Site icon ETHIO12.COM

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ 100 ጉቦ በመቀበላቸው ከስራ ተሰናበቱ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ ዓመት 12ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ በዚህም መደበኛ ሥብሰባው ላይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩትን ፋንታሁን ደለለው ሽፈራውን ከሥራ አሰናብቷል።

የሥራ ስንብት ውሳኔ ሃሳቡን ያቀረቡት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እፀገነት መንግስቱ፤ ፋንታሁን የዳኞች የሥነ-ምግባርና የዲሲፕሊን ክስ ሥነ-ስርዓት ደንብ በመተላለፍና የሐቀኝነት ተነጻጻሪ ግዴታ በመተላለፍ ከአመልካች ብር 100 ሺሕ (አንድ መቶ ሺሕ ብር) መደለያ (ጉቦ) መቀበላቸው በማስረጃ ተረጋግጧል ብለዋል።

ምክር ቤቱም የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ ሪፖርት ካዳመጠ በኋላ የፋንታሁን ደለለው ሽፈራውን የሥራ ስንብት የውሳኔ ሃሳብ ቁጥር 13/2015 አድርጎ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

Exit mobile version