Site icon ETHIO12.COM

አሜሪካና ካናዳ ድንበር ጥሰው የሚገቡ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ላለመቀበል ተስማሙ

አሜሪካ እና ካናዳ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ደንበሮቻቸውን አቋርጠው የሚገቡ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ላለመቀበል ከስምምነት መድረሳቸውን መሪዎቻቸው ገለጹ።

ስምምነቱን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ፣ ባይደን ጉብኝት በሚያደርጉባት የካናዳዋ ኦታዋ ከተማ ዛሬ ይፋ እንደሚያደርጉት ይጠበቃል።

ይህ ስምምነት በሁለቱም አራት በኩል ያሉ ባለሥልጣናት ወደ አሜሪካ ወይም ወደ ካናዳ ለመግባት ድንበር የሚያቋርጡ ሰዎችን ወደመጡበት እንዲመልሱ የማድረግ ሥልጣን የሚሰጥ ነው።

አሜሪካ በካናዳ በኩል የሚያዋስናትን ድንበር አቋርጠው ወደ አገሯ የሚገቡ ፍልሰተኞች ቁጥር አሻቅቧል።

ይህ ስምምነት እየጨመረ የመጣው እና ሮክሳም በተባለው መንገድ ከካናዳዋ ኪውቤክ ግዛት ወደ ኒው ዮርክ ግዛት የሚፈልሱ ስደተኞችን ቁጥር ለመገደብ እየተደረገ ያለው ጥረት አካል ነው።

በስምምነቱ መሠረት ካናዳ ከደቡብ እና ከማዕከላዊ አሜሪካ ግጭት እና ጥቃትን የሚሸሹ 15 ሺህ ስደተኞችን የሚትቀበልበት አዲስ መርሃ ግብር እንደሚዘረጋ አንድ በስም ያልተጠቀሱ ባለሥልጣን በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር ለሆነው ሲቢኤስ ኒውስ ተናግረዋል።

ባይደን በካናዳ ኦታዋ በኢኮኖሚ፣ በንግድ እና በስደት ጉዳይ ከትሩዶ ጋር ለመምከር ለ24 ሰዓት የሚቆይ ጉብኝት እያደረጉ ሲሆን፣ የፍልሰተኞች ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥነው ስምምነት ፕሬዝዳንቱ ወደ አገራቸው ከመመለሰቻው በፊት ይፋ ይሆናል።

ሁለቱ አገራት የደረሱበት ይህ አዲስ ስምምነት እንደ አውሮፓውያኑ በ2004 የነበራቸውን ስምምነት ያሻሻለ ነው።

ይህ ስምምነት ስደተኞች አሜሪካ ወይም ካናዳ ከመግባታቸው ቀድመው በሌላ “ደኅንነቱ በተጠበቀ ” ሦስተኛ አገር ጥገኝነት እንዲጠይቁ የሚመራ ነው።

አዲሱ ስምምነ ከቀድሞው በተለየ ካናዳ ይፋዊ ባልሆነ ድንበር የሚያቋርጡ ስደተኞችን እንድትመለስ የሚያሰችል ነው።

የቀደመው ስምምት ፍልሰተኞች ወደ ካናዳ እንዲገቡ የሚያደርግ ነው።

አገራቱ እዚህ ስምምነት ላይ ለመድረስ ወራትን የፈጀ ድርድር ማድረጋቸውንም ሪፖርቶች አመልክተዋል።

የፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳደር በአሜሪካ ደቡባዊ ደንበር ከሜክሲኮ አቋርጠው የሚገቡ ሰዎች ጥገኝነት ለመጠየቅ የሚሂዱበትን መንገድ አስቸጋሪ የሚያደርግ አዲስ ዕቅድ አዘጋጅቷል። ይህ ዕቅድ ከሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ነቀፌታ ገጥሞታል።

ይህ በአሜሪካ እና በካናዳ መካከል የተደረሰው ስምምነት በአሜሪካ ኮንግረስ በከል አልፎ መጽደቅ ሳያስፈልገው በፍጥነት የሚተገበር ይሆናል።

Exit mobile version