ቁጥር እንስጥ ከተባለ ትናንትም ፣ ዛሬም፣ ነገም የአማራም የኢትዮጵያም አንደኛ ጠላት ህወሓት ነው። ህወሓት ማለት ለአንድ ሺህ ዘመን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከማልቀስና ከማፍረስ የዘለለ አዎንታዊ አስተዋፅኦ የሌለው ፣ በየዘመኑ እያገረሸ ሀገር የሚያደማ አውራጃዊ ልሂቅ መንፈስ ነው። ህወሓት የዝርፊያና የደም ማፍሰስ ምሱን ትቶ ፣ ከዳርቻ ፖለቲካ ወጥቶ በሰላም ለመኖር ተፈጥሮው አይፈቅድለትም። በመጀመሪያ ደረጃ ይህን ኃይል ከትግራይ ህዝብና ከትግራይ እጣፋንታ ለመነጠል ድፍረትና ብልሃት የሌለው መፍትሔ ፋይዳ ቢስ ነው።
- የሀገራችን ጉዳይ ከእለት እለት ይበልጥ የማይጨበጥና አስጊ እየሆነ ነው። የትግራይ ወራሪ ኃይል የለኮሰው ጦርነት በምን እንደሚቋጭ አይታወቅም። በአንድ ወገን ህወሓት ለጦርነት እየተዘጋጀ ፣ ኦነግ/ሸኔና ሌሎች የአመፅ ኃይሎች ይበልጥ እየተጠናከሩ ነው። በሌላ ወገን አማራው ከወረራው ጉዳት እንዳያገግም ፣ ለደህንነት ስጋቱ መፍትሔ እንዳይፈልግ ውስጣዊ ሰላም እያጣ ነው። በዚህ ሁሉ ትርምስ ላይ የሰላምና ድርድር ወሬ ይናፈሳል ፤ የሀገራዊ ምክክርና ውይይት ይደገሳል።
- ዘላቂ መፍትሔ ከፈለግን ከማይጥሙ ጥያቄዎች ጋር መጋፈጥ አለብን። የጦርነትን አስከፊነት አይተናል ፣ ለሰላምስ የምንከፍለው ዋጋ ምን ያህል ነው? ስለሰላም የምንመክረውና የምንደራደረው ከማን ጋር ነው ? በማን ኪሳራ ፣ በምን ስሌት ነው ሰላም የሚመጣው ?በተለይ ህወሓት የሰላም ዋጋ የሚገባው ፣ ለሰላማዊ ድርድር ክብር ሊሰጠው የሚገባ ኃይል ነው ወይ ? ከእንግዲህ ትግራይና የትግራይ ህዝብ ከአማራም ሆነ ከኢትዮጵያ ጋር የሚኖራቸው እጣፋንታ ምን ሊሆን ይችላል?
- ቁጥር እንስጥ ከተባለ ትናንትም ፣ ዛሬም፣ ነገም የአማራም የኢትዮጵያም አንደኛ ጠላት ህወሓት ነው። ህወሓት ማለት ለአንድ ሺህ ዘመን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከማልቀስና ከማፍረስ የዘለለ አዎንታዊ አስተዋፅኦ የሌለው ፣ በየዘመኑ እያገረሸ ሀገር የሚያደማ አውራጃዊ ልሂቅ መንፈስ ነው። ህወሓት የዝርፊያና የደም ማፍሰስ ምሱን ትቶ ፣ ከዳርቻ ፖለቲካ ወጥቶ በሰላም ለመኖር ተፈጥሮው አይፈቅድለትም። በመጀመሪያ ደረጃ ይህን ኃይል ከትግራይ ህዝብና ከትግራይ እጣፋንታ ለመነጠል ድፍረትና ብልሃት የሌለው መፍትሔ ፋይዳ ቢስ ነው።
- የዋህ አንሁን። ከታሪክ አንፃር የአንድ ሚሊኒየም ጣረሞት የተጫነውን የአማራና የትግራይን ህዝብ “ወንድማማችነት” እንደተማላ መልሶ ነፍስ መዝራት ጉም እንደ መዝገን ዓይነት ነው። ከቶንስ የአማራ ህዝብ ከአጋም ጉርብትና የተረፈው ከውጋት ፣ ከሸክምና አመድ አፋሽነት ሌላ ምንድነው ? የትግራይ ህዝብ ከተጣወረው የህወሓት መንፈስ ፍፁም ካልተላቀቀ በቀር የአማራም የሌላውም ህዝብ ወዳጅ ይሆናል ማለት ዘበት ነው። ያለፉት 40 ዓመታትን ቁስል ለማሻር እንኳን ገና በርካታ በጎ ትውልዶችን ይጠይቃል።
- ካነሳነው አይቀር “ጦርነቱ የአማራ አይደለም ” ፣ “ወያኔን አሳልፈን ከኦህዴድ – ብልፅግና እንገላገል” የሚሉት ሃሳቦች የደደቦች ፣ የክፉዎችና የሰነፎች ናቸው። ደደቦች ስለማይሰሙ እንዝለላቸው። ክፉዎች የአማራን ህዝብ በጠላትነት መርዘው ለማዳከምና ለማጥፋት የማይተኙ አዛኝ ቅቤ አንጓቾች ናቸው። ከአማራው በላይ አማራ መስለው ግፍና በደል ይዘረዝራሉ ፣ ሬሳ ይቆጥራሉ። “ህወሓትስ ከዚህ በላይ ምን በደለህ ?” እያሉ አማራ ጠላቴ ነው ብሎ የተነሳ ብቸኛ ድርጅትና ለአርባ ዓመታት በግልፅ ሲያደማው የነበረ መሆኑን ፣ ህወሓት የኦህዴድም ፣ የብአዴንም ፣ የብልፅግናም ፈጣሪነቱን ለመሸፈን ይባጃሉ። ሾርት ሚሞሪ አይደለንም!
- ሰነፎች ያው ገልቱዎች ናቸው። ከ1983 ታሪክ የመማር እንኳን ወኔ የላቸውም። ትግልና መስዋዕትነት ፣ ላብና ደም መክፈል አይፈልጉም። እነሱ በሚዲያ ፈረስ ተፈናጥጠው ፣ ምናባዊ ግንባር ከፍተው ያዘው ፣ ፍለጠው ቁረጠው ሲሉ ይውላሉ። አፈር ሳይነካቸው ህወሓት ቆስሎ ደምቶና እንደ አንበጣ ሞቶ ሥልጣን በወርቅ ሳህን እንዲሰጣቸው ይፈልጋሉ። ወንድሜ ! ብልፅግና በድሎኛል ፣ አብይ አንገሽግሾኛል ካልክ ወገብህን ጠበቅ ፣ ሀሞትህን ዋጥ አድርገህ መታገል እንጂ በወያኔ ጀርባ ታዝዬ ልሞሸር ማለት አፀያፊ ነው።
- ጦርነት የሰውን ልጅ አውሬ የሚያደርግ እጅግ አስከፊ ድርጊት ነው። በገዛ ቤታችን አይተነዋል። ነገር ግን ሰላም በአንድ ወገን ምኞትም ሆነ ፀሎት ፣ ኪሳራና ተንበርካኪነት አይመጣም። አንድ ሺህ ጊዜ ተፈትኖ ያላዋጣ መፍትሔ በመድገም አይገኝም። ሰላም ለማግኘት ጠንክሮ መስራትና ለጦርነትም መዘጋጀት የግድ ነው። አስቸጋሪ ውሳኔዎችን በጥበብና በአስተዋይነት መውሰድ ፣ የሩቢከንን ወንዝ በቆራጥነት መሻገር ያስፈልጋል። ነቀርሳውን ህወሓትን ቆርጦ መጣል ለኢትዮጵያም ፣ ለአማራም ፣ በአጠቃላይ ለአፍሪካ ቀንድም ዘላቂ ሰላም የማይታለፍ ቅድመ ሁኔታ ነው። ለትግራይም ህዝብ ታላቅ ውለታ ነው።
ይህ ጽሁፍ በጁን 11,2022 የተጻፈ ነው ። ጸሐፊው Dr. Tewodros Hailemariam ናቸው። ጠቃሚ መልዕክት አለው በማለት አቶ ውብሸት በቴሌግራም ገጻቸው ካካፈሉት እንዳገኙት ጠቅሰው አንባቢ የሆኑ ልከውልን አትመነዋል። አቋሙም ሆነ አሳቡ የጸሃፊው ነው።