Site icon ETHIO12.COM

አብይ አሕመድ በፓርላማ ማብራሪያ ይሰጣሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች፤ ነገ በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተሰምቷል። የኑሮ ውድነት ቀዳሚ አጀንዳ እንደሚሆን ተመልክቷል።

ከፓርላማ አባላት መረጃ እንደሚደርሰው ገልጾ ኢንሳይደር እንዳለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ማክሰኞ መጋቢት 19፤ 2015 በሚኖረው መደበኛ ስብሰባው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከፓርላማ አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎችን የሚሰጡትን ምላሽ እና ማብራሪያ እንደሚያዳምጥ እና የፓርላማ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ያስገቡት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ነው።

“ብዙዎቻችን ‘አይሆንም፤ ተረጋግተን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርብ አይነት ጥያቄ በአግባቡ ማዘጋጀት አለብን’ ስንል እስከ እሁድ አመሻሽ ድረስ አቅርቡ ተባለ” ሲሉ ጥያቄ የማቅረቢያ ጊዜው በአንድ ቀን እንዲራዘም መደረጉን አስረድተዋል።በዚህ አካሄድ እስከ ባለፈው ሳምንት እሁድ አመሻሽ ድረስ፤ የፓርላማ አባላቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያቀርቧቸውን ጥያቄዎች አስገብተው ማጠናቀቃቸውን ጨምረው ገልጸዋል።

በነገው ዕለት በሚካሄደው የፓርላማ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሚቀርቡ ጥያቄዎች መካከል፤ “የኑሮ ውድነትን የተመለከቱ ይኖራሉ” ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች ጠቁመዋል። “ወደ አዲስ አበባ አትገቡም እየተባለ ወደ አማራ ክልል የሚመለሱ ሰዎች” ጉዳይን የተመለከቱ ጥያቄዎችም፤ በነገው የፓርላማ ስብሰባ ጥያቄ ሊቀርብ እንደሚችል ዘገባው ግምቱን አስቀምጧል።


Exit mobile version