Site icon ETHIO12.COM

ዲያስፖራው የሽግግር መንግስት ሲጠይቅ አንቶኒ ብሊንከን ለስራ አዲስ አበባ ይመጣሉ

በየትኛው ጠቅላላ ጉባኤና ምርጫ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወኪል እንደሆኑ፣ ማን እንደመረጣቸው የማይታወቁትን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት መሆናቸውን የገለጹ ከለውጡ በሁዋላ አንድም በጎ ተግባር እንዳልሰራ አድርገው የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ባስታወቁ ማግስት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አዲስ አበባ ለስራ እንደሚገቡ ይፋ ሆነ።

ኢትዮጵያዊያን በሚኖሩባቸው አደባባዮች ለተቃውሞ አውራጎዳናዎችን እንዲሞሉ ከወዲሁ በሚያሳስብ መልኩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ የማስጠንቀቂያ ናዳ ያወረደው ደብዳቤ ” ዶላር አንልክም” የሚል ማስፈራሪያ አስቀድሟል።

ሰዎች ለቤተሰቦቻቸው ወይም ለወገኖቻቸው የሚልኩትን ገንዘብ ማስፈራሪያ ያደረገው የድርጅቶቹና ማህበራቱ ደብዳቤ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ክደውናል” ሲል ይወተውታል። በአብዛኞች የሚደጋግሙትና ውጭ ባሉ ማህበራዊና ለዚሁ ዓላማ በተቋቋሙ አውዶች የሚሰማው ይህ ክህደት በትክክል ምንና እንዴት እንደሚፈጸም አልተገለጸም።

በተደጋጋሚ እንደሚሰማው ግን የሁሉም ፍላጎት ህገመንግስቱ ተቀዶ እንዲጣል ሲሆን አሁን ባለው የአገሪቱ ህግ መሰረት ህገ መንግስቱን ለመቀየር ሁሉም ክልሎች ሊስማሙበት እንደሚገባ፣ ካልሆነም በድምጽ ብልጫ የሚፈጸም እንደሆነ የህገ መንግስት አዋቂዎች ሲያስረዱ ሰንብተዋል። ክልሎች ለመቃወምና “አይሆንም” ብለው በረ እንዲዘጉ ተደርጎ የታሰረውን ህገ መንግስት ቀደው እንዲጥሉ የሚጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጅምሩ “ለሁሉም ህጋዊ አካሄድ አለው” ሲሉ መመለሳቸው ይታወሳል። ድርግቶቹም ሆኑ ማህበራቱ ይህንኑ ተቀብለው ከመንግስት ጋር በአገር ጉዳይ ሲሰሩና ሲታገሉ መቆየታቸውም አይዘነጋም።

በቅርቡ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጠረውን አለመግባባት ተክከትሎ ድምጻቸውን አጥፍተው የከረሙ ከያሉበት መነሳታቸውን ተከትሎ ” የሽግግር መንግስት ይቋቋም” ሲል የማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ያሰራጩት ማህበራትና ድርጅቶች “ዲያስፖራው ክንዱን ይጠቀማል” ዓይነት ዛቻ ዝተዋል። ዶላር መላክ እንደሚያቆሙም አመልክተዋል። እነዚሁ አካላት በመግለጫቸው መንግስት ትህነግን ዳግም ለማቋቋም እንደሚሰራም ገልጸዋል። መንግስት ያቋቋመውና ከአርባ በላይ ፓርቲና ድርጅቶች ጋር ለመስራት ተስማምቶ በሂደት እየተንቀሳቀሰ ያለው የአገራዊ እርቅ ኮሚሽን፣ ህገመንግስት እስከመቀየር ድረስ ስልጣን ያለው እንደሆነና ይህንኑ ሊያደርግ እንደሚችል መገለጹም አይዘነጋም።

በሽብርተኛነት የተፈረጀው ትህነግ በትግራይ የመቀጠልና የመሞት ውሳኔ የሚያገኘው በኢትዮጵያ መንግስት ሳይሆን በትግራይ ህዝብ ፍላጎት መሆኑ እየታወቀ፣ የሰላም ስምምነቱ የሚያመታውን በረከትና የሚያስከፍለውን ዋጋ መክፈል ግዴታ ሆኖ ሳለ “ሰላም ጥሩ ነው፣ ለሰላም የሚከፈለው ዋጋ ትክክል አይደለም” የሚል እንደምታ ያለበት ደብዳቤ እንዳስገረማቸው የሚገልጹ ” ጨዋታዋ ተደራጅተውና ታግለው ስልታን መያዝ የማይችሉ ሃይሎች ሲያካሂዱ የነበረው የትርምስ ፖለቲካ ዓላማ ማሳረጊያ” እንደሆነ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የሽግግር መንግስት ብሎ ቀለድ እንደማይሰራ መናገራቸውና ፣ ክልሎችም በመሪዎቻቸው በኩል በህግ በተሰጣቸው መብት እንደማይደራደሩ ግልጽ አድርገው መናገራቸው አይዘነጋም።

ይህ በተሰማና መንግስት ለማስቀየር የዶያስፖራ ወኪል ነን የሚሉ ደወል በደወሉ ማግስት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ሊያደርጉ ቀን መቁረጣቸውን መንግስት ይፋ አድርጓል። አንቶኒ ብሊንከን ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ በኢትዮጵያ እና ኒጀር የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ነው ይፋ የሆነው።ተሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የፊታችን ረቡዕ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ነው የተናገረው።

በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ሠላም ለማሥፈን በተወሰዱ እርምጃዎች እና የጦርነት ማቆም ስምምነቱን ተከትሎ አፈፃፀሙ ላይ እንደሚመክሩም ይጠበቃል። ምን አልባትም የራውሮፓ ህብረት የጣለውን ማዕቀብ ለማንሳት ከዳር በደረሰበት ሰዓት ይህ ጉብኝት መደረጉ ዜናውን ትልቅ ሊያደርገው እንደሚችል ግምት አለ።

በተጨማሪም የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት አጋሮችን እና የሲቪል ማኅበረሰብ አካላትንም በማነጋገር የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ፣ በምግብ ዋስትና እና በሰብዓዊ መብቶች ላይም ይወያያሉ ነው የተባለው። በተጨማሪም ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ጋር እንደሚወያዩም የመንግስት ሚዲያዎች ጠቁመዋል።

Exit mobile version