Site icon ETHIO12.COM

በኦሮሚያ ጥቃትና ግጭት መጨመሩን ኢሰመኮ ገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ ባወጣው ሪፖርት በኦሮሚያ ክልል ከዚህ ቀደም ጥቃትና ግጭት የተከሰተባቸውን እና እየተከሰተባየው ያሉ 36 ወረዳዎች መመዝገቡን ገልጿል።

ኢሰመኮ ከሐምሌ ወር 2014 ዓ.ም እስከ ኅዳር ወር 2015 ዓ.ም ድረስ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶችና ጥቃቶች መቀጠላቸውን በሪፖርቱ አስታውቋል።
ኢሰመኮ “በአካል ተገኝቶ ምርመራ ለማካሄድ ባልቻለባቸው አካባቢዎች ደግሞ ተጎጂዎችን፣ የተጎጂ ቤተሰቦችን፣ ከእነዚህ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን፣ የዐይን እማኞችንና የመንግሥት ኃላፊዎችን ጨምሮ የተለያዩ ምንጮችን በማነጋገር የቃል እና የጽሑፍ መረጃና ማስረጃዎችን” እንደሰበሰበ አስታውቋል።

በኦሮሚያ ክልል እስካሁን 13 ዞኖች ውስጥ ባሉ 36 ወረዳዎች ላይ ግጭቶች ተከስተው በሰውና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል ብሏል ኢሰመኮ፡፡

በተለይም በሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ በምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ በሰሜን ሸዋ፣ በቄለም ወለጋ ዞን፣ ኢሉ አባቦራ ዞን፣ በቡኖ በደሌ ዞን፣ በምሥራቅ ሸዋ፣ በምዕራብ ሸዋ፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ በአርሲ ዞን እና በሁለቱ የጉጂ ዞኖች ውስጥ ግጭቶች ተከስተዋል ብሏል፡፡

ኢሰመኮ ግጭት ከተከሰተባቸው ወረዳዎች መካከልም በኪረሙ፣ ጊዳ አያና፣ አልጌ፣ ሁሩሙ፣ በአሙሩ፣ ሆሮ ቡሉቅ፣ ጃርደጋ ጃርቴ፣ ቦሰት፣ ግንደበረት፣ ጮቢ፣ ደራ፣ ኩዩ፣ መርቲ ጀጁ እና የአርሲ ዞን አጎራባች ወረዳዎችን የሚደርሱ ግጭቶችና ጥቃቶችን በመከታተል ላይ እንደሚገኝ ጠቅሷል፡፡

ኢሰመኮ ግጭቶቹና ጥቃቶቹ የሚከሰቱባቸው አካባቢዎች ስፋት ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩን እና የሚያስከትሉት  የሰብአዊ መብቶች ቀውስ ደረጃ አስከፊነት ነው ብሏል፡፡
በእነዚህ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖች በአይነታቸውና በቁጥራቸው የመጨመር ወይም የመወሳሰብ አዝማምያ ማሳየታቸውም ኢሰመኮ በሪፖርቱ አስታውቋል።

በተለያዩ ወቅቶች የተለያዩ ቡድኖች ሙሉ ቀበሌዎችን ወይም ወረዳዎችን ጭምር ተቆጣጥረው የቆዩ መሆናቸው የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶቹን አባብሶታልም ብሏል ኢሰመኮ።

እንዲሁም መንግስት ተመጣጣኝና የተጎዱ ሰዎችን ብዛትና አካባቢዎችንም የሚመጥን ምርመራ ማድረግ እንዳልቻለ አስታውቋል።

ኢሰመኮ ባወጣው ሪፖርት  የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች፣ ራሳቸውን ለመከላከል የታጠቁ የአካባው ኃይሎች፣ በአካባቢው በተለምዶ የአማራ ታጣቂዎች ናቸው የሚባሉት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊ( ሸኔ) እንደሚንቀሳቀሱ ገልጿል።

ኢሰመኮ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና ታጣቂ ቡድኖቹ እርስበእርሳቸው በሚያደርጉት ውጊና እና በሌላ ወቅት በጠናጠል በሚያደርሱት ጥቃት በርካታ ንጹሃን ለሞት፣ ለመፈናቀል እና ለንብረት ውድመት ተዳርገዋል ብሏል፡፡

ከሰሞኑ በምስራቅ ወለጋ በተለያዩ አካባዎች በተፈጸመ ጥቃት በርካታ ሰዎች ሲገደሉ፣ በርካቶች መገናቀላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
ALain

Exit mobile version