Site icon ETHIO12.COM

መከላከያ በቅድመ ሁኔታ ጓዙን ሰብስቦ አማራ ክልልን ለቆ ሊወጣ እንደሚገደድ ተሰማ

የክልል ልዩ ሃይል አደረጃጀት “ህጋዊ አይደለም” በሚል በፌደራል የጸጥታ መዋቅር እንዲደራጅ በተወሰነው መሰረት ከሌሎች ክልሎች በተለይ አማራ ክልል ላይ ተግባራዊ እንዳይሆን ተቃውሞ መነሳቱና አሁንም ድረስ መቀጠሉ ይታወሳል። ተቃውሞው ከተቃውሞ አልፎ መከላከያን በተለያዩ አካባቢዎች በመተናኮልና በጥይት በመምታት የታጀበ እንደሆነ ምስክሮች እየገለጹ ነው።

በዚህም መነሻ የአገር መከላከያ ሰራዊት እየተተነኮሰና ” አንምንህም” እየተባለ አማራ ክልል መቅመጡ አግባብ ባለመሆኑ፣ አጻፋ እርምጃ ከውሰደ ጉዳቱ የአገርና የወገን በመሆኑ ለጥንቃቄ ሲባል ነው መከላከያ ጓዙን ጠቅልሎ መንግስት በሚያስቀምጠው ቅድሚያ ሁኔታ መሰረት ክልሉን ለቆ ሊወጣ እንደሚገደድ የተሰማው።

በማህበራዊ ሚዲያ “መከላከያን በለው፣ ደምስሰው” የሚል መመሪያና መፈክር ሲስተግባ እንደነበር ያስታወሱና አካሄዱ መከላከያን እልህ ውስጥ በመክተት ወደ ለየለት ትርምስ ውስጥ የመግባት በመሆኑ ነው መከላከያ ይህን እርምጃ ሊወስድ የሚገደደው።

ከየትኞቹ አካባቢ እንደሚለቅ ዝርዝር ባይገለጽም በውልቃይት በኩል ጥቃት ስለተዘነዘረበትና ግፊቱ ስለበዛ ስፍራውን ሊለቅ እየተገደደ መሆኑን እማኞች አስታውቀዋል። አካባቢውን ለቀው ከሚወጡት መካከል የአማራ ልጆች ሆነው መከላከያን የሚያገለግሉ የኢትዮጵያ ልጆች ይገኙበታል።

መከላከያ ቁልፍ የሚባሉትን የስጋት አካባቢዎች ለቆ ሲወጣ ማን ሃላፊነቱን እንደሚወስድና እንደሚተካው አልተገለጸም። ጉዳዩን የሰሙ ዜናውን ገለጹት እንጂ መንግስት በይፋ የገለጸው ነገር የለም።

Exit mobile version