ETHIO12.COM

የትጥቅ ማስፈታቱ ሂደት በይፋ ተጀመረ፣ ክልሉም ስምምነቱን መቀበሉን ይፋ አደረገ

ይፋ በሆነው የፕሪቶርያ ስምምነት መሰረት የትጥቅ ማስፈታቱ ስራ መጀመሩ ታወቀ። በቅርቡ የሽግግር አስተዳደር የሚቋቋምለት የትግራይ ክልል ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤትም ስምምነቱን መቀበሉን በይፋ አረጋግጦ መግለጫ አሰርራጨ።

“… ይህ ስምምነት በተፈረም በሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ የሁለቱ ወገኖች ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተገናኝተው ይነጋገራሉ” በሚለው ግልጽና በፊርማ የጸደቀ ውል መሰረት የኢፌድሪ ጠቅላይ ኢታማዦር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላና የትህነግ ማዕከላዊ ኮማንድ ፖስት አዛዥ የሚባሉት የቀድሞ ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ በዛሬው ዕለት ተገናኝተው መናገራቸውን ኢ ኤም ኤስ የተሰኘው የእነ ሲሳይ አጌና ሚዲያ ቀድሞ ቢገልጽም የኢትዮ 12 የአዲስ አበባ ዘጋቢ የዜናውን ትክክለኛነት ማረጋገጡን ገልጿል። የትህነግ ጦር ሌላ አዛዥ የሆኑት ባለሃብቱ ሌተናል ጄነራል ጻድቃንና ሌሎች የትህነግ ሰዎች በንግግሩ አዲስ አበባ ሆነው ተሳትፈዋል።

ይህ የሆነው እነ ዘ- ጸዓትን ጨመሮ በርካቶች የሰላም ስምምነቱ በተገለጸው መሰረት መፈረሙ ” ክህደት ነው” በሚል በስፋት እየገለጹ ባለበት ወቅት ነው። በግልጽ ቋንቋ የትህነግ ደጋፊዎች ሳይቀሩ የስምምነቱን ይዘት ሳይወዱ አምነው በተቀበሉበት ወቅት ስምምነቱን ከግል ስሜትና ፍላጎት፣ እንዲሁም “ለምን ስልጣን አልያዝኩም” ከሚል ቁጣና ቂም በመነሳት እያጣመሙ ለማቅረብ የሚሞክሩ ቢኖሩም ተግባራዊነቱ በተያዘለት ዕቅድ መሰረት እሳክሁን ሳይዛነፍ እየተከናወነ መሆኑንን መረጃዎች ሊካድና ሊሸፋፈን በማይቻልበት ሁኔታ እያረጋገጡ ነው።


የፕሪቶሪያው ስምምነት ትርጉም በ360 ደርዝ ለዞረባችሁ

… አቅም አልባ ከሆንክ ማንም የማይፈልግህ ውዳቂ ትሆናለህ። የራስህን አቅም በሚገባ ከገመገምክ በኋላ ማን ነው አጋሬ ወደሚለው ትዞራለህ። አጋርህ ከጠላትህ እና ከአንተ ጋር ያለውን መስተጋብር ትገመግማለህ። አጋርህ ከጠላትህ ይልቅ አንተን ለምን እንደመረጠ አንተም ለምን እንደመረጥከው …


” ትህነግ ትጥቅ አይፈታም፣ የትጥቅ መፍታቱ ሂደትም ብዙ ጊዜ የሚፈጅ ነው። ዝርዝር ስምምስነቱ ገና አልተፈረመም” በሚል ስለም ለጠማው ህዝብ ሌላ የጦርነት ድግስና የእልቂት ከበሮ እየመቱ ላሉት መልስ ይሆን ዘንዳ ቢቢሲ ዘግይቶም ቢሆን በዝርዝር አፈጻጸሙ ላይ ፊርማ መቅመጡን ሮይተርስ ጉዳዩን ሲያከናውኑ ከነበሩት እንዳረጋገጠ ዘግቧል።

ተጨማሪ ከድርድሩ በፊት የተዘገቡትን ያንብቡ

ራሱን የትግራይ መንግስት በሚል ስያሜ ሲጠራ የከረመርው ትህነግ ስሙንና መለያውን አስተካክሎ “ስምምነቱን ተቀብያለሁ” ሲል በገሃድ አስታውቋል። ይህም መግለጫ የስምምነቱ አካል እንደሆነ ታውቋል። ገና ተጨማሪ መግለጫዎችና የተግባር ውሳኔዎች እንደሚከታተሉ ስምምነቱን ጠቅሰው ያስታወቁ እንዳሉት ” በመሬት ላይ ያለውን እውነታ አለመቀበል፤ ተራ መወተርተር ካልሆነ የሚያመጣው ለውጥ የለም”

ትህነግ ለህግ፣ ለህገመንግስት መከበርና የበላይነት ሲል ወደ ጦርነት መግባቱን የደጋፊዎቹን ስሜት በሚጠብቁ ቃላቶች አዋዝቶ የተደረሰበትን ውሳኔ እንደሚቀበል ማስታወቁ

በተመሳሳይ መንግስትም የተቋረጡ አገልግሎቶችን ከማስጀመር አንስቶ በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ የማቋቋምና የማደስ፣ ሕዝብ በፍጥነት ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴው እንዲመለስ በውሉ ከተቀመጠው ባለፈ መንግስታዊ ሃላፊነቱን እንደሚወጣ፣ ሪፎርሙ በደንብ እንዳይካሄድ ማነቆ የሆኑትን ጉዳዮች በማስወገድ ሪፎርሙን ማጠናከር፣ ለሰላም ማበልጸግ ይረዳሉ የሚባሉ ጉዳዮችን ማከናወንና ድንበርን የመጠበቅ ሃላፊነቱን ይወጣል። ተረጂዎች በተሳካ ሁኔታ በቀጥታ እርዳታ እንዲደርሳቸው ይሰራል።

አሜሪካ “ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወይም ሞት” ስትል ድጋፏን ሰጠች

ስምምነቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለተገባራዊነቱ አስፈላጊውን ሁሉ መንግስታቸው እንደሚያከናውን፣ ይህንንም ከልብ እንደሚያደርገው መግለጻቸውን ተከትሎ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ” ከጎንዎት ነን” ሲል መግለጫ ማውታቱን የመንግስት ኮሙኒከሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያቤትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን እስትንፋስ ሁሉ የግንባር ዜናቸው የሚያደርጉት በኢትዮጵያዊያን የሚመሩ ሚዲያዎች ዜናውን ዝም ብለውታል። “በክህደትና በባንዳነት ታሪክ የዘገባቸው አብዛኞቹ የውጭ ሚዲያ ተቀጣሪዎች የተሰማሩበት የክህደት ዘመቻ በመንጠፉ ከገቡበት ኮማ እስከሚነቁ ይህ የሚጠበቅ ነው” ሲሉ አስተያየት የሰጡ አሉ።

ጫና ስታሳድር የነበረችው አሜሪካ ” ሁሉንም አድርጌ ሞክሪአያለሁ አልተሳካም። ህዝቡ አገሩን ይወዳል። ከዚህ በላይ ጫና ማድረግ አንችልም” ስትል ድርድሩ ከመጀመሩ በፊት ለትህነግ ሰዎች መንገሯን ኢትዮ12 መዘገቧ ይታወሳል።


አሜሪካ “ሕዝቡ አገርኑ ይወዳል ከዚህ በላይ ጫና ማድረግ አንችልም”፤ ትህነግ ተስማምቶ ተነጋጋሪ ሰየመ

ባለቀ ሰዓት አሜሪካ ” ሕዝቡ አገሩን ይወዳል” ስትል ሞክራ ሞክራ፣ ሁሉንም ድንጋይ ፈንቅላ እንዳልሆነ ገሃድ አስታውቃለች መባሉ ተሰምቷል። ሁሉም ተዳምሮ ምስኪኖች ጫንቃ ላይ የወደቀውን ሃዘን ማን ይጠበው?


Exit mobile version