Site icon ETHIO12.COM

“የቅዱስ ሲኖዶስ የሰማዕትነት ጥሪ” የተባለው ሰልፍ እይካሄድም

ራሳቸውን “አክቲቪስትና ጋዜጠኛ” በሚል የሰየሙ ” የቅዱስ ሲኖዶስ የሰማዕትነት ጥሪ ” ሲሉ የጠሩት ሰልፍ እንደማይካሄድ ታወቀ። ሁሉም ነገር በእርምት ወደነበረበት እንደሚመለስም ተሰምቷል። ይህ በተሰማ ቅጽበት የዕቅዱ አንቀሳቃሽ መሆናቸውን ሲገልጹ የነበሩ ግን ንዴታቸውን እየገለጹ ነው።

ዛሬ በቤተ መንግስት ውይይት ከተደረገ በሁውላ ቅዱስ ሲኖዶስ አጭር፣ ግን ሰላም መውረዱን የሚያበስር መግለጫ በገሃድ መስጠቷን ተከትሎ የተቃውሞ ድምጽ ቢሰማም፣ ሰላማዊ ሰልፍ እንደማይካሄድ ማስተማመኛ መሰጠቱ ታውቋል። ይህም ቅዳሜ ይፋ እንደሚሆን ተመልክቷል። ይህ እንደሆነ መረጃው ያላቸው በቅጽበት ሙስሊም ወገኖችን የማተራመስ አዲስ አጀንዳ መከፈቱን አብስረዋል። ለተግባራዊነቱም ኦሮሚያን ነቀምት መመረጡ ታውቋል። ድፍን ወለጋ መከላከያ ከገባ በሁዋላ እየተወነጃጀሉ ነገር ግን አብረው የሚሰሩትን ሳይለይ ከመታ በሁዋላ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ነዋሪዎች መመስከራቸው ይታወሳል።

የኦርቶዶክስን ቀኖናና የቤተክርስቲያኒቷን ህግ የተከተለ ጥያቄ መነሳቱን ተከትሎ በከፍተኛ ደረጃ የፖለቲካ አጀንዳ መራገቡ ሊካድ በማይችል ደረጃ ” ቤተመንግስት ውረር፣ ድል ያለምስዋዕትነት አይገኝም፣ ሴሪላንካን ተከተል …” የመሳሰሉ ጥሪዎች ሲተላለፉበት ነበር።

አገራቸውን የሚወዱ ባደረጉት ርብርብና የዕምነቱ አባቶች ባሳዩት ፈቃደኛነት በቤተመንግስት በተካሄደ ግልጽ ውይይት በተደረሰ ስምምነት መሰረት ቤተክርስቲያ የጠራችውና ፖለቲከኞች የጠለፉት ሰልፍ እንደሚሰረዝ ታውቋል።

” ግብጽ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተቆርቁራ እሷ በጠራቸው ስብሰባ እንዳኝ? የአፍሪካ ህብረትን ከኢትዮጵያ ለመንቀል ድንጋይ ስትፈነቅል ለኖረችው ግብጽ የዓላማዋ ማሳኪያ እንሁን? ይህ ነው የኦርቶዶክስ ታሪኳ? ኢትዮጵያ በልጆቿ አለመግባባት ትልቁን አጀንዳ ትጣ? ይህ በታሪክ ይመዝገብ?… ” በሚል አንድ ሽማግሌ በውይይቱ ላይ ሲናገሩ ያነቡ አባቶች ነበሩ። ለውይይቱ ቅርብ የነበሩና ቅድሚያ በስምምነት መጠናቀቁን የገለጹልን እንዳሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከሁሉም አንጀት ዘልቆ የሚገባ አሳብ ተሰንዝሯል። በዚህም ሳቢያ ሃዘን የተሰማቸው ይህንኑ ስሜታቸውን በሲቃ ግለጸዋል።

ነገ ሲኖዶስ መግለጫ እንደምትሰጥ ይፋዊ ቀጠሮ የያዘች ሲሆን፣ በዚሁ መግለጫ ላይ ሰልፍ እንደማይካሄድ በይፋ ይነገራል። ይህንኑ መግለጫ ቀድመው ጫና ለማድረግ ቀደም ሲል የወጡ መግለጫዎች ሙሉ በሙሉ ሊተገበሩ እንደሚገባ በመግለጽ ” ስምምስነቱ የባድመ አይነት ነው” በሚል 360 ጽንፍ ረግጦ ማምሻውን ሲተነትን ነበር። ሰልፉ እንደማይካሄድም ግምቱን ሲያስቀምጥና ይህ ሽንፈት መሆኑንን ሲያውጅ ነበር።

ይህንኑ የቤተክርስቲያን ችግር ተንተርሶ የተነሳው ተቃውሞና የሰልፍ ጥሪ አካሄድ ያስጨነቃቸውና በጉዳቸው፣ በልባቸውና በምግባራቸው ዝቅ ብለው በእንባ የጸለዩ ” ጸሎታችን ተሰማ” በሚል በሰሙት ዜና ምስጋና እያቀረቡ ናቸው። እነዚሁ ወገኖች አምላክ ጨርሶ ምህረቱን እንዲያወርድ እየተማጸኑ ነው።

Exit mobile version