Site icon ETHIO12.COM

አምስት እጥፍ ከጸሓይ ልቆ መሞቅ የቻለው የቻይና “አርቲፊሻል”ፀሓይ

የቻይና ከተፈጥሮ ፀሃይ ፀኃይ አምስት እጥፍ መሞቅ የቻለ “ሰው ሰራሽ (አርቲፊሻል)”ፀኃይ መስራቷ ተስመቷል።

“EAST” የሚል መጠሪያ ያለው ‘ሰው ሰራሽ ፀኃይ ለኤሌክትሪክ ኃል ለማመንጨት ይችላል የተባለ ሲሆን፤ ይህ ፈጠራ ገደብ የሌለው ንጽሁ የተፈጠሮ የኃይል ምንጭ ለማግኘት የሚያስችል ነው ተብሏል።

እውነተኛውን ፀሃይ በማስመሰል የተሰራው የሰው ሰራሽ ፀሐዩ ሃይድሮጅን እና ዱተሪየም ጋዞችን እንደ ሀይል ማመኝጫ ነዳጅነት በመጠቀም ንጹህ ኢመርጂን ለማመንጨት ታስቦ ዲዛይን መደረጉ ታውቋል።

በዚህ መልኩ የተሰራው “EAST” የሚል መጠሪያ ያለው ‘ሰው ሰራሽ ፀሐይ’ በ1 ሺህ ሰከንድ ከ100 ሚሊየን ዲጊሪ ሴልሽየስ ሙቀት 1 ሚሊየን አምፒር ከረንት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማምንጨት የተያዘውን ግብ ማሳካቱን ተነግሯል።

ቻይና ለዓለም አዲስ የሆነው እና ”ሰው ሰራሽ ፀሐይ” የሚል ስያሜ ያለው ይህ ከብክለት ነጻ የሆነ የኑክሌር ማብላያ በፈረንጆቹ 2020 ላይ ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።

“EAST” የሚል መጠሪያ ያለው ‘ሰው ሰራሽ ፀሐይ’ ከዚህ ቀደም በግንቦት ወር ላይ ለ101 ሰከንድ በ120 ሚሊየን ዲግሪ ሴልሺየስ የሙቀት መጠን በመቆየት አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቦ እንደነበረ ይታወሳል።

የቻይና ‘ሰው ሰራሽ ፀሐይ’ ከወራት በኋላ በደረገችው ሌላ ሙከራ ለ1,056 ሰከንድ በከፍተኛ የፕላዝማ ሙቀት መቆየት መቻሉም አይዘነጋም።

በዚህም በሙከራ ደረጃ ለረጅም ሰዓት የቆየ በሚል ቻይና በራሷ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በማሻሻል አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ማስመዝገቧም አይዘነጋም።

ሰው ሰራሽ ፀሐዩ ከተፈጥሮ ፀሐይ 13 እጥፍ ያክል ሙቀት ያመነጫል ተብሏል።

አል አይን

Exit mobile version