Site icon ETHIO12.COM

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ታሰሩ

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ በቀለን ጨምሮ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ዋሉ


የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ በቀለን ጨምሮ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፍትህ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተናገሩ።

ይህ የተገለፀው በቅርቡ የተቋቋመው የፀረ ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ ስራውን በይፋ መጀመሩን አስመልክቶ የኮሚቴው አባላት ዛሬ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።

በአዲስ አበባም የአርሶ አደር ልጆች ወይም የልማት ተነሽ ሳይሆኑ የሆኑ በማስመሰል በሐሰት ሙስና የሰሩ ግለሰቦችም ተለይተዋል ብለዋል የብሔራዊ ኮሚቴው አባል ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ።

175 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታና የኮንዶሚኒየም ቤት ምዝበራ የፈፀሙ እንዲሁም በፍትህ ዘርፉ ስልጣናቸውን በመጠቀም ከግለሰቦችና ከንግድ ተቋማት ጋር ለግል ጥቅማቸው ሲሰሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎችም ተለይተዋል ተብሏል።

ኮሚቴው ሶስት ንዑስ ኮሚቴዎችን ማለትም የህግ፣ የመረጃ እና የፋይናንስ ንዑስ ኮሚቴዎችን በማቋቋም እቅድ አውጥቶ ስራ መጀመሩንም የብሔራዊ ኮሚቴው ሰብሳቢና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተናግረዋል።

በመንግሥት አግልሎት አሰጣጥ፣ በፋይናንስና ግዥ፣ በፍትህ ስርዓቱ እና በመሬት አስተዳደር እንዲሁም በመሰረታዊ ፍጆታ አቅርቦት ዘርፎች ላይ ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ ይስተዋላል ብለዋል።

የሌባ ትንሽ የለውም ያሉት አቶ ተመስገን ጥሩነህ፤ ከመታወቂያ አሰጣጥ ጀምሮ ህብረተሰቡን የሚያማርሩት ላይ ጠንካራ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

በንብረቴ ተሆነ EBC

Exit mobile version