Site icon ETHIO12.COM

“አጨዳ የጀመረው መከላከያችን ዳግም እንዳይታጨድ” ጥሪ እየቀረበ ነው

በትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ ወኪሎችና በመንግስት መካከል የተደረሰው የሰላም አማራጭ ስምምነት እጅግ ያስደሰታቸው ወገኖች ስጋታቸውን መግለጽ ጀምረዋል። ስጋቱም የመነጨው ትህነግ አንዳንድ ወታደራዊ የስምሪት ለውጥ ማድረጉንና ምሽግ ቁፋሮ ላይ መጠመዱን የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ በመሆኑ ነው። “ሰራዊታችን አገር አማን ብሎ ዳግም እንዳይታጨድ” ሲሉ ማሳሰቢያቸውን የሰጡት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ናቸው።

ትህነግ የመከላከያ ሰራዊትን በክህደት ማረዱን በገሃድ በኩራት መንፈስ ማስታወቁን የሚያስታውሱ፣ አሁንም ያ ክህደት እንዳይፈጸም ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የሚያመላክቱ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን ነው ጥሪ አራቢዎቹ የሚናገሩት።

ሰላም ለመላው ኢትዮጵያ አስፈላጊና አንገብጋቢ ጥያቄ መሆኑ፣ አሁን የተጀመረው የሰላም አካሄድ እጅግ ሊበረታታ እንደሚገባው ያመልከቱት ክፍሎች ” እንደ ልብ የዋህ፣ እንደ እባብ ልባም መሆን ግን ግድ ነው” ይላሉ።

በትግራይ ሰማኒያ አምስት ከመቶ የሚሆነውን ክፍል የተቆጣጠረው የመከላከያ ሰራዊት አሁን ላይ የደረሱ ምርቶችን እየሰብሰበ፣ አርሶ አደሮችን እየረዳ መሆኑንን መስማት እጅግ ደስ የሚያሰኝ የበጎ ስራ ሁሉ ምሳሌ እንደሆነ በማውሳት ” ትህነግ በባህሪው ክፋትን በየቀኑ የሚጸንስ፣ የሚያዋልድና የሚያከፋፍሉ ቡድን በመሆኑ ከቀናናት ብዛት መዘናጋት አይገባም” ሲሉ የሚያሳቡ ወገኖች ” ትህነግ በመከላከያ ሰራዊት ዱላ በመወላለቁ ትንፋሽ ለመውሰደና የፈረሰውን ሃይሉን ዳግም ለማደራጀት፣ ስንቅና ነዳጅ ለማከማቸት፣ መሳሪያ ለመጠገን፣ በጎንም የቻለውን ያህል ለማሰባሰብ የሰላም ስምምነቱን ተቀብሏል” ብለው እንደሚያምኑ ያስታውቃሉ።

ትንፋሽ ከወሰደ በሁዋላ ሳያቅማማ የፈረመውን ሁሉ ተግባራዊ ለማድረግ የሚዳዳው አሁንም “ሲጠግብ” አጎራባች ክልሎችን እንደለመደው ለማፈራረስ ካለው መሰሪ የቅናትና አውዳሚ ተፈጥሮው የተነሳ በመሆኑ መንግስት ከትህነግ ተፈትሮ በመነሳት ሁሉንም ተግባሩን እንዲመረምር አስታውቀዋል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ዳግም ” መከላከያ በክህደት ታረደ የሚል ዜና መንግስትና ህዝብን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያለያያል” ሲሉ ያስታወቁት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ናቸው። እነዚሁ ወገኖች የሳፉትና ለዝግጅት ክፍሉ የላኩት የግል ደብዳቤ ጠንካራ ቃላቶችንና ማስተንቀቂያዎችን ያካተቱ በመሆናቸው ለጊዘው ከማተም ተቆጥበናል። በደብዳቤው ስለሰላም አስፈላጊነትና፣ ሰላምን ለማስፈን መከፈል ስላለበት ዋጋ በስፋት ተመልክቷል።

Exit mobile version