Site icon ETHIO12.COM

አብዮት ሲረጋጋ ክምሩን ይወቃል

Women stand next to a window at Wukro General Hospital in the city of Wukro, north of Mekele, on February 28, 2021. - Every phase of the four-month-old conflict in Tigray has brought suffering to Wukro, a fast-growing transport hub once best-known for its religious and archaeological sites. Ahead of federal forces' arrival in late November 2020, heavy shelling levelled homes and businesses and sent plumes of dust and smoke rising above near-deserted streets. Since then the town has been heavily patrolled by soldiers, Eritreans at first, now mostly Ethiopians, whose abuses fuel a steady flow of civilian casualties and stoke anger with Nobel Peace Prize-winner Abiy. (Photo by EDUARDO SOTERAS / AFP) (Photo by EDUARDO SOTERAS/AFP via Getty Images)

ለስም ያህል ለውጥም ይባል እንጂ ያለፉት አራት፣ በተየም ሁለቱ ዓመታት ከልብ ኢትዮጵያዊ ለሆኑ ጥቅጥቅ ያለ የፈተና ጊዜ፣ ለመንግስት ደግሞ ስም ሊወጣለት የማይችል እጅግ የከበደ፣ ከመሞት ብቻ የሚቀል ጊዜ ነበር። ይህን እውነት ማንም ህሊና ያለው አይክደውም። ብልጽግና ውብ ስም ይዞ ሲንደፋደፍ የኖረውም በዚሁ የለውጥ አበሳ ውስጥ ላለመውደቅ ሁሉንም አዝሎ፣ ያገኘውን ሁሉ እንደ ጩሉሌ የክረምት ምግብ በማግበስበሱ ነው።

የደህንነት አመራሮቹ ዳር ዳሩን ሲወራ የነበረውን ሁሉ ሰሞኑንን ይፋ አድረገውታል። አዲስም ባይሆን ሃላፊዎቹ እንደ ጸሃይ በሚያበራ ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብለው እንዳስታወቁት አገሪቱ ፖሊስ፣ መከላከያ፣ ደህንነት፣ ኢኮኖሚ የሚባል ነገር አልነበራትም። ሌላው ቀርቶ መረጃው እንኳን ተሰውሮባት ባዶ ቤትና እዳ ነበር የታቀፈችው። ሁሉን ጠርጎ ባዶ ቤት ያስረከበው ደግሞ ” በሴራ” አምራችነቱ የሚታወቀውና በነጻ አውጪ ስም ኢትዮጵያን ሲነዳት የነበረው ትህነግ፣ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ነበር። ትህነግን ትህነግ የምንለው በስሙ የቆረበ፣ ጫካ ሆኖ፣ መንግስት ሆኖ፣ አፍሪካ ላይ ተቀምጦ፣ የተባበሩት መንግስታትም ገብቶ ስሙን ሊቀይር የማይፍለግ፣ ሁሌም ኮሳሳ አስተሳሰብ ውስጥ የሚርመጠመጥ፣ ዘር ላይ ተንጠልጥሎ፣ በዘራው የዘር መርዝ የሰከረና በዛው ራሱ በጠመቀው መርዝ ሳቢያ አገርና ህዝብ ያደቀቀ ድርጅት በመሆኑ ብቻ ነው።

እዚህ ኦና ቤት ውስጥ የገባው ኢህአዴግ ውስጥ የተወለደው የለውጥ ሃይል ያገኘውን ሁሉ አግበስብሶ ያለፉትን አራት ዓመታት ያለ አንዳች እረፍት ሲናጥ፣ ከውስጥና ከውጭ ሲወገር፣ በሰበሰበው ግብስብስ ሲታመስና ሴራ አምራቾች በሚለቁት ተለዋዋጭ የነጠላ ዜማ ንፋስ ሲሰቃይ ቢቆይም፣ ሕዝብ ከጎኑ ሆኖ ሁሉንም አስተንፍሶ በድል ለመውጣት ችሏል።

የዓለም ታላላቅ የሚባሉ መሪዎች፣ አገሮች፣ ተመድን ጨምሮ ታላላቅ ድርጅቶች፣ ተቋማት፣ ሚዲያዎችና ግለሰቦች “ምን አደረግናቸው” እስኪባል መከራ ሲያዘንቡብን፣ “ኢትዮጵያዊ” የሚባሉት ወገኖች፣ በቢቢሲ፣ ቪኦኤ፣ጀርመን ድምጽ ሳይቀር ሽብር ሲረጩብን፣ ” እነተርፋለን” ብሎ ያሰበ አልነበረም። ግን አለፈ። ኢትዮጵያ አሸነፈሽ። የሚዲያ ባንዶችን እየገላመጠች፣ ለነሱ ጥቁር ካባ የሚያለብሱትን ተላላዎች እየገረመመች ዛሬ ላይ ደረሰች። ኢትዮጵያ ስታሸንፍ ተባብረው የዘመቱብን ሁሉ ዘፈናቸው ተቀየረ። ትህነግም ልክ እንደ ሌሎች ወገኖቹ በመቀመጫው ልክ እየተሰፈረለት ለመኖር ማለ። እዛም እዚህም አልፎ አልፎ ከሚጮሁት በስተቀር ኢትዮጵያ ሱሉሱን አዙራ አዲስ ለውጥ ጀመረች። እንግዲህ አብዮት ሲረጋጋ ክምሩን ይወቃል ማለት ይህ ነው። እንዴት?

ባዶ የነበረችው ኢትዮጵያ ግዙፍ ጦር፣ አስፈሪ አየር ሃይል፣ አያያዙ አጓጊ ደህንነትና የጸጥታ ተቋም ገንብታለች። እየገነባችም ነው። መገንባታቸው ብቻ ሳይሆን ዘመናዊና ወቅቱ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጂ እየተላበሰች ነው። የወደፊቷ ኢትዮጵያ የምትሰራበት የሳይንስ ማዕከል ስራ ለማይገባቸው ጉዳዩ ውስብስብ ቢሆንም ሃቁ ይህ ነው። ” የምናደርገውና ልናደርግ ያሰብነው የሚገባቸው ጠላቶቻችን ናቸው” ሲሉ አብይ አህመድ እንዳሉት መሆኑ ነው። ደግሞም ነው። ስንዴው ምስክር ነው። አርትርፊሻል ኢንይተለጀንስና … ብዙ ሊባል ይችላል።

አሁን ጦርነቱ ጋብ ሲል “ሌቦች” የተባሉ ላይ ዘመቻ ሲጀመር ጎን ለጎን ለሁለት ዓመት ሲሰራ የነበረ የውጭ ግንኙነት አስፈጻሚዎችና የአምባሳደሮች ምንጠራ አልቋል። በሁለት ቢላ ሲሸከሽኩ የነበሩ የጠሩ ይመስላል። የሚኒስትሮች ምክር ቤትም ይጠራል ተብሏል። ደመቀ መኮንን ጭምሮ አቅምና አቋማቸው የማይፈቅድላቸው እንደሚወገዱ ጅምሩ ያሳያል።

ከምንም በላይ አሁን ወደታች ይወርዳል የተባለው ዘመቻ መንጥር መንሹን በጅምላ የሰበሰባቸው ላይ እንደሚያነሳም ተሰምቷል። መንግስት ከመቃተትና ከመዛል ተላቆ በገነባው ሃይል ሴረኞችን መልቀም የሚያስችል ክንድ ስላለው ” ውቂያውን” እንደሚያከረው እየተሰማ ነው። በስመ ” ባለሃብት” ጸብ ለረጩ ክፍያ ከሚያዘጋጁት ጀምሮ በቢሊዮን ዕዳ ተሸከመው ፊልም የሚሰሩትን ሊገርዛቸው ዝግጅቱ እንዳለም ነፋሱ እያሳበቀ ነው። አንድ ኮዳ ቅባት ሳያመርቱ የጎበዝ አለቃና ዱርዬ የሚያደራጅና ያደራጁ ሁሉ በቅርቡ በምስፈሪያቸው እንደሚሰፈሩ አመላካች ደወሎች እየተሰሙ ነው። መንግስት ይህን የሚያደርገው ለህዝብና ብሎ ሳይሆን ይን ካላደረገ ሊበሉት የሚችሉ እባጮች ስላቆጠቂጡ ነው።

እነዚህ በደሃው ሃብት ከብረው በማይከፈል ብድር ላይ ተሰቅለው ድራማ የሚሰሩ ቁጭበሉ ሃብታሞች በሚሊዮኖች እየከሰከሱ ሰርጋቸውን፣ ምላሻቸውን፣ ተስካራቸውን ከሚያሳዩን በቀር፣ አሸባሪ እያሰማሩና እያስታጠቁ ከሚያሰቃዩን በቀር፣ ዕዳቸውን በወጉ እየከፈሉ አገር የሚያለሙትን ወደ ህገወጥ መንገድ እንዲያመሩ ከማመላከት በቀር ሌላ ጥቅም ስለሌላቸው፣ በህጋዊ ኤክስፖርትም ሆነ የአገር ውስጥ ምርት ተሳትፎ ስለሌላቸው መንግስት መንሹን ቢያነሳባቸው ድጋፍ፣ ደግ አደረክ፣ እሰይ ከሚል ድምጽ ውጭ ምንም እንደማይሰማ ግልጽ ነው።

አሁን ላይ በምርመራ የተያዘው መረጃ ገሃድ ቢወጣ ለቀናት ራስን አስይዞ ጸጉር ከሚያስነጭ ዜና ውጭ ታሪክ የሌላቸው ዱር ሃብታሞች አይነት መንግስት ቤትም አሉ። ህዝብ ፊት እየቀረቡ ስለ ሌብነት የሚያወሩ ሃፍረተ ቢስ የኢህአዴግ ምርቶች አሉ። መንሹ ወደዛም እንደሚሄድ ተሰምቷል። ከፍተኛ ጥቆማ የቀረበባቸው አሉና!!

መንግስት አግበስብሶ፣ በደጋፊ ሚዲያ ስም፣ በበታች አደረጃጀትና አወቃቀር ስም፣ የለቃቀማቸውን ሌቦችንም እገረ መንገዱን እንዲያያቸው ማሳሰቢያዎች አሉ። ለውጡ ወደ አብዮት ተቀይሮ የሚጸናው ይህ ሲሆን ነው። ሪፎርም ሲረጋጋ አብዮት መሆኑ፣ አብዮት ሲረጋጋ መንሹን ባግበሰበሳቸው ላይ እንደሚያነሳ ጥርጥር የለውምና!! አለያ ጨው ላእራስ እንዲሉ … ነውና!!

Exit mobile version