Site icon ETHIO12.COM

” የትግራይ ሕዝብ በራሱ ልጆች እንጂ በማንም ሊተዳደር አይገባም” መንግሥት

ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

የትግራይ ሕዝብ ሕወሐት ከጫነበት ቀንበር ነጻ እንዲሆን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መሥዋዕትነት እየከፈለ ነው የመከላከያ ሰራዊቱ መሥዋዕትነት የታሰበውን ግብ እንዲያሳካ የትግራይ ሕዝብ የማይተካ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

የመከላከያ ሠራዊቱን በመንከባከብ፣ ስንቅ በማቀበል፣ ስለተደበቁ ጀሌዎችና የጦር መሣሪያዎች መረጃ በመስጠት፣ መንገድ በመምራት እና አካባቢውን በመጠበቅ የትግራይ ሕዝብ ከሠራዊቱ ጋር ተሰልፏል።

ለዚህም መንግሥት ምስጋናውን ያቀርባል። የትግራይ ሕዝብ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር ያለው ቅንጅት ሕወሐትን አስደንግጦታል።

በዚህም የተነሣ “ምስለኔዎች ሊያስተዳድሩህ እየመጡ ነው” የሚል ውዥንብር እየነዛ ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሕወሓት ጋር የታገለው የምስለኔ አስተዳደር እንዲቀር ነው። የምስለኔ አስተዳደርን በክልሎች ላይ እንደገና የዘረጋው ሕወሐት በመሆኑ። የትግራይ ሕዝብ በራሱ ልጆች እንጂ በማንም ሊተዳደር አይገባም።ፌዴራላዊ ሥርዓቱም ይሄንን አይፈቅድም። ሕወሐትም ይሄንን ያውቃል። ይደብቃል እንጂ።

በመሆኑም የትግራይ ሕዝብ የሕወሐትን የምስለኔ ቴአትር፣ በምስለኔነት ለኖረው ለሕወሐት ትቶ፣ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር የጀመረውን ትብብር እንዲያጠናክር መንግሥት ጥሪውን ያቀርባል።

ጥቅምት 20 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Exit mobile version