Site icon ETHIO12.COM

የፊታችን ማክሰኞ ከሸኔ ጋር የሰላም ንግግር በይፋ ይጀመራል

ከሸኔ ጋር የሚደረገው የሰላም ንግግር ከነገ ወዲያ በታንዛኒያ የሚጀመር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በሂደቱ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉ የእውቅናና ምስጋና መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ወዳጅነት መናፈሻ በተካሄደበት በዛሬው ዕለት ነው።

ኢትዮ12 በኦሮሚያ ካሉ የተቀናቃኝ ድርጅቶችና ሸኔ ጋር የሰላም ነገገር ለመጀመር የቅድመ ሁኔታ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ቀደም ብ፤አ መዘገበቧ ይታወሳል። በዚህ ዘገባ ችግር ሆኖ የነበረው የሸኔ አመራር ነን ባይዮች መበራከታቸው ብቻ እንደነበር ጠቅሰን ነበር።

አብይ አህመድ “ጦርነት ይብቃ፣ ሰላማችንን እናጽና” ሲሉ በመርሐግብሩ ላይ መልእክት ሲያስተላልፉ እንዳሉት የኢትዮጵያን ሰላም ለማረጋገጥ እስካሁን በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል።

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ብዙ ውጤቶች የተገኙበት መሆኑን በመጥቀስ ይህንን የሰላም ተግባር በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ማስፋት ይገባል ብለዋል። በዚሁ ሰላምን የማስፋት አገራዊ አጀንዳ አማካይነት የፊታችን ማክሰኞ ከሸኔ ጋር በታንዛኒያ የሰላም ንግግር እንደሚጀመር አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ ፓርላማ በሪፖርታቸው የጋምቤላ አማጺያን ጋር ውይይት መጀመሩን ጠቅሰው የነበረ ሲሆን በተባለው መሰረት ራሱን ” የጋምቤላ ነጻ አውጪ” የሚለው ቡድን ትጥቁን ፈቶ በሰላም ክልሉን ለማልማት መግባቱን በይፋ ማስታወቁ ይታወሳል።

በአማራ ክልል ቅማንት፣ አገው የመሳሰሉት ንቅናቄዎች በሰላማዊ መንገድ መንቀሳቀሰ እንዲችሉ ንግግር መጀመሩ ይታወሳል። የቤኒሻንጉል ጉምዝ ነጻ አውጪ ብረት ማውረዱን አመራሮቹ በይፋ አሶሳ በተካሄደ ስን ስርዓት ላይ ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

ከትህነግ ጋር የተደረገውን የሰላም አማራጭ ስምምነት ተከትሎ የፊታችን ማክሰኞ ከሸኔ ጋር የሚካሄደው የሰላም ንግግር ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም ወገኖች የበኩሉን እንዲወጣም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አስተላልፈዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያው ርዕሰ መስተዳድር አቶ ረዳ ” ጦርነት ሰልችቶናል” በሚል የትግራይ ህዝብን የሰላም ጥማት በገለጹበት ንግግራቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ” በነካ እጃቸው ከሁሉም ጋር ሰላም እንዲፈጠር እንደሚሰሩ እምነቴ ነው” ካሉ በሁዋላ ይህ እንዲሆን የበሉላቸውን እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል። አቶ ጌታቸው በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት መርዝ ሲረጩ የነበሩ አንደበቶች ሰላምን የሚያጸና መልካም ቃላትን እንዲያሰሙ ተማጽነዋል። ወደፊት ብዙ እርምጃ መራመድ ስንችል ወደ ሁዋላ ቀርተናል። ብዙ መከበር ስንችል ዕድሉን አበላሽተናል። ሲሉም የጦርነትን ክፋት በብዙ መገለጫዎች ተንትነዋል።

“የኢትዮጵያ የጦርነትና የመከራ ጊዜ አብቅቶ፤ ትናንትን ተሻግረን ለነገ የተሻለ ለመስራት ሁላችንም እንዘጋጅ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለሁሉም ወገኖች ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ ጌታቸው ይህን ብለዋል።

“የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንዲፋጠን የጠሚ አብይ አህመድ ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው። አሁንም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈጣን እርምጃዎች የተጀመረውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ መስራት አለበት እላለሁ። የትግራይ ህዝብ ጦርነት ሰልችቶታል። ከማንም ጋር ጦርነት መግባት አንፈልግም። ከአማራም ከአፋርም የሚያቀራርብ እንጂ የሚያቃቅር ነገር የለንም።

ትናንት በአፋር በኩል የሰላም ባስ አገር አቋራጭ አልፏል። ሐጂ አወል ይህንን ለማጠናከር መስራት ይገበዋል። በተመሳሳይ ከአማራ ክልል ጋር በተያያዘም ዶክተር ከፋለ ኃላፊነት ወስደህ መስራት አለብህ ለማለት እፈልጋለሁ።

ዶክተር አብይ በጀመረው እጁ በሌሎች አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶችን በሆደ ሰፊነት ለመፍታት መስራት እንደለበት ለመጠቆም እፈልጋለሁ! በመጨረሻ ከይዋጣልን መንፈስ ወጥተን የፍቅር፣ የስራ ቋንቋ መጀመር አለብን። ሰላም እንዲፀና የትግራይ ክልል ጊዚያዊ መንግስት የበኩሉን ይሰራል”

Exit mobile version