ETHIO12.COM

ትግራይም አረፈች፣ እኛም ተገላገልን … የመጨረሻው ድምጽ

“ተተኪው ትግሉን ይመራዋል” ሲሉ ጥሪና አደራ ያቀረቡት ዶክተር ደብረጽዮን ወደ ደፈጣ ውጊያ የሚያመራ እንደምታ ያለው አሳብ ቢያጋሩም መከላከያ መቀለን ጨምሮ ሙሉ ትግራይን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሚያውጅበት ሰዓት ስለመቃረቡ ፍንጭ እየተሰጠ ነው።

ትናንት ተሲያት የመቀለው አሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ መከላከያ በሚመራው ጥምር ጦር እጅ መግባቱን ተከትሎ ይፋ በሆነ ዜና የትህነግ ተዋጊዎች በሁሉም ግንባር መበተናቸውና “የታደሉ ናቸው” የተባሉ እጅ እየሰጡ እንደሆነ መከላከያ በኦፊሳል የፌስ ቡእክ ገጹ አመልክቶ ነበር።

ለንግግር ወገኖቻቸውን ወደ ደቡብ አፍሪካ የላኩት የድርጅቱ መሪ ዶክተር ደብረጽዮን በውል ባልተገለጸ ቦታ ሆነው በሰጡት መግለጫ ሰራዊታቸው እንደማይቻል አመልከተው፣ ” ትግራይ የገቡት የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጥምር ኃይል አባላት መቀበሪያቸው ትግራይይሆናል” በማለት ነበር የተዋጊዎቹን ሃያልነት ያጎሉት። ይህን ባሉ ሰዓታት ውስጥ መከላከያ ድል አብስሯል። የትህነግ ሰራዊት መበተኑንንም አመልክቷል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በማህበራዊ ገጹ ላይ አስቀድሞ እንዳሰፈረው ተወሰደ ባለው ከባድና ፈጣን ርምጃ የትህነግ ታጣቂዎች መበታተናቸውን አመልክቷል። “የታደሉት” ሲል የጠራቸው እጅ መስጠታቸውን አመልክቶ የተቀሩት ያላቸው ደግሞ “በተሳሳተ መረጃ ተደናግረው ግራ በመጋባት ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንደማያውቁ ጠቁሟል።

መከላከያ ቀድሞ ባሰራጨው ዜና ላይ ይፋ ባያደርገውም የመቀለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ በመንግስት ሃይሎች ቁጥጥር ስር መውደቁ ተገልጿል። ይህንኑ ተከትሎ ለሰላም አማራጭ ንግግር ወደ ደቡብ አፍሪካ ያቀኑት የትህነግ ወኪሎች እጣ ፈንታ በተለያዩ ስሜቶች የማህበራዊ አውዶች መነጋገሪያ ሆኗል።

ዛሬ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት በደቡብ አፍሪካ ንግግሩ መካሄዱን ጠቅሰወና እነማን በታዛቢነት እንደተገኙ አመልክተው መግለጫ ባወጡበት ቅጽበት መከላከያ ” ፈጣንና ከባድ” ርምጃ መወሰዱን፣ ይህንኑ ተከትሎም በርካታ የትህነግ ተዋጊዎች መማረካቸውንና የተቀሩትም መበተናቸውን ማስታወቁ ሁኔታውን በርጋታ ለሚከታተሉ ከንግግሩ ብዙም አዲስ ነገር እንደማይጠበቅ እየገለጹ ነው። አዲስ ነገር ከሆነም ትህነግ መንግስት ያቀረበውንና በውስጥ ተቀብሎ በገሃድ ያላስታወቀውን “የትጥቅ ፍታና እንደ ክልል እያሰብክ ኑር” የሚለውን መሰረታዊ ጥያቄ በገሃድ “ጠብመንጃ አውርደናል” በማለት ማውጅ ብቻ እንደሆነ ተመልክቷል።

በሌላ በኩል መንግስት በወቅታዊ ሁኔታ ማጣሪያ ገጹ ላይ “የሀገር መከላከያ ሰራዊት ዋንኛ ተልዕኮ የሽብር ቡድኑን ወታደራዊ አቅም ማዳከምና ቡድኑ ሰብአዊ ጋሻ ያደረጋቸውን ንጹሃን ዜጎች ነጻ ማውጣት ነው” ሲል ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ መቀለ ሙሉ በሙሉ በመከላከያ ስር ገብታለች ማለት በሚያስችል ደረጃ ጥምር ጦሩ ቀለበቱን እያጠበበ መሆኑ በየአቅጣጫው እየተሰማ ነው።

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር መሪ ዶክተር ደብረጽዮን ንግግሩ ከመጀመሩ ቀደም ብለው ባስተላለፉት መልዕክት፣ “አትችሉንም” ብለዋል፤ ትግራይ የአድሃሪያን መቀበሪያ ነች” ሲሉ ጠላቶቻችን ያሉት የኢትዮጵያ መንግስትም ይህንኑ እንደሚያውቅ አመልክተዋል። የድርጅቱ የውጭ አመራሮችም የደፈጣ ውጊያ እንደሚጀመር፣ ለዚህም ዝግጅት መደረጉን በይፋ እያስታወቁ ቆይተዋል። ቀደም ብሎም ” ትግራይ ሰላም ካልሆነች ኢትዮጵያ ሰላም አትሆንም” በሚል አቶ ጌታቸውን ጨምሮ አመራሩ ማስታወቃቸው አይዘነጋም። ሁሉም ይህን ቢሉም ” ንግግሩ ለአንድ ሳምንት እንደሚቆይ ይፋ መሆኑ ሌላ ዜና ይዞ እየመጣ ነው። የትግራይ ሃይሎች እንዳከተመላቸው የሚገልጹ የትግራይ ሁሉም የአየር ማረፊያዎች በመከላከያ እጅ ከወደቁ፣ በንግግሩ ማብቂያ የትህነግ ሰዎች ወደ ትግራይ መግባት የመቻላቸው ጉዳይ ነው ዜና የሆነው።

“በቅርቡ ለመከላከያ እጅ የሰጡ የአሸባሪው የትህነግ ታጣቂዎች የክፋት አዝማቾቻቸውን ሁኔታ በአንድ ጥሩ የትግርኛ ምሳሌያዊ አነጋገር ገልጸውታል። ማሽላውን ከአደጋ ለመከላከል የከበበው አጥር ለማሽላው እንጂ ራሱ አጥሩን አልጠቀመውም። ይሄም ጁንታው እንጂ ታጣቂዎቹ ከጦርነቱ ያተረፉት እልቂት ብቻ መሆኑን ያሳያል” ሲል ተማራኪዎቹን ጠቅሶ የመከላከያ ዜና “የተበተኑና ከጁንታው የጥፋት ወጥመድ ማምለጥ የሚፈልጉ የጁንታው ታጣቂዎች መከላከያ ወደ ተቆጣጠራቸው የትግራይ አካባቢዎችና ወደ አጎራባች ክልሎች በመሄድ እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ የመከላከያ ሠራዊት ጥሪ ያቀርባል” ሲል ወደ መቀለ እግሩን እያስተጋ ጥሪ አስተላልፏል።

መከላከያ ዛሬ ይህን አለ እንጂ የትህነግ የቅርብ ሰው የሆነው እንግሊዛዊው አሌክስ ዴዋል “የትህነግ ተዋጊዎች ፈርሰዋል። ዜሮ ወደሚባል ደረጃ ለመድረስ ጠርዝ ላይ ናቸው” ሲል ያስታወቀው ከሳምንት በፊት ነው። ይህንንም ብሎ ዓለም ሊደርስላቸው እንደሚገባ ጥሪ ማቅረቡ አይዘነጋም።

በደቡብ አፍሪካ የሰላም ንግግር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፣ በአሜሪካ መንግስትና በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት ተወካዮች በታዛቢነት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ሙሳ ፋኪ ገልጸዋል። አክለውም ሁለቱ ወገኖች ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት መገናነታቸውን ገልጸዋል። የሙሳ ይህ አገላለጽ ቀደም ሲል የአፍሪካ ህብረት ያዘጋጀው ጅቡቲ ላይ በአካል የተደርገ ንግግር ነበር የሚለውን ፕሮፕጋንዳ እርቃን አስቀርቶታል።

ንግግሩን አስመልክቶ ምን እንደሚገመት ፍንጭ ባይሰጥም የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎዛ ቃል አቀባይ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትና በትህነግ መካከል በአፍሪቃ ኅብረት መሪነት ፕሪቶሪያ የተጀመረው የሰላም አማራጭ ንግግር እሑድ ጥቅምት 20 ቀን 2015 ድረስ እንደሚሰነብት አስታወቀዋል። ይህንኑ ተከትሎ ንግግሩ እሁድ ድረስ እንደሚቆይ መገለጹ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከካናዳው አቻቸው ጋር መወያየታቸውን መግለጻቸው፣ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ወደ ካናዳ ለመሄድ ቀጠሮ መያዛቸውና፣ የትህነግ ወኪሎች ወደ ካናዳ ሂደው ቀሪ ህይወታቸውን እንደሚያሳለፉ መሰማቱ ዝም ተብሎ የሚታለፍና ተራ ግጥምጥም እንዳልሆነ እየተነገረ ነው። እስከ እሁድ መቀለ ምን ይሆናል?

ደብረጽዮንን መቀለ አስቀምጦ ወደ ደቡብ አፍሪካ ያመራው ክፍል እጣ ፈንታ በቀናት ውስጥ የሚለይ ሲሆን የኢትዮ 12 የመረጃ አቀባዮች ” አሜሪካ አታለለችን በሉል፤ እኛ ሃላፊነቱን እንወስዳለን” የሚል ቃል እንደተገባላቸው ቃል በቃልም ባይሆን በተዛማጅ ተመሳሳይ ትርጉም ባለው አገላለጽ አመልክተዋል።

አዲስ አበባ ተደምረው ትግራይ እንደሚቀነሱ እየተገለጸ ሲቀለድባቸው የነበሩት የትህነግ ሊቀመንበር፣ የተረፈውንና ወደ በረሃ የገባውን ሃይል ከሚመሩት ጋር ሆነው እስከመጨረሻ እንደሚመሩ ቅንጣት ጥርጥር እንደሌላቸው የሚገልጹ ጥቂት አይደሉም። እነዚህ የትህነግ ደጋፊዎች ዳግም ትህነግ እንደሚያሸንፍም ያምናሉ። ጆቤም አሜሪካ ሆነው ያረጋገጡት ይህንኑ ነው። የጽምቅ ውጊያና ሌላ የታቀደ ሃይል መኖሩን ተናግረዋል። በመንግስት በኩል ደግሞ በትግራይ “ተጨቁነናል” የሚሉና ራስን የመቻል ጥያቄ ያላቸውን አክብሮ ምላሽ ስለሚሰጥ የረሃውን ኑሮ ዕቅድ ያከሽፈዋል ሲሉ ትህነግን የሚቃወሙ እየገለጹ ነው። ከሁሉም በላይ የትግራይ ሕዝብ ሰላም ስለናፈቀው እንደ ቀድሞው ሊተባበር ይችላል ወይ? የሚለው አንኳር ጥያቄ ሆኗል። ይህ መወያያ በሆነበት በአሁኑ ሰዓት የትህነግ አመራሮች ደቡብ አፍሪካ ለንግግር ደቡብ አፍሪካ ናቸው።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ማነጋገራቸው አስታወቀዋል። እዛና እዚህ እየደወሉ የፖለቲካ ስራ የሚስወሩት ብሊንከን አገራቸው ኢትዮጵያ ላይ እያረደገች ያለውን ከልክ ያለፈ ጫና እንድታቆም ሕዝብ በከፍተኛ ቁጣ መጠየቁ ይታወሳል።

ሕዝብ በከፍተኛ ደረጃ ሰላም እንዲወርድ ምኞት ቢኖረውም ከሸኔ ጋር በይፋ ግንባር ፈጥሮ የነበረው ትህነግ አሁን ላይ ” አማራ ወይም ሞት” ማለቱና ላለፉት ሃምሳ ዓመታት በፕሮግራሙ ነድፎና መታገያው አማራን ፈርጆ የፈጸመበት በደል ለሚያውቁ ዜጎች ድርጅቱ ” ጤና የለውም” በሚል ይበልጥ ቁጭት ውስጥ እየከተታቸው ነው። በማናቸውም ዓይነት ሚዲያና ቅስቀሳ ሊስተባበል በማይችል ደረጃ የአማራ ሕዝብ ላይ ትህነግ የፈጸመው ግፍ ” አማራ ጋር ችግር የለብንም” በሚል ማጣፊያ የሚደመሰስ ቀላል የግጦሽ መሬትና ውሃ ግጭት አድርጎ ማሳየት አሁንም ድርጅቱ አማራን ይታለላል ብሎ እንደሚያስብ ማሳያ ከመሆን እንደማያልፍ እየተገለጸ ነው።

” በማጠልሸት፣ በመፈርጅ፣ እንዳይዋለድ በማድረግ፣ በውክልና በመላው አገሪቱ ሰርቶ እንዳይበላ፣ ሰርቶ ያፈራውን እንዲነጠቅ፣ ድረሱልኝ ሲል ‘ወራሪ፣ ነፍጠኛ’ በማለት፣ በቅርቡ በወራራ ከብቱ፣ ውሾቹና ቦሃቃውን ሳይቀር ዘርፈውት፣ ደፍረውት፣ ቀዬው ድረስ ዘልቀው ገለውትና ልማቱን አመድ አድርገው … ሂሳብ አወራርደርውበት የሄዱትን ህዝብ እንዴት ዓይነት ልብና አንጎል ቢኖራቸው ነው ዛሬ እንዲህ የሚሉት” ሲሉ ቁጣቸውን የሚገልጹ አምባሳስደር ሱሌማን ደደፎ ከላይ የተናገሩትን እየደገሙት ነው። ሰላም አስፈላጊ ቢሆንም በዚህ ደረጃ እንደ እቃ እቃ የህጻን ቀልድ ዓይነት ከሚጫወት ድርጅት ጋር ቁጭ በማለት ሊገኝ የሚችለው መልካም ነገር ለበርካቶች አይገባቸውም።

” ትህነግን መረዳት የሚቻለው ባለመረዳት ነው” ሲል ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የተናገርወን የሚደግሙ ከትህነግ ባህሪና ውልደት አንጻር የሚጠበቀውን ሲያስኑ ይጨልምባቸዋል። አመክኖ የሚባል ነገር የማያውቅ፣ ሃፍረትና ይሉኝታ ያልፈጠረበት፣ ያሻውን ቢል የማይጨነቅ፣ አይኑንን በአሞሌ ያጠበ፣ አካሉ ሁሉ በሴራ የተመረዘ እንደሆነ የሚገልጹ” ኢትዮጵያ የራባት ሰላም እንዴት እውን ይሆንላታል” ሲሉ አዘኔታቸውን ያስታውቃሉ።

በቅርቡ በመላው አገሪቱ የሰው ማዕበል በፈሰሰበት ሰልፍ ህዝብ በገሃድ ” ትህነግን እስከወዲያኛው አልፈልግም ብሏል።ጠልቶት መትፋቱን አሳይቷል፤ ሰለቸን ታስወጉን፣ አትውጉን፣ እንኑርበት ብሏል። እዛና እዚህ እያጣቀሱ ሁለት ቢላ ለሚጠቀሙም እንደታከተው አስታውቋል፤ ትህነግም ሆነ ደጋፊዎቹ ይህን ሁሉ እያዩ ተስፋ አለመቁረጣቸው በርካቶችን የሚያስገርም ጉዳይ ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን “ተተኪው ይመራዋል” ሲሉ ለተተኪውም ሌላ የሞት ውርስ፣ የጥላቻ ፖለቲካ እያወረሱት መሆኑ ነው። ለዚህ ነው ትግራይም ሌላው ህዝብም ማረፍ አለበት የሚሉ ድምጾች የበዙት። “ትግራይም አረፈች እኛም አረፍን” የመጨረሻው መፍትሄ!!

Exit mobile version