Site icon ETHIO12.COM

የአለማችን አስደንጋጩ ስፍራ
“ቤርሙዳን”

《ቤርሙዳትሪያንግል》በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ከአሜሪካ ፍሎሪዳ ግዛት ዝቅ ብሎ
የሚገኝ ስፍራ ነው ።

ቤርሙዳ ትሪያንግልን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየው ክርስቶፈር ኮለምበስ ሲሆን
ዘመኑም 1449 አ.ም ነበር: :
ክርስቶፈር ይህ
ስፍራ ደርሶ አንድ ነገር ተመለከተና በማስታወሻው ፃፈ: : ይህንን ያየውን ነገር ሲያሰፍር እንዲህ በማለት ነበር:
“በአድማስ ላይ የሚደንስ እንግዳ የሆነ የብርሀን ጮራ”
“በሰማይ ላይ የነገሰ የእሳት ነበልባል”
“የአቅጣጫ መጠቆሚያ ኮምፓስን የሚያመሰቃቅል ሀይል” ይለዋል: :

ይህ አነጋጋሪ ውሃማ ክልል በተለያዮ ጊዜዎች ባልታወቀ ሚስጥር በርካታ ቁጥር
ያላቸውን አውሮፕላኖች፣ መርከቦች፣ የጦር ጀቶች የሰውን ልጅ ህይወትና ሀብት እንደያዙ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጠፍተዋል
ዱካቸውን አጥፍቶ ለአርጂ እንኳን ወሬው ሳይደረስ እስካሁን ሲያነጋግር የቆየ ሚስጥር ነው፡፡

ይህንንም ተከትሎ ተመራማሪዎች ለበርካታ ጊዜያት የጉዳዩን ምንነት
ሚስጥር ለመፍታት ሲታትሩ ቆይተው አሁን ላይ ፍንጭ አግኝተናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከጉም ወይም ደመና ስር ደግሞ በሰዓት 170 ማይል በከፍተኛ ፍጥነት የሚምዘገዘግ ንፋስ እንደሚፈልቅ ከሳተላይት
ከተገኘ መረጃ ለማወቅ መቻላቸውን ይናገራሉ ተመራማሪዎቹ ፡፡

ይህም 45 ጫማ ከፍታ ያለው ሰፊ የባህር ሞገድ የሚፈጥር በመሆኑ መርከቦችን የመገልበጥና አውሮፕላኖችን ደግሞ ወደ ውቂያኖሱ የመድፈቅ ከበቂ በላይ አቅም እንዳለው ነው ተመራማሪዎቹ ያረጋገጡት፡፡
በዚህም ምክንያት ታዲያ ተመራማሪዎቹ ይህን ግዙፍ ሀይል የሚያመነጨውን ደመና በግርድፉ ‹‹የአየር ቦንብ›› የሚል ስያሜ
አውጥተውለታል፡፡

Via Muktarovich

Exit mobile version