ETHIO12.COM

ሰበር ዜና – ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በሃዋርያቶች መንገድ ችግሩን ለመፍታት ተስማማች

በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተፈጠረውን መከፋፈልና ችግር በሃዋሪያቶች መንገድ መፍትሄ እንዲፈለግለት ወደ ስምምነት መደረሱ ተሰማ። ይህ የተሰማው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከሲኖዶስ አመራሮች ጋር መወያየት መጀመራቸውን ተከትሎ ነው። ቅዳሜ ጠዋት መግለጫ ይሰጣል። ዜናውን ከተጻፈ ከሳዓታት በሁዋላ ስምምነቱ ተረጋግጧል።

የቤተክርስቲያኗ አባቶች ዛሬ ረፋዱ ላይ ከመንግስት ከፍተኛ አመራሮችና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በቤተመንግሥት እየመከሩ ነው። ለስብሰባው ቀርብ የሆኑ ክፍሎችን ጠቅሰው ለአዲስ አበባ ተባባሪ ዘጋቢያችን ፍንጭ የሰጡ እንዳሉት፣ ችግሩን ከጣልቃ ገቦች አሳብ ነጥሎ በሃዋሪያነት አግባብ ለመፍታት የመስማማት ፍንጭ አሳይቷል።

በቡራኬ የተጀመረው ውይይት ላይ ሽምግላናውን የሚመሩት ወገኖችና ከአባቶቹ መካከል አሳብ ሲሰጡ ያለቀሱ እንዳሉና ግልጽ ውይይት እየተደረገ መሆኑንን፣ ዕረፍት ላይ ከምጀመሪያው የተለየ ስሜት መታየቱንም እነዚሁ ክፍሎች አስታውቀዋል።

ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስንና አስራ አምስት የሚሆኑ ሊቀነ ጳጳሳት ኢትዮጵያን በሚወዱ የተግባር ሰዎች አማካይነት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ውይይት መጀመራቸው ሲገለጽ ” ክህደት ተጀመረ” በሚል እሁድ ቤተ መንግስትን እንዲወረርና የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ እንዲታወክ ያቀዱ ክፍሎች ተቃውሞ ጎን ለጎን ማሰማት ጀምረዋል።

ክልሎች ከሰላማዊ ውይይት በስተቀር በእምነት ስም የሚደረገውን መንግስትን የመናድ አካሄድ እንደማይቀበሉ እያስታወቁ ባለበትና ውይይት ብቻ መፍትሄ እንደሚሆን እያስታወቁ ባለበት ሰዓት የተሰማው ዜና ለተጨነቁ እረፍት እንደሚሆን የዜናው ሰዎች አስታውቀዋል።

በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ በርካታ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ተጠራርተው በተጠናና ቅንጅት ባለው መልኩ ዘመቻቸውን በጥድፊያ እያካሄዱና ” ቤተ መንግስት ውረሩ፣ ይህ አጋጣሚ ከተበላሸ ሌላ አጋጣሚ አይገኝም” ሲሉ የነበሩ ውይይቱን ተከትሎ ማምሻውን ማብራሪያና ትንተና ይሰታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

“የቅዱስ ሲኖዶስ የሰማዕትነት ጥሪ” ሲሉ የእሁዱን ሰልፍ ” የጠቅላይ ጨዋታ ነው” ያሉት ወገኖች ” መንግስት አጀንዳ ለማስቀየር እና አማራን ለማስወረር በዋግ ኽምራ ዞን በፃግብጅ በኩል ወያኔን እየደገፈ ጦርነት አስጀምሯል” የሚል የጎንዮሽ ቅስቀሳም እያሰራጩ ነበር። ይህ ሁሉ ቢባልም መንግስት ትናንት ከክልልና ከፌደራል የፓርቲው አመራሮች ጋር ከተወያየ በሁዋላ ክልሎች አቋማቸውን ህገመንግስት ጠቅሰው ማስታወቃቸው የፈተረው ስሜት እስካሁን ብዙም አልተባለለትም።

መንግስት ከህገ መንግስቱ አግባብ ውጭ ምላሽ መስጠት እንደማይችል በማሳሰብ ክልሎች መግለጫ እያወጡ ሳለ የተሰማው የስምምነት ዜና ለሕዝብ በገሃድ እንደሚገለጽ መረጃውን ያካፈሉን አስታውቀዋል። የአማራ ክልል ብቻ ውይይቱ እስኪጠናቀቅ ጠብቆ በውጤቱ መደሰቱን አመልክቷል።

ይህ ዜና ከተዘገበ ከሰዓታት በሁዋላ ስምምነት መደረሱና ቤተ ክርስቲያን ቅዳሜ ጠዋት መግለጫ እንደምትሰጥ ተመልክቷል። በዚህም ዜና እውነትነት የመረጃ ምንጮቻችንን እናመሰግናለን።

Exit mobile version