ETHIO12.COM

የሰላማዊ ሰልፉ ተራዘመ፤ የስምምነት ፍንጭ እየተሰማ ነው

በኦርቶዶክስ ቤት ክርስቲያን ሲኖዶስ ውስጥ የተፈጠረውን መከፋፍለ ተከትሎ አንደኛውን ወገን ለማውገዝ ተጠርቶ ከነበረው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ መካከል የባህር ዳሩ መዘረዙ ተገለጸ።

“ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንዲቀርብ” ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ ባስተላለፈው ጥሪ መሰረት ነው “ጥር 28 በባሕር ዳር ከተማ እሑድ ጥር 28 ፡ 2015 ዓ.ም ባሕር ዳር መስቀል አደባባይ ሊደረግ የነበረው “ኦርቶዶክሳዊ” የተባለው ሰልፍ እና የምህላ ፀሎት መራዘሙ በመግለጫ የተገለጸው።

“ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ አስተላልፏል። ስለሆነም በቀጠይ በቅዱስ ሲኖዶሱ የሚቀርብልን አቅጣጫ ተከትለን የተጀመሩ ስራዎች ሳይቋረጡ ለጊዜው ለጥር 28 ተጠርቶ የነበረው ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል” ሲል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የባሕርዳር ሀገረ ስብከት አምልክቷል።

ቀደም ሲል “ሼር ፖስት ይሁን” በሚል “ባሕርዳር ኦርቶዶክሳዊ ሰልፍና ጸሎተ ምህላ ጥሪ አድርጋለች። የፊታችን እሑድ ሁሉም ምእመን ከአጥቢያው በኅብረት ተነሥቶ 1:30 ባሕር ዳር መስቀል አደባባይ እንዲደርስ ጥሪ ተደርጓል። በዚህ አጋጣሚ በኮሚቴው ከተዘጋጁ ባነሮች ውጭና ያልተፈቀዱ መልእክቶችን ይዞ መምጣትና ማስተላለፍ የተከለከለ ሲሆን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዐርማ ውጭም ምንም ነገር መያዝ አይፈቀድም ተብሏል” ታውጆ ነበር።

በተመሳሳይ ዜና ችግሩ በመነጋገር ብቻ እንደሚፈታ የመስማማት ፍንጭ መታየቱን ለጉዳይ ቅርብ የሆኑ ገልጸውልናል። ዝርዝሩን ወደፊት እንደሚናገሩ ያስታወቁ ” ኦርቶዶክስ በፖለቲክ ቁማርተኞችና ካድሬዎች ሴራ ከገጠማት ችግር በቅርቡ እንደምትፈውስ አምነት አለን” ሲሉ ተናግረዋል።

“ሁሉም ወገን ጋር እውነት፣ ሁለቱም ወገኖች ጋር ስህተት አለ” ያሉት ክፍሎች፣ እንደ እምነት አባት ንስሃ ገብተው ችግራቸውን መፍታት ሲገባቸው ጉዳዩን ለተመሪው ምዕመን አቀብሎ ለውዝግብ በር መክፈት ትክክል እንዳልሆነ የተቀበሉ አሉ። ከሁለቱም ወገን ስህተታቸውን ለማረም የተዘጋጁ መኖራቸው አንድ እርምጃ እንደሆነ ገልጸው ” ታላቁ መስዋዕትነት ይቅርታ ማድረግና ይቅርታን መቀበል ነው። ይህን የማያደርጉ ክርስትና አለገባቸውም” በሚል መወቀሳቸውንም አመልክተዋል። ህዝበ ክርስቲያኑ ለዕምነቱ ስለሚቀና ከስሜትና ድፍን ጥሪ መታቀብ እንደሚገባ በታመኑ መላዘብ እንደተጀመረ ታዉቋል።

ይህን ችግር በመጥለፍ የፖለቲካ አላማና የቆየ ጥላቻቸውን ለማቀጣጠል ” የማይቀረው ህዝባዊ አብዮት” በሚል ሰሞኑንን ጉዳዩ ላይ ነዳጅ ሲያርከፈክፉ የነበሩ በዜናው መበሳጨታቸው ታውቋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዛሬ የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በመንግስት የተለያዩ ተቋማትና በተወገዙት የቀድሞ ሶስት ጳጳሳትና የተሾሙት 25 ጳጳሳት ላይ ክስ መመሥረቷም ተሰምቷል።

የክሱ ዝርዝር ዋና ዋናዎቹ የቤትክርስቲያንን ክብርና ስም በመንካት፤ በህይወት የመኖር፣ የመዘዋወር እና የማምለክ መብትን በመንካት፤ መንግስት ሁሉን ሰው በእኩል ህጋዊ ጥበቃ እና በእኩልነት የማየት ህገመንግስታዊ ሀላፊነትን ባለመወጣት፤ የቤተክህነት ንብረት ሲዘረፍ እርምጃ ባለመውሰድ፤ ጳጳሳትን እና የቤተክህነት ህጋዊ መዋቅር ውስጥ ያሉትን በማፈን፣ በማሰርና በማስፈራራት፤ የመንግስት ሚዲያ በህዝብ ሀብት እየተዳደረ የቤተክርስቲያኗን መግለጫ እና የደረሰባትን የህግ ጥሰት ባለመዘገብ ህገመንግስታዊ ሀላፊነትን ባለመወጣት፤ አቶ ሀይለሚካኤል ታደሰ የተባሉ የህገወጦቹ ቃል አቀባይ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ፀብ አጫሪ ቅስቀሳ በማድረጋቸው ተከሰዋል።

ክሱ ሰኞ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት በስምንት ሰዓት ይሰማል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በተለያየ አገረ ስብከቶች የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳተ አሁንም አየታሰሩ እንደሚገኙ የቤተ ክርስቲያኗ የዜና ምንጮች ይጠቁማሉ። ይህንን አፈና፣ ማዋከብና እስር በተመለከተ ከመንግሥትም ሆነ በአብዛኛው ችግሩ ከሚከሰትበት ኦሮሚያ ክልላዊ መሥተዳድር የተባለ ነገር የለም።

ከተወገዘው ሲኖዶስ ጋር አብረው የነበሩት እና በኋላም በንሰሐና ይቅርታ የተመለሱት ከጥቂት ቀናት በፊት ታሰርሁ ብለው መልዕክት ከላኩ በኋላ በዚያው ስልካቸው ተለቅቄአለሁ ብለው ለወዳጃቸው መላካቸው ብዙዎችን ጥርጣሬ ውስጥ የጣለ ተግባር ሆኖ አልፏል።

Exit mobile version