Site icon ETHIO12.COM

የኳታር ዓለም ዋንጫ ያስተዋወቀው ጋኒም አል ሙፍታህ

ጋኒም አል-ሙፍታህ ይባላል፤ የ20 ዓመት ዕድሜ ያለው ይህ የኳታር ዜጋ፣ Caudal Regression Syndrome (CDS) በተባለ ችግር ምክንያት ከወገብ በታች አካል የለውም።

እናቱ ከመወለዱ በፊት ልጇ ችግሩ እንዳለበት ተነግሯት በበርካቶች “ልጅሽን አስወርጂ” በሚል ብትመከርም፣ እናት ግን ጋኒምን ወልዳ ችግሩን አብራ መጋፈጥን መርጣለች።

ከአባቱ ጋር በመሆንም “ልጃችን ከወገቡ በታች አካል ባይኖረውም አንዳችን ቀኝ እግር፣ ሌላችን ግራ እግር እንሆንለታለን” ሲሉ ቃል በመግባት የዓለምን ፈተና አብረውት ለመታገል ቆረጡ።

የሚጋባ ፈገግታ የተቸረው ጋኒም በማኅበራዊ ሚዲያው ለሚሊዮኖች ንቃትን የሚፈጥር ወጣት ሆኗል። ቀድሞ በጓደኞቹ ማንጓጠጥ ሊያቋርጠው የነበረውን ትምህርት ቀጥሎም በፖለቲካል ሳይንስ ዲግሪውን ለማግኘት እየተማረ ይገኛል። ዛሬ ደግሞ የ2022ቱ የኳታር የዓለም ዋንጫ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ድምቀት ሆኖ አሳልፏል።

(EBC)

Exit mobile version