Category: OPINION

«መጥፎ ስራ እንዲህ ነው – መጠጊያ መሸሸጊያ ያሳጣል» – ጁንታው አንዴት አንደፈራረሰ ምስክርነት ከግዳጅ ቀጣና

አሁንም አብሯቸው መቃብራቸው ድረስ የተከተላቸው ነገር ቢኖር ውሸታቸው ነው። እየሞቱ ገደልን ፣ እየተደመሰሱ ደመሰስን ፣ እየተቀበሩ ቀበርን ፣ እየጠፉ አጠፋን የሚለው አሳሳች ፕሮፖጋንዳቸውን በተከፋዮቻቸው ቢያሰራጩም ወጣቱን የስርዓት ጠባቂ ሊያደርጉት ቢሞክሩም ከመደምሰስ አላተረፋቸውም።

“የግብፅ መሠረታዊ ችግርም ያለው ሱዳን ከግድቡ ለምን ትጠቀማለች ከሚል የሚመነጭ ነው”

በአሸረቅ S24 ቴሌቪዥን ሱዳናዊ ምሁርና ባለስልጣን የሰጡት ሐሳብ ነው። ° ጋዜጠኛው — “ለዚህ አባባልዎ ማስረጃ አለዎት?”“ብዙ አለ ። ዋናው መሠረታዊ ችግር ከአባይ ወንዝ አጠቅላይ ውሃ 50 ቢሊዮን ኪዩቢክ ምንጩ ብሉናይል ነው ይህ ከፍተኛ ውሃ ሚመጣው ደግሞ ለ3 ወር ነው ማለትም ከጁን አጋማሽ እስከ ሴብቴምበር ግማሽከዚህ በኋላ የውሀው ሀይል […]

የ“ጄኖሣይድ ” ፕሮጀክቶች የደም ፖለቲካ አራማጆች የመጨረሻው የትርምስ እቅድ!!

ለማጋደል በጀት ይመደባል። በጀቱን የሚያከፋፍሉ አሉ። በበሉት መጠን ሰው ለማረድ የሚሰማሩት ወደ ማረዱ ከመግባታቸው በፊት ” ነጭ ነጯን” ምናምን እያሉ መርዝ ያሰራጫሉ። ስልጣን የተከለከሉ፣ የትህነግ ቅሪቶችና የቀድሞ ካድሬዎች በብሄርና ሰባኪነት ስም ተከልለው በተቆርቋሪነት ካባ ተጀቡነው የልቂት ከበሮ እየተናበቡ ያራግባሉ። መንግስትን በየመካከሉ እያስገቡ ማስጠንቀቂያ ይሰጣሉ። እርዱ እንዲከናወን በተወሰነበት አካባቢ […]

ግብፅና ሱዳንን ፀጥ የሚያሰኘው የኢትዮጵያውያ ጀግና – ዶ/ር ስለሺ በቀለ አውላቸው

በህዳሴ ግድብ በስሜት ጋልበው” ኡኡ “የሚሉትን ግብፅና ሱዳንን ፀጥ የሚያሰኘው ያልተዘመረለት ጀግና – ዶ/ር ስለሺ በቀለ አውላቸው የዶክትሬት ማዕረግ ያላቸው ብዙ ሺ ኢትዮጵያውያን አሉ ። ግማሹ ሀገሩን እረስቶ በብሄር ተቧድኖ አንደ አፍላ ጎረምሳ ሲሰዳደብ ይውላል። ከፊሉ ምንም ሳይሰራበት ዶክትሬት ዲግሪ አለኝ እያለ ሲፎክር ይውላል። ግማሹ የተሻለ ብር ለማግኘት […]

ሱሃይር መታለች – ለካይሮው መንግስት መርዝ፣ ለሱዳን መንግስት ጭንቀት፣ ለሀበሾቹ ብርታት

ፁሁፏ ከመለቀቁ የተነሳ የአረብ ሶሻል ሚዲያዎች አንድ መቶ ሰማንያ ዲግሪ ተለውጠዋል!.ፕሬዝዳንት ሲሲ ሱዳን ለጉብኝት ሊመጣ መሆኑን ከሰማችበት ቀን ጀምራየፀረ አይሲሲ መንግስት ተቃውሞ ጠርታ የሱዳንን ከተሞች በተቃውሞ አጨናንቃለችሲሲ እንደ ብርቱካን በካርቶን የመጣ እስኪመስል ድረስ ተሸማቆ ምሳ እበላበት ቤተመንግሥት እራቱን እንዳይደግም አድርጋለች (ብዕረኛዋ ሱሀር ) ከዛን ግዜ ጀምራ ድምጿ ጠፍቶ […]

ትግል መልኩን እየቀያየረ ይቀጥላል . . .

ከ1997 ጀምሮ የምመኛትን ኢትዮጵያ ለማየት በግልም በድርጅትም ታቅፌ የተቻለኝን ጠጠር ወርውሬያለሁ። ትናንትም ዛሬም ኢትዮጵያ አሸንፋ፤ ያለ ልዩነት ለሁሉም ዜጎቿ የተስፋ ምድር ሆና ከማየት የዘለለ ህልም የለኝም። የፖለቲካ ትግል የማደርገውም ከዚሁ የፀና መሻት የተነሳ ነው! እነሆ ዛሬ አምርሬ እታገለው የነበረው ህወሓት የለም። በኢትዮጵያ ምድር የረጨው መርዙ ግን ብዙ ትግል […]

የአባይ ግድብ ሁለተኛ ሙሊት እንዳይከናወን ግብጽ ከሰማይ በታች ማንኛውንም አማራጭ እንድትጠቀም…

ከሁለት ወራት በፊት ግብጻዊው ምሁር ያሰራጩት መልዕክት የግብጽን ቀጣይ አካሄድ የሚጠቁም ነበር። የአባይ ግድብ ሁለተኛ ሙሊት እንዳይከናወን ግብጽ ከሰማይ በታች ማንኛውንም አማራጭ እንድትጠቀም የሚገፋፋ፡ የሚያበረታታ ነው። ይህ ጽሁፍ በአንድ ምሁር ቀረበ እንጂ የግብጽ መንግስትን እቅድ በጎን እንድናውቀው ሆን ተብሎ የተደረገ ለመሆኑ አሁን ላይ ከሚሆኑት ክስተቶች ተነስቶ መግለጽ ይቻላል። […]

“የምናስተውላቸው ሀገራዊ ፈተናዎች እንደ ፖለቲካ ብቻ ሳይሆን እንደ ማኅበረሰብም መውረዳችንን አመላካቾች ናቸው፡፡” ረ/ፕ ሽመልስ ኃይሉ

በታሪክ አጋጣሚ ጠንካራ እና ታላቅ ሀገረ-መንግሥት የገነቡ ሀገሮች ለታላቅነት የበቁበት ታላቅ ሚስጥር ሀገራዊ እሳቤዎችን ከውስጣቸው ስለገነቡ ነበር፡፡ ከፈረንሳይ እስከ እንግሊዝ፣ ከጀርመን እስከ ጣሊያን፣ ከአሜሪካ እስከ ጃፓን፣ ከቱርክ እስከ ደቡብ ኮሪያ፣ ከሩሲያ እስከ ቻይና የምናያቸው የዓለም ታላላቅ ሀገራት እና መንግሥቶቻቸው የተፈጠሩት ከፍ ካለ ሀገራዊ ሃሳብ እንጂ ከልዩነቶቻቸውማ ለተደጋጋሚ ጊዜ […]

ʺጌታውን መስሏልና ሐይቁን በድንጋይ ታንኳ ተሻገረው”

የሚመስሉትን ፀጋውን ያለብሳቸዋል፣ ይመስላቸዋል፣ የማይመስሉትን ደግሞ ይቀጣቸዋል፤ ምድር ለሰው ልጅ ተሰጠች፤ ሰውም በምድር ላይ ነገሰ፡፡ ምድርን የሰጣቸውን እንዲያስቡና እንዲያከብሩም ትዕዛዝ ተሰጣቸው፡፡ ሕጉን የጠበቀ ሁሉ ምድርን ይገዛል፤ የሚገዛት ምድርም ትጠበቅለታለች፡፡ ሕጉን ያልጠበቀ ሁሉ መከራው ይፀናበታል፡፡ የሰማይ ዓይኖች ምድርን ተመለከቷት፡፡ ምድርም በሐጥያት አድፋለች፡፡ ሕዝቡ ሁሉ በአላፊ ነገር ተጠምዷል፡፡ አንዲት ምድር […]

ያልተሟሸ ፓርቲ ሃገር ያገነፍላል!

ሃገርን የመምራት ተግባር በተወሰኑ አመራሮች ብቻም የሚፈፀም ተግባር አይደለም። ይልቁንም በትውልድ ቅብብሎሽ በተተኪዎች የሚፈፀም ረጅም ጉዞ ነውና።ካልሆነ ግን በየጊዜው ድንገት ሳያስበው ወደ አመራርነት የሚመጣ ድንገቴ “አመራር” ልክ እንዳልተሟሸ ጀበና ይሆንና ሃገር ስትገነፍል ትቀጥላለች። ምጣድም ሆነ ጀበና በደንብ ከተሟሸ እንጀራውም ያምራል ቡናው ይጣፍጣል። ነገር ግን ያልተሟሸ ምጣድ እንጀራ እና […]

ስለኔ ፀሐይ እየተቃጠለ በጥላ ያሻግረኛል!!

መጋቢት 22 ቀን 2013. የጉዞ ማስታወሻ ‹‹ሰብዓዊነትና ፍቅር ለትግራይና ለመተከል ›› በሚል ከአርቲስት ፣ አክቲቪስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ ጋር ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ መስራት ከጀመርኩ ሁለት ወር ሲጠጋኝ ነው ፡፡ የመጀመሪያው ዙር ድጋፍ ወደ መተከል ከሚወስዱት አባላት ውስጥ ቦታውን በደንብ ስለምታወቀው ተብሎ ከሜሮን እና እዮብ ጋር ተመድቤያሁ […]

ወሎ አግላይ ወይስ አቃፊ? ዶ/ር ሁሴን አዳል መሐመድ

“–ለዜጎች የሚሻለው በቋንቋ ግድግድ አጥር ውስጥ መታጠር ሳይሆን ዴሞክራሲያዊ መብቱ ተከብሮ፣ በዕኩልነት የሚኖርበት ሐገር ባለቤት መሆን ነው፡፡–” ወሎ የዘርም ሆነ የኃይማኖት አግላይነት የሌለበት ሁሉን አቃፊ ክ/ሐገር ወይም ብሔር ነው፡፡ የ1960ዎቹ የብሔር ትግል አቀንቃኝ ተማሪዎች በተገነዘቡት ልክ ከቀሰሙት የማርክሲስት-ሌኒኒስት አስተምህሮ በመነሳት፣ ለብሔር/ብሔረሰብ የሰጡት፣ “ያልጠራ አፋጅ ትርጉም” አለ፡፡ ይህን ከባዕድ […]

«በ1976-77 ዓ.ም ከቀድሞው ላስታ አውራጃ ወለጋ እንዲሰፍሩ ከተደረጉት እኔና እናቴ እንገኝበታለን» Fisseha Tegegn

በ1976-77 ዓ.ም ከቀድሞው ላስታ አውራጃ ወደተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በግዳጅ ተወስደው እንዲሰፍሩ ከተደረጉት ላስቴዎች መካከል እኔና እናቴ እንገኝበታለን፡፡ በወቅቱ በነበሩት የገበሬ ማህበራት አማካኝነት ከየአካባቢው ቤተሰቦች እንዲመረጡ ከተደረገ በኋላ እኛም ወደ ሌላ ቦታ ተወስደው እንዲሰፍሩ ከተወሰነባቸው መካከል በመሆናችን እኔ፣ እናቴና እኛን ለመሸኘት በሚል የእናቴ ወንድም አጎቴ ሆነን ከገጠሯ ‘ብርግነት’ ‘ሰማይ […]

አልሲሲ «የግብፅን ውሃ አንዲት ጠብታ እነካለሁ የሚል ይሞክር… ይህ ለግብፅ ቀይ መስመር ነው»

የግብፁ ፕሬዝዳንት አልሲሲ «የግብፅን ውሃ አንዲት ጠብታ እነካለሁ የሚል ይሞክር:: የግብፅን ውሃ አንዲት ጠብታ ለመንካት የሚደረግ የትኛውም ሙከራ አጠቃላይ ቀጠናውን ያተራምሰዋል:: ይህ ለግብፅ ቀይ መስመር ነው:: >> ብሏል:: አክሎም << ይህን ስል ግን ለማስፈራራት ሳይሆን የህዳሴ ግድብን አሞላል እና ኦፕሬሽን በሚመለከት ህጋዊ ስምምነት ላይ እንደርሳለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ:: […]

የአርተፊሻል ደመናው ነገርስ?

ግብፅ “ኢትዮጵያ የግድቡን የውሃ መጠን በሳተላይት እንዳላይ ሆን ብላ አከባቢው በአርተፊሻል ደመና እንዲሸፈን አድርጋብኛለች” ብላ የመክሰሷ ነገርስ? ባሻዬ – የዝናቡ ሲገርምህ ደመናውን ጨመረልህ? በእርግጥ የህዳሴው ግድብ ከሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል ባሻገር ለኛ ለኢትዮጵያውያን፦ ታሪክ ነው – የአሁኑ ትውልድ አሻራ ዳግማዊ አድዋ ነው – መዘከርያ የመደራደርያና ተፅዕኖ መፍጠሪያ አቅማችን ነው […]