Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ስንዴ እንድትልክ የሚያስችል ስምምነት ተደረሰ

 ኢትዮጵያ ወደ ኬንያ የስንዴ ምርት እንድትልክ የሚያስችል ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መሪዎች መካከል ተደረሰ፡፡ ሰምምነቱ የተደረሰው የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በይፋዊ የስራ ጉብኝታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

የኬንያ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው፥ የስንዴ አቅርቦት ስምምነቱ በኬንያ የተከሰተውን የምግብ ምርቶች የዋጋ ንረት ለማረጋጋት አስተዋፅኦ ይኖረዋል። ከስንዴ አቅርቦት ስምምነቱ በተጨማሪ መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ አቅም ለመጠቀም በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ የሁለቱን የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና የድንበር ተሻጋሪ ንግድን ለማሳደግ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የዘገበው ፋና ነው።

መንግስት በሚቀጥለው ዓመት ስንዴ ወደውጭ መላክ የሚያስችል ደረጃ ላይ መደረሱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ወልቃይት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመስኖ ስንዴ በስፋት እንደሚዘራ፣ በሶማሌና አፋር ክልል ሚዳ ላይም በስፋት ስንዴ ለማመረት ከወዲሁ ዝግጅት መደረጉም ጎን ለጎን እየተዘገበ ነው።

Exit mobile version