Site icon ETHIO12.COM

መንግስት መቀለ ገባ፤ ሰላም ያሰጋቸው በቅጽበት ተቃውሞ አሰሙ

ምስል - አቶ ታገሰ በትግራይ ክልል መስተዳድር ጽህፈት ቤት ከእምነት አባት ጋር ሲመክሩ

ዛሬ ማለዳ ላይ በሰበር የተሰማው ዜና መንግስት ባለስልጣናቱን መቀለ መላኩ ነው። ይህ ታላቅ ዜና ሰላም የተጠሙትን ሁሉ ያስተነፈሰ ዜና ቢሆንም ቅድሚያ ወስደው ያወገዙት ” የተከበሩ” የሚባሉትና ብዙ ጊዜ በኮድ የታሰሩ መረጃዎችን ያለመከሰስ መብታቸውን በመጠቀም እንደሚያሰራጩ የሚነገርባቸው አቶ ክርስቲያን ታደለ ናቸው።

ዜናው የተሰማው በትናንትናው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከካቢኔያቸውና ከከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች ጋር በሰላም ስምምነቱ አተገአበር ዙሪያ ግምገማ ማካሄዳቸውን አመልክተው ለሰላሙ ቁርጠኛ መሆናቸውን ካስታወቁ በሁዋላ ነው።

የልኡካን ቡድኑ ወደ መቀሌ ያቀናው የሰላም ስምምነቱን የትግበራ ሂደት ለመቃኘትና በስምምነቱ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች በታቀደው መሠረት እንዲፈጸሙ ለማድረግ እንደሆነ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አስታውቋል። የመንግስት ከፍተኛ ሃላፊዎች ከሁለት ዓመት በሁዋላ በይፋ ትግራይን ሲረግጡ የመጀመሪያ ነው። የክልሉ ቲቪ በዩቲዩብ አውዱ ያሳየው የአቀባበል ስነስርዓት ልብ የሚነካና ህዝብ የሰላም ጥማት እንዳለው ያሳየ ነው።

አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በፍጹም ትህትና ጎንበስ እያሉ ለሚቀበሏቸው ሁሉ በመሪነት ያሳዩት ትህትና ሰላም ለናፈቃቸው ሁሉ የልብን ምት የሚጨምር ሆኖ ታይቷል። አቶ ጌታቸው ረዳም ቢሆኑ የተሰማቸውን ደስታ መደበቅ በማይችሉበት ሁኔታ እንኳን ደህና መጣችሁ ሲሉ ታይቷል።

በአጀብ የወጣውና አቀባበሉን እጅግ የሚፈለግ እንደሆነ ያሳየው በሁሉም ፊት ይነበብ የነበረው ደስታ ነው። ሁለት ወንድማማቾች ህዝብን በማይረባና ” ካልበላሁት ጭሬ ልበትነው” በሚል ትዕቢት ያጫረሰው፣ በተለይም ትግራይ ጨለማ ያወረሰው ጦርነት መጠናቀቁን የሚያመላክተው የመንግስት ባለስልጣናት ጉዞ የማያስደስታቸው ቢኖሩ በባዶ “የኢትዮጵያዊነት” መፈክር ስር ልዩ ተልዕኮ ያላቸው ተከፋዮችና ተላላኪዎች ብቻ ናቸው።

ወገን የሆነው የትግራይ ሕዝብ፣ አጎራባችና አብሮ የኖረው የአማራና አፋር ህዝብ ሰላም ይሻሉ። ኢትዮጵያ ሰላም ተርባለች። ከትህነግ ጋር ሰላም አውርዶ ወደ ዋናው የድህነት ላይ ዘመቻ መመለስ ለኢትዮጵያ ቁልፍ ጉዳይ ነው። ዛሬ ገና በማለዳው ህዝብን ያስደሰተና የሰላም ተስፋውን ያሳደገ እርምጃ ሲወሰድ ዘሎ ለመዘናጠል መፍጠን ማንም ዜጋ አይቀበለውም።

የልኡካን ቡድኑ ከሁለት ዓመት በኋላ ወደ መቀሌ የተጓዘ የመጀመሪያው የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልኡክ ሲሆን ስምምነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማሳያ መሆኑ ታምኖበታል። በልዑካን ቡድኑ የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላትም መካተታቸወን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሲገልጽ፣ መቀለ የደረሱትን የቴሌኮምና የኢንደስትሪው ዘርፍ ባለስልጣናት በቡድኑ ውስጥ መካከተታቸው በትግራይ ኢንደስትሪዎች ወደ ስራ የሚመለሱበት፣ ህይወት ዳግም የሚለመልምምበትን አግባብ ለማፋጠን እንደሆነ ያመልክታል። የባንክና የኤሌክትሪክ ዘርፉ መሪዎችም መካተታቸው በተመሳሳይ ምልክቱ ያው ነው።

“መንግስታዊነት ሆይ ወዴት አለሽ?” ሲሉ በምጸት የጀመሩት አቶ ክርስቲያን ትህነግ አሸባሪ ድርጅት ስለተባለ ለምን መንግስት ባለስልጣናቱን ላከ በሚል ህግ የተንተራሱ መስለው የሰላም ስምምነቱን ቀዋሚ ለማድረግ የሚደረገውን ፈጣን እርምጃ ኮንነዋል።

“ሕወኃት አሸባሪ ድርጅት ተብሎ የተፈረጀው በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ነው። የሰላም ስምምነት ፊርማ እንደተጠበቀ ሆኖ በሕግ ሕወኃት አሁንም ድረስ አሸባሪነቱ ያልተሰረዘለት ቡድን ነው። አስፈፃሚው አካል በማናለብኝነት የሚሰራውን ሕጎችን የመጣስ በጎ ያልሆነ ልምምድ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የመቆጣጠር ሕዝባዊ ኃላፊነት አለበት። ለስነስርዓታዊ ጉዳዮችም ከሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት በላይ ማን ሊጨነቅ ይችላል?” ሲሉ ሁለት ታላላቅ ጉዳዮችን አለባብሰው ያነሱት አቶ ክርስቲያን ማብራሪያ እንደሚጠየቁ ይጠበቃል።

“ትህነግ አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀ ድርጅት ነው። ስለዚህ አሸባሪነቱን ተሰብስበን እናንሳለት” የሚል ጥያቄ እያቀረቡ ይሁን ወይም፣ “የሰላም ስምምነቱ እንዳለ ሆኖ” ብለው አተገባበሩን የነቀፉበትን አግባብ አድበስብሰውታል።

በማህበራዊ ገጽ በስማቸው፣ በተለያዩ ግሩፕ አጃቢ ለማግበስበስ የታቦታት፣ የግለሰቦች፣ የድርጅት፣ … ጉዳይ እያነሱ ዲያቆን፣ ሰባኪ፣ የታሪክ ጠባቂ፣ ፖለቲከኛ፣ የሚናባበ ህጋዊ የተቃዋሚዎችና የሽብር ቡድኖችን ዓላማ የሚያራምድ … በተለይም ” ቤተመንግስት ግባ፣ በአንድ እጅህ …” እያሉ የውጭው ጽንፈኛ ቡድን አፍ ሆነው እየሰሩ ያሉት አቶ ክርስቲያን መንግስት ከልክ በላይ እንደታገሳቸው በስፋት እየተገለጸ ነው።

“እነዚህ መንግስታዊ ባሕሪያት ሁሉ ግን በብልጽግና መሩ የኢትዮጵያ መንግስት ዘንድ ከመጤፍ የሚቆጠሩ ሆነዋል። የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈጉባዔ የተከበሩ ታገሰ ጫፎ የመቀሌ ጉብኝት የመንግስትነት ወግ ብልሽት ዓይነተኛ ምሳሌ ሆኖ ለትውልድ አብነት ሊጠቀስ የሚችል ነው። መንግስታዊነት ሆይ ወዴት አለሽ? ከዚህ በኋላስ በምክርቤት ጉባዔዎች የስነስርዓት ጥያቄዎችን የማስከበር ሞራላዊ ቅቡልነት ይኖር ይሆን? ” ሲሉም የሚገናኘውን ከማይገናኘው አነካክተው ሂደቱን በመንቀፍ ጽፈዋል።

ሲቋጩም “ከደሙ ንጹህ ነኝ” ለማለት “ይኼ የስነስርዓት ጥያቄዬ የሰላም ስምምነቱን ከመቀበል እና አለመቀበል ጋር ግንኙነት የለውም” የለውም ሲሉ ለትችት እንዳይጋለጡ ካብ አበጅተዋል። ክርስቲያን ታደለ ጩኸታቸውን ባሰሙበት ገጻቸው ስር ” የመቀንጨር በሽታ ያቀጨጨው ክሪስ ለምን መቀሌ አልገባሁም ይመስላል ትችቱ” ሲሉ የለመጠጡዋቸው አሉ። “ገብሬዬ ጀግናችን” በሚል ጭብጨባ ያሰሙም አሉ። “ጦርነት ሰልችቶናል። ስለምን ጦርነትን አውግዘህ አትጽፍም” ሲሉ ” ሰላም ከሰፈነ ከዚህም በላይ ዋጋ ቢከፈል ድጋፍ እንጂ ተቃውሞ አንደማይገባ የገለጹ ጥቂት አይደሉም።

Exit mobile version