ETHIO12.COM

የትህነግ “[የአማጺው] ሃይል በደረሰበት ጥቃት ለመፈራረስ ቋፍ ላይ ነው” አሌክስ ዲዋል

በትግርኛ መግለጫ ” እኛ ደጋግመን ተናግረናል።የኤርትራ ህዝብ እኛ በተናገርነው ሃሳብ ላይ የመረዳት ችግር አለበት ብዬ አላምንም።አሁንም ግን ደግሜ ልናገር።የኢሳያስ መንግስት የኤርትራን ሉዓላዊነት እና ነፃነት ከማይቀበሉ ሰዎች ጋር ህብረት ፈጥሯል።ይሄ ደግሞ ሄዶ ሄዶ የኤርትራን ሉዓላዊነትና ነፃ አገርነት ጥያቄ ውስጥ የሚጥል ነው”

“አብይ አህመድና ኢሳያስ አፉወቂ ወደ ማብቂያቸው እያመሩ ነው” ሲሉ የትግራይ አማጺው ቡድን ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ። ጦርነቱን የሚከታተሉ በበኩላቸው ነገሮች እያበቃላቸው መሆኑንን አመልክተዋል። አቶ ጌታቸው የኢትዮጵያና ኤርትራ መሪዎች ወደ ማክተሚያቸው መዳረሳቸውን ባስታወቁበት ቅጽበት አሌክስ ዲዋል የትህነግ ሰራዊት መፈረካከሱንና የአቅም አልባነት ነጥብ ላይ መድረሳቸውን ይፋ አድርጓል። አሌክስ ከትህነግ ሃይሎች ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው በመሆኑ መረጃው ጥርጥር እንደሌለው ተመልክቷል።

አሜሪካና አውሮፓ በአስቸኳይ ኡሁሩ ኬንያታን በማገዝ ሊከሰት የሚችለውን ጄኖሳይድ ለማስወገድ ጣልቃ እንዲገቡ የጠየው አሌክስ ድዋል፣ ጌታቸው ረዳ ጋር የተስማሙት ጦርነቱ ያለማቋረጥ ሃምሳ ቀን መደረጉና ዓለም ጣልቃ የመግባቱ ጥሪ ላይ ብቻ ነው።

እንግሊዛዊው አሌክስ ዲዋል ሃምሳ ቀን ያለማቋረጥ ጦርነት መካሄዱን አመልክቶ የኢርትራና የኢትዮጵያ ጦር በጣምራ የትህነግን ሰራዊት አሽመድምደው ወደ መፈረካከስ ደረጃ አድርሰውታል በማለት ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚወጡትን መረጃዎች አግባብነት አረጋግጧል። ጥሪውን የሰሙት አንቶኒ ብሊንከንም ተመሳሳይ አሳብ ቲዊት አድርገዋል።

It is incumbent on all armed actors to respect and protect civilians, and we call on them to allow unhindered humanitarian access to all Ethiopians in need.

We reiterate that the government of Ethiopia and Tigray regional authorities should immediately cease all hostilities and participate seriously in the forthcoming African Union-led peace talks.  The United States is fully engaged with the African Union, the governments of Kenya and South Africa, and other international and regional partners to organize and mediate peace talks as soon as possible. https://www.state.gov/intensifying-military-operations-in-northern-ethiopia/

ከእነ ማርቲን ፕላውት ተርታ ለረዥም ዓመታት የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ተሟጋችና የሚዲያ አጋር እንደሆነ የሚነገርለት አሌክስ ዲዋል የአማጺው ሃይሎች መፈረካከሳቸውን አቅም አልባ ወደ ሆኑበት ልኬትና ነጥብ ላይ መድረሳቸውን ይፋ ማድረጉ ስለ ጦርነቱ መረጃ አለን የሚሉ ነገሮች ወደ አንድ ምዕራፍ መጠጋታቸው ከገለጹት ጋር የሚስማማ ሆኗል።

አሌክስ ዲዋል

በመንግስት በኩል ለአፍታ እንኳን ትንፍሽ የማይባልበት፣ ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ የማይቀርብበት ጦርነት ” ዲዳው ዘመቻ” ሲሉ በርካቶች ይጠሩታል። ይህ ጦርነት ወደ አንድ በውል ስሙ የማይታወቅ ምዕራፍ መሸጋገሩ ሊታበል በማይችል መልኩ እውነት ከሆነ “ቀጣዩ ምን ሊሆን ይችላል?” የሚለው ጥያቄ አስፍቶታል። ከተለያዩ አካላት የሚሰማውን ይህን ዜና ማስተባበል የተሳናቸው አቶ ጌታቸው ረዳም “ዓለም ዝም አለ” ሲሉ ቅሬታ በማቅረብ “ጀግናው የትግራይ ሰራዊት እየመከተ ነው” ሲሉ ይህን ሃይል ማንበርከክ እንደማይቻል አስታውቀዋል።

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በሚል ስያሜ ላለፉ አምሳ ዓመታት የቆየው ትህነግ “አንድም ቀን ስለ መገንጠል አስቦም፣ አውርቶም አይውቅም” ሲሉ አቶ ጌታቸው አዲስ ነገር ባሰሙበት ማብራሪያቸው በራያ ግንባር፣ በዛላንበሳ፣ በራማ፣ በአዲ አርቃይ፣ … በሁሉም አቅጣጫ ጥቃት መከፈቱን እየተወራጩ አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ በአንዱም ግንባር እንዳልተሸነፉ በማብራራት ዓለም እንደረሳቸውና፣ ጦርነቱ የትግራይን ህዝብ የማጥፋት እንደሆነ በማግለጽ ” አሳባቸው ተሳክቶላቸውል” ሲሉ ደብለቅለቅ ያለና ጭብጡን ሪፖርት ለማድረግ የሚቸግር መረጃ ሰጥተዋል።

የአማጺያኑ ጦር ዋና ሃላፊ የቀድሞ ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ሰፊ ሃይል በየአቅጣጫው ጥቃት መክፈቱን በይፋ ካስታወቁበት ጊዜ ጀምሮ የሚወጡ መረጃዎች ጥምር ጦሩ ከበባውን ማጠናከሩን ነው። አቶ ጌታቸው በአሁኑ መግለጫቸው “አንሰበርም፣ እንፋለማለን፣ አይቻላቸው” የሚሉ የትግል ቃላትና ሃረጎችን ከማከላቸው በስተቀር ቀደም ሲል ጀነራሉ የተናገሩትን እውነት በተዘዋዋሪ ደግመዋል።

” አብይ አሕመድ የኢትዮጵያን ጦር ሙሉ በሙሉ ለኢሳያስ አስረክቧል” ሲሉ የተናገሩት አቶ ጌታቸው “ኤርትራ እዚህ ግባ የሚባል ሰራዊት የላትም” ሲሉ ተደምጠዋል። የኤርትራ አዋጊዎች ማለቃቸውንም አመልክተዋል። መረጋጋት በማይታይበት ንግግራቸው መለስ አድርገው ” ሃይለኛ ምት አሳርፈንባቸዋል” ሲሉ ስለወቅታዊው የጦርነት ሁኔታ አስታውቀው ዓለም እንዲደርስ ጥሪ ያሰማሉ …

ሶስት ጠቅለል ያለ አሳብ ላላቸው የመወያያ አጀንዳዎች ማብራሪያ የሰጡት አቶ ጌታቸው “የምንፈልገውን አበላሽተንና አከናውነን ከቆቦ በራሳችን ፈቃድ ወጣን” ካሉ በሁዋላ ይህ ውሳኔ የተወሰነው በወልቃይት በኩል አብይ አሕመድ ሰፊ ሃይል በማሰማራቱ፣ ይህም የሆነው ለኢሳያስ ሲባል በመሆኑ ያንን ለመከላከል ሲባል ነው ብለዋል። ይሁን እንጂ በተጠቀሱት ግንባር የጥምር ሃይሉ ሰፊ ይዞታ ተቆጣጥሮ ወደፊት መገስገሱን መግታት ስለምቻላቸው በግልጽ ስፍራ ጠቅሰው ያቀረቡት ነገር የለም። እንደወትሮው በመቶ ሺህ መግደላቸውንና በአስር ሺህ መማረካቸውንም አላስታወቁም።

ዓለም ዝም ማለቱን በተደጋጋሚ በንግግራቸው መካከል ሲጠቅሱ የነበሩት የአማጽያኑ ቃል አቀባይ፣ የአውሮፓ ህብረት በተደጋጋሚ ተመሳሳይ አቋም በማራመዱና በጀት በመከልከሉ አድንቀዋል። ሊሎቹ ግን ከመግለጫ የዘለለ ያደረጉት ነገር እንደሌለ አመልክተው ወቅሰዋል። ሲቀጥሉም ለዩክሬን የተደረገው ዓይነት ድጋፍ ቢደረግ ብዙ ነገር ማየት ይችል እንደነበር ገልጸዋል።

በሁሉም አቅጣጫ የጥምር ጦሩ ወደፊት እየሄደ መሆኑና ይዞታውን እያሰፋ መቀጠሉን ተከትሎ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን ማስጠንቀቂያ መሰል አሳብ አስፍረዋል፣ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ተሳታፊ የሆኑ ኃይሎች ግጭቱን የሚያባብሱ ድርጊቶችን እንዲያቆሙ በጠየቁበት የቲውተር መልዕክታቸው ኢትዮጵያና የኤርትራ የትግራይ አማጺ ቡድን ላይ በጋራ እያካሄዱ ያሉትን ጥቃት እንዲያቆሙ ጠይቀዋል። አማጺዎቹ የጠብ አጫሪነት ተግባራቸውን እንዲያቆሙ ሲሉ አሳስበዋል። እሳቸው ይህን ቢሉም ኤርትራም ሆነች ኢትዮጵያ የሰጡት ምላሽ የለም።

አሁን ላይ እንደሚሰማው የአማጽያኑ ሃይል ተሰብሯል። አሌክስ ዲዋል እንዳለው ተፈርካክሶ በየአቅጣጫው ተበትኗል። አንዳንድ የትግራይ አክቲቪስት መሆናቸውን የሚናገሩ አለቆች ሰራዊታቸውን ትተው እየሸሹ ነው።

በቅርቡ የትግራይ ሕዝብ በሙሉ ክተት እንዲል ጥሪ ያቀረበው ትህነግ፣ ሌላ ምን አዲስ ምን ዓይነት ጥሪ እንደሚያቀርብ ባይታወቅም “የቻይነት ወይም ታጋሽነት ባህላችንን አጠናክረን የማንሻገረው ችግርና የማናሸንፈው ጠላት የለም ! አይኖርምም!” ብለዋል።

Exit mobile version