Site icon ETHIO12.COM

አክሱም ነጻ ወጣች – ንግግሩ ሳይጀመር ነገሮች ወደ ድምዳሜ፤ አሜሪካ የመኖሪያ ፈቃድ መፍቀዷ አነጋጋሪ ሆኗል

Axum - Mehakelegnaw Zone, Tigray Region, Ethiopia: domed Church of Saint Mary of Zion - built by Emperor Haile Selassie and modelled on Constantinople's Hagia Sophia - Ethiopian Orthodox Tewahedo Church - photo by M.Torres

መከላከያ የሚመራው ጥምር ጦር አክሱም ከተማን መቆጣጠሩ ተሰማ። ጥምር ሃይሉ ከአደዋ በ፪፭ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን የአክሱም ከተማ መቆጣጠሩ የተገለጸው ዛሬ ረፋዱ ላይ ነው። አደዋንም በቅርብ ርቀት እያየ መሆኑ ተሰምቷል።

በርካታ ከተሞች በመከላከያ አጅ መግባታቸውን ተከትሎ የአሜሪካ የአገር ውስጥ ደኅንነት ከጥቅምት 20, 2022 ጀምሮ ኤሜሪካ እየኖሩ ያሉ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ በጊዜያዊነት 18  ወራት እንዲቆዩ መፍቀዱ ተሰምቷል።

አሁን አሜሪካ ያሉና በግጭት፣ በጎርፍ፣ በድርቅ፣ በመፈናቀል ወይም በምግብ እጥረት ሳቢያ በተነሳ ሰብአዊ ቀውስ ምክንያት ወደ አገራቸው መመለስ የማይችሉ ኢትዮጵያውያን፤ አገራቸው ያለው ሁኔታ እስከሚሻሻል ድረስ አሜሪካ ቆይተው መሥራት እንደሚችሉ የተገለጸው በደቡብ አፍሪካ የሰላም አማራጭ ንግግሩ ሊደረግ ሰባ ሁለት ሰዓታት ሲቀሩት ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት እያነጋገረ ነው። 

አሜሪካ ሰኞ የሚካሂደውንና “ውይይት” ስትል የጠራችውን ስብሰባ ከወዲሁ “ድርድር” እንዳልሆነ ፣አርጋገጫ ሰጥታለች። ይህንኑ ውይይት ደግፋ መግለጫም አውጥታለች። ደቡብ አፍሪካ ይህንን ውይይት ለማስተናገድ በመፍቀዷ አወድሳ የአፍሪካ ኅብረት ልዩ ልዑክ ኦሉሴጎን ኦባሳንጆን ጨምሮ አብረዋቸው ወይይቱን ለሚመሩት ድጋፍ እንደምታደርግ ቃል ገብታለች።
በዚህ መካከል ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ እንደማይቀበል አስታውቆ ወደ ድርድር ያመራው መንግስት፣ አብዛኛውን ትግራይን አየተቆጣጠረና የተቋረጠውን ኣገልግሎት ለማስጀመር በዘመቻ አየሰራ መሆኑንን ደጋግሞ አያስታወቀ ነው። በቁጥጥሩ ስር ያዋላቸውን አየር ማረፊያዎች በመተቀም እርዳታ እንዲሰራጭ፣ ትህይነግ በመጋዘን ያከማቸውንም እህል በማውጣት ለህዝብ እያከፋፈለ መሆኑንን በምስል እያሳየ ነው።

እንደ ቅርብ ሰዎች ገለጻ ከሆነ ንግግሩ ሲጀመር የመንግስት ሃይሎች አድዋን ጨምሮ ተጨማሪ ከተሞችን ይቆጣተራሉ። በሌሎች ከተሞች እንዳደረጉት አስተዳደራዊ መመሪያዎችን በማውረድ የፈረሰ መዋቅር የሚጠገንበት የማስተካከያ ውሳኔ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ ማለት ለንግግር ደቡብ አፍሪካ የገቡት የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር መሪዎች በአገሪቱ ህገመንግስት መሰረት የፌደራሉን መንግስት ህልውና ለማክበር አስቀድመው በወሰኑት መሰረት በትግራይ ላለው ታጣቂ ” ትጥቅህን አውርድ” የሚል መልዕክት በማስተላለፍ ውይይቱ የሰላም መንገዱን እንዲያጸና ከማመቻቸት ውጭ ሌላ ተስፋ እንደማይኖራቸው መሆኑ ቀድሞ እየተሰማ ነው።

ንግግሩን በተፍለገው መልኩ ማስኬድ ካልተቻለ ምን አልባትም በደቡብ አፍሪካ ጥገኝነት ሊጠይቁ የሚችሉበት አጋጣሚ ሊኖር እንደሚችል እየተሰማ ነው። መንግስት እንደመንግስትነቱ ህገ መንግስቱን አስታኮ የሚያቀርበውን ጥያቄ ከመቀበል ውጭ ምንም አማራጭ የሌላቸው የትህነግ አመራሮች ምን አልባትም ልክ የዛሬ ሰላሳ ዓመት በሎንደን ድርድር እንደሆነው መንግስት ቢፈቅድ እንኳን ተመልሰው ሄደው የሚያስተዳደሩት ቀበሌ ሊኖራቸው እንደማይችል የመከላከያን ፍጥነት ያሰሉ እየገለጹ ነው። በዚህም ላይ አሜሪካም ” ሃላፊነቱን እኔ እወስዳለሁ። ተከዳን በሉ” የሚል ፍንጭ መስጠቷን ተሰምቷል። ደጋፊዎቻቸው እንዳይቆጣቸው ” አሜሪካ ከዳችን” በሚል መግለጫ ነገሩ ለጊዜው ሊዘጋ እንደሚችልም የሚጠቁሙ አሉ።

ከሁሉም በላይ ግን መከራ የዘለቃቸው የትግራይ፣ የአማራ፣ የአፋርና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላም መናፈቃቸው የሰሜኑንን ጦርነት ይቋጨዋል የሚለው አሳብ የሚያስማማ ሆኗል።

Exit mobile version