Site icon ETHIO12.COM

የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና መመስረቻ ስምምነት የአማርኛ ቋንቋ ትርጉም ይፋ ሆነ

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና መመስረቻ ስምምነት የአማርኛ ቋንቋ ትርጉም ይፋ ሆነ።

ስምምነቱ በብዙ ቋንቋቸው መተርጎሙ ሁሉንም አገራት የንግድ ተዋናይ ለማድረግ ያስችላል ተብሏል።

በኢትዮጵያም ሁሉም የንግድ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ስለስምምነቱ እና የነፃ ንግድ ቀጣና ፋይዳ በቅጡ እንዲረዱ ያደርጋል ተብሏል።

ነፃ የንግድ ቀጣና ስኬታማ እንዲሆን የኢትዮጵያ መንግስትና የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን የመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙ ባለድርሻ አካላት ገልፀዋል።

የተቀላጠፈ የአፍሪካ አገራት ቀጣናዊ ንግድ በማደረግ ልማትን ለማረጋገጥ ያስችላል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የነፃ ንግድ ቀጣና ከፍል ኃላፊ አቶ ይታገስ ሙሉጌታ፣ ኢትዮጵያ ለስምምነቱ ትግበራ ቁርጠኛ መሆኗን ገልፀዋል።

የፓን አፍሪካዊነት እና አፍሪካ አህጉራዊ ትስስርን በማጎልበት መንፈስ የተጠነሰሰው ስምምነቱ፣ ለአጀንዳ 2063 የልማት ግቦች መሳካት ወሳኝ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት መልከ ብዙ የኢኮኖሚ ሪፎርም እያደረገ መሆኑን ገልፀው፤ ቀጣናዊ የንግድ ትስስርን መፍጠር አንዱ ቁልፍ ጉዳይ ነው ብለዋል።

ተገማች ገበያ ማመቻቸት የኢትዮጵያንም በዘርፉ ተጠቃሚና ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለመሳብ አይተነኛ አሰተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልፀዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ የነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነቱ በአማርኛ ቋንቋ ተተርጉሞ መቅረቡ፤ የግሉ ዘርፍ የንግድ ዝርዝር ግንዛቤ እንዲኖረው በማድረግ ወደ ተግባር እንዲገባና ተጠቃሚነቱንም እንዲያረጋገጥ ያስችላል።

ENA

Exit mobile version