላርና 8ሺህ ዩሮም ቃል ተገብቷል።

በዚሁ ጊዜ ውስጥ ከ8 ሚሊዮን ዶላር በላይ ግምት ያላቸው ቁሳቁሶች መሰባሰባቸውም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለተሰባሰበው ከፍተኛ መጠን ያለው ሀብት ምስጋናው አቅርቧል።

ዳያስፖራው በሚሲዮኖች አስተባባሪነት በኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስቴር በተዘጋጁት አካውንት ቁጥሮች ማለትም ለዩሮ (1000439142832)፣ ለዶላር (1000439142786) እንዲሁም ለፓውንድ (1000443606304) በመጠቀም ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ የአይዞን ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ አማራጭን በመጠቀም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀርቧል።

Via ENA

Exit mobile version