Site icon ETHIO12.COM

የሌብነት ዘመቻው ጥርስ አለው? አብይ አሕመድ 110 ፋይል መከፈቱ ሪፖርት ቀረበላቸው

በኢትዮጵያ ሙስናን እንዲከላከልና እዲያሳድድ ስልጣን የተሰጠው ኮሚሽኑ፣ ቀደም ባሉ አመታት ” ራሱ ሌላ ኮሚሽን ያስለገዋል” ሲሉ ሌብነት እዛም እንዳለ በርካቶች ሲናገሩ ነበር። ትልቅ ስልጣንና ፎቅ ያለው የፌደራል የጸረ ሙስና ኮሚሽን ውስጡን በካሜራ መቆጣጠሪያ ከማድመቅና የሚያስፈራ ድባብ ከመፍጠሩ ሌላ ጥርስ አልባ ድርጅት እንደሆነ መረጃ ጠሰው ለዓመታት ሲወቀስ የኖረ ተቋም እንደነበር ይታወሳል።

ተጠሪነቱ በቀጥታ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሆን ተደርጎ በአቶ መለስ ውሳኔ በሃያ አራት ሰአት ውስጥ “የተሰራው” ይህ ኮሞሽን የፖለቲካ ቂምና ቁጣ መወጣጫ ድርጅት ስለ መሆኑ እዛው ሲሰሩ የነበሩና የኮበለሉ መስክረውበታል።

አሁን ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ “ብሔራዊ የጸር ሙስና አስተባባሪ ኮሚቴ” ላዩ ላይ የደረቡበት ቦርድ ምን ያህል ኮሚሽኑንን እንደሚያንቀሳቅሰው ባይታወቅም፣ ቦርዱ ከተቋቋመ ወዲህ ብቻ የሰራቸው ስራዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት አስገምግሟል። በግምገማው በአጭር ጊዜ ውስጥ ብቻ ከህብረተሰቡ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሙስና ወንጀል የተመለከቱ ጥቆማዎች እንደደረሱት አስታውቋል። ይህንን ጥቅሰው ሚዲያዎችም እየዘገቡ ነው።

ከትህነግ ጋር የስደላም ስምምነት ከመፈረሙን ጋር በአንድ ላይ ይፋ የሆነው ይህ ሌብነት ያሳድዳል የተባለው ቦርድ፣ ከሕዝብ ከደረሱት በርካታ ጥቆማዎች ውስጥ አንጥሮ በህግ አግባብ እንዲጣሩ 110 የምርመራ መዝግቦች እንዲከፈቱ መደረጋቸውን ይፋ አድርጓል። ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ነው ይህን ያለው።

ይህ ጥርስ አልባ ሲባል የነበረ ኮሚሽን ከብሄራዊ ኮሚቴው ጋር በትብብር አብሮ የሚሰራ መሆኑ ቀደም ብሎ ሲቋቋም ተገልጾ እንደነበር ያታወሳል። አሁን ላይ ይፋ ባይሆንም መንግስት የሰለጠኑ የኢኮኖሚ ደህንነት አስጠባቂ አካላትን አዘጋጅቶ ከፍተኛ ስራ መስራቱ ታውቋል። ከሚቀርበው ጥቆማ በተጨማሪም በክትትልና በኔትዎርክ ከፍተኛ ሃብት የመዘበሩ ሌባ ሃባታሞች፣ የሚያዘርፏቸው ባለስልጣናትና እየተለዩ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” አንድ ባለገንዘብ አንድ ሚዲያ ይዞ…” ሲሉ ሳያፈርጡ ምሳሌ የሰጡበት ይህ የኔት ዎርክ ጉዳይ መፍትሄ ሊበጅለት ከዳር በመድረሱ እርምጃ ሲወሰድ የሚፈጠረውን ጫጫታና ግር ግር ለመግታት በወጉ ስለጥነዋል የተባሉ የጸጥታ አካላት ከወዲሁ በቂ ስምሪትና የስምሪት ቁርጭት መፍጠራቸውን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ገልጸዋል።

መንግስት በጩኽትም ሆነ በግርግር ሌብነት ላይ የተጀመረው ዘመቻ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በተደጋጋሚ እገለጸ ነው። ይህን ዘምቻ ለማስቆም እዛና እዚህ የተሚሞከሩ ውንብድናዎች እንቅፋት እንደማይሆኑም መንግስት አቅሙን ተማምኖ ነው የሚገልጸው። ይህንን የሚከታተሉ ኮሚሽኑ ስልጣኑንን እንዲጠቀም ከፍተኛ ድጋፍ ስላለው ጥርሳም ይሆናል ብለው እንደሚያምኑ አመልክተዋል።

Exit mobile version