ETHIO12.COM

እመኑ – ኢትዮጵያ ዛሬ አረፈች! የሴራው ዋርካ ተገነደሰ

የሰላም ንግግር እንደሚደረግ እንደተሰማ ” ስምምነት ላይ ከተደረሰ ኢትዮጵያ ታርፋለች፣ በርካታ መልካም አጋጣሚዎች ይሆኑላታል” የሚል ዜና ጎን ለጎን ተሰማ። የሰላም ስምምነቱ በሚፈለገው መልኩ እውን ከሆነ ትህነግ በብር፣ በትጥቅ፣ በስልጠና፣ በሎጂስቲክ፣ በሴራ፣ በፕሮፓጋንዳና በክህደት የፈለፈላቸው ድርጅቶች፣ ግለሰቦች፣ ተላላኪዎች፣ ሚዲያዎች፣ በቀቀኖች፣ ተሳዳቢዎች፣ ነጮቹን ተከፋዮች ጨምሮ ይነጥፋሉ ነበር ትንቢቱ። ዛሬ እነዚህ ሁሉ ከሰሙ። ወዲያው ኮማ ውስጥ ገብተው የቁም ሞት የሞቱም አሉ።

የዛሬው የስምምነት አሳብ ቀድሞ የገባቸው ተከፋዮች 360 ዲግሪ እየተወራጩ ሲሳደቡ፣ ሲያቅራሩ፣ የመቀመጫቸው ቋጠሮ እስክበጠስ ሲጮሁ ነበር። ማንም ምንም ቢል “አገር ሻጭ” እየተባሉት፣ ኢትዮጵያን ከፋፋይ፣ግድቡን የሸጡ” በሚል ስድብ የሚወርድባቸው አብይ አሕመድ የበቀቀኖቹን ላንቃ ዘግተውታል። መጨረሻውን የምያውቁት አብይ አህመድ አዲስ አመት ላይ ሰላም እንደሚመጣ ሲናገሩ ” ለኢትዮጵያ በሚተቅም መልኩ” ነበር ያሉት። ሆኗል። ካሉትም ያጉደሉት የለም። ስንዴና አኩሪ አተር በገፍ እንዲመረት ትክረት በመስተታቸው፣ የህጻናት መቦረቂያ በማስገንባታቸው፣ ኢትዮጵያ ልይ የተደረተው የጎሳ ፖለቲካ ቆዳ የሚገፈፍበት የሳይንስ ማዕከል በማስገንባታቸው … የስድብ ናዳ የሚወርድባቸው አብይ ” ክብር ለአምላካችን” ሲሉ ነው የሰላሙን ታላቅ ዜና በምስጋና ያወደሱት።

አስኪ ይህን አስቡት – ጌታቸው ሽፈራው እንዳለውንግግሩ ከዓመት በፊት ሆኖ ቢሆን ብለን እንጠይቅ

ላለፉት ሶስት ዓመታት አካባቢ ቁጭ ብለው ነገር ሲጠምቁ፣ ሽብር ሲረጩ፣ በሃሰተኛ ወሬ ሕዝብን ሲያሸንሩ የነበሩ፣ ልጆቻቸው ፊት፣ ትዳራቸው ውስጥ፣ ባልደረቦችና ወገኖቻቸው እያዩ በደም ሲነገዱ የነበሩ ተከፋይ ቁማርተኞች ከአሁን በሁዋላ ስራ ፈት ሆኑ። በሚከፈላቸው መጠንና ዲያስፖራውን እያዋከቡ ሲያልቡ የነበሩ ዲጂታል ለማኞች ጉሮሯቸው ተቀረቀረ። ኢትዮጵያ እንደ አገር አሸነፈች። ትግራይ አማራና አፋር ተነፈሱ። የሰላም ዜና መሰማቱ በሕዝብ ዘንድ ሃሴትን ፈጠረ። ውድመትን፣ መከራን፣ ስቃይንና ስደት ለተፈራረቀባችሁ፣ የአብራኮቻችሁን ክፋይ ለተነጠቃችሁ፣ ግፍና በደል ለተፈጸመባችሁ ሁሉ ይህ ቀን ታላቅ ነው።

ኢትዮጵያ ላይ ሲዛበቱ፣ ሕዝቧን የመከራ ማቅ ሲያለብሱ የነበሩ ሁሉ በሰላም ስምምነቱ እረፍት ቢያጡም፣ ቢከፋቸውም ህዝብ ክፉውን ረስቶ ወደፊት በሰላም ለመጓዝ ዛሬ መንገድ ጅምሯልና አልቃሾች ደረታቸውን ቢመቱም የሚቀየር ነገር እንደማይኖር ከብሽሽቅ ስሜት የራቁ እየገለጹ ነው።

ልክ የኢትዮጵያ ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት በታረደበት ቀን የተበሰረው የኢትዮጵያ ልጆች የደም ዋጋ ካሁን በሁዋላ ማንም እንዳይነግድበት ሰላሙን ለማጽናት በቀናነት፣ ከተራ የድል አድራጊነት ስሜት፣ ከብሽሽቅና ጥላቻ ራስን በማቀብ መንቀሳቀስ ግድ እንደሆነ የሚያመለክቱ፣ ሰላም ይፋ በሆነ ሰዓታት ውስጥ አዲስ አበባ ተቀምጠው መርዝ መርጨት የጀመሩ የሚድያ ባለሙያ ነን ባዮች ላይ መንግስት የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ፣ አስቸኳይ ህግ በማውጣት ጭምር ገደብ እንዲጥል መክረዋል። እነዚህ ክፍሎች እንደሚሉት ካሁን በሁዋላ በተቀላቢና ተላላኪ ሚዲያዎች ኢትዮጵያ የመትሰክርበት፣ ህዝብም የሚሰቃይበት አንዳችም ምክንያት ሊኖር አይችልም።

በዚህ ሚዲያ የሰላም አማራጭ ንግግሩ ከመጀመሩ ሳምንታት በፊት ትህነግ ትጥቅ ለመፍታት መስማማቱን ተጽፎ ነበር። አሜሪካንም “ከዚህ በላይ ጫና ለማድረግ አንችልም” ሲሉ ትህነጎች ትጥቅ እንዲፈቱ ቀጭን ትእዛዝ ማስተላለፏ ተጠቅሶ እንደነበር ይታወሳል። የትህነግ መሪ ዶክተር ደብረጽዮንም ” ትግሉን ተተኪው ይመራዋል” ሲሉ ነገሩ ቀድሞ ማለቁን አመልክተው ነበር። አቶ ስዬ አብርሃም ” ከንግግሩ ምንም አንጠብቅም” ሲሉ የትግራይን ወጣቶች ለሽምቅ ውጊያ ወገባችሁን አጥብቁ የሚል ጥሪ አሰምተው ነበር። የዓለም የጤና ድርጅት መሪ ቴዎድሮስ አድሃኖምም “የዲፕሎማሲ ቃላቶች አለቁብኝ” በሚል ማልቀሳቸው የተስፋ መቁረጥ ምልክት እንደሆነ ተመልክቶ ነበር። አብይ አህመድ በበክላቸው የስንዴ ነዶ ውስጥ ቆመው በኮምባይነር ውቂያ ሲያካሂዱና ማሽን እርሻ ሜዳ ላይ ሲያርመሰምሱ ነገሩ እንዳበቃ ግምት ነበር።

ሁሉም ሆኖ ጉዳዩ ጫናውን ሁሉ በደረማመሰቸው ኢትዮጵያ ምድር ሰላም እንዲሰፍን ህጋዊ ውል ተዘጋጅቶ ይፋ ሆኖ ተጠቃሏል። በዋናነት ስምምነት የተደረሰባቸው ነጥቦች እነዚህን ይመስላሉ። ከስምምነቶቹ መካከል ትህነግ ኢትዮጵያን በሚነኩና በብሄራዊ ጥቅሟ ላይ ከሚነሱ ማናቸው አካላት ጋር ግንኙነትም ሆነ ንክኪ አይኖረውም። በአገር ቤትም ከማናቸውም ሃይላት ጋር ድጋፍና ህብረት አይፈጥርም። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ላይ በነጻ አውጪ ስም ከፍለፈላቸው ድርጅቶች ጋር በይፋ ውሉን እንዲቀድ ተደርጓል። ትህነግ የፈታው ትልቁ ትጥቅ ይህ ነው።

  1. ህወሓት ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ለመፍታት መስማማቱን፦ በስምምነቱ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንደሚፈታ፤ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በ24 ሰዓት ውስጥ አመቺ ቦታ መርጠው ንግግር ያደርጋሉ፤
  2. ስምምነቱ በተፈረመ አምስት ቀናት ውስጥ የሁለቱ ወገን ወታደራዊ አመራሮች የትጥቅ ማስፈታት ሂደቱ የሚመራበትን ዝርዝር አፈጻጻም በጋራ በማውጣት ተግባራዊ ሥራዎችን መሥራት ይጀምራሉ፤
  3. የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በተገናኙ አስር ቀናት ውስጥ ህወሓት ያሉትን ሁሉንም የቡድን እና ከባድ መሣሪያዎች ለመከላከያ ሠራዊት ያስረክባል፤
  4. ስምምነቱ በተፈረመ ሰባት ቀናት ውስጥ የፌደራል መንግሥት መቀሌን ተረክቦ በከተማው ውስጥ እና ዙሪያ ሁሉንም አይነት የጦር መሣሪያ ያስፈታል፤
  5. በአጭር ቀናት ውስጥ አሁን ያለው የህወሓት መዋቅር ፈርሶ የፌደራል መንግሥት የሚመራው የጊዜያዊ አስተዳደር ይቋቋማል። በሚዋቀረው ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥም የትግራይን ሕዝብ የሚወክል አካል ይሳተፋል፤
  6. የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከጎረቤት ሀገራት የሚያዋስኑ የድንበር አካባቢዎችን ደኅንነትና ሰላም የሚያረጋግጥ ስምሪት የሚያደርግ ይሆናል። መከላከያ ሠራዊቱ በማንኛውም የትግራይ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ ሕግ የማስከበር ስልጣኑን ከህወሓት ሙሉ በሙሉ ይቀበላል። ህወሓት ለተግበራዊነቱ ምንም አይነት እንቅፋት እንደማይፈጥር ተስማምቷል።
  7. የሚመሰረተው ጊዜያዊ አስተዳደር በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች የማኅበራዊ አገልግሎቶች በፍጥነት እንዲጀመሩ ሁኔታዎች ያመቻቻል፤ ተግባራዊነታቸውን ያረጋግጣል፤
  8. ህወሓት ያለ ፌደራል መንግሥት እውቅና ከማንኛውም የውጭ አካል ጋር ግንኙነት ማድረግ ያቆማል።

ምንም ተባለ ምን አሁን የሴራው ዋርካ ተገንድሷል። የሴራው ዋርካ ደርቋል። ስሩን መከላከያ በጣጥሶ ጥሎታል። አሁን በድን ሆኗል። በነጻ አውጪ ስም ሲነዳ የነበረው የቅማንት ሽፍታ “በቃኝ” ብሏል። በሰላም ገብቷል። የቤኒሻንጉሉ ተቀላቢ “በቃኝ” ብሎ ለሰልም እጁን ከሰጠ ሁለት ሳምንቱ ነው። ደሞዝና ሎጂስቲክ የቆመበት ሸኔም የዕርቅ ያለህ እያለ ነው። ትህነግንም ከዳኽኝ ብሎ እየረገመ ነው። ብታምኑም ባታምኑም ኢትዮጵያ ድናለች። ዛሬ መከላከያ በተከዳበት ቀን ጸሃይ ወጣ። አምላክ ይፈርዳል።

Exit mobile version