Site icon ETHIO12.COM

አርሰናል አይኑንን የጣለባቸው ተጨዋቾች

አርሰናል በስኳዱ ጥልቀት ማነስ ነዳጅ ጨርሶ ዋናጫ ባያነሳም ከነበረበት ደረጃ ተስፈንጥሮ በተጸእኖ ፈጣሪነት ሁለተኛ ደረጃ ማግኘቱ ድንቅ ውጤት መሆኑንን በርካታ የስፖርት ቤተሰቦችና ባለሙያዎች ገልጸዋል። የተበለጠው ደግሞ በሲቲ መሆኑ የአርሰናልን ድክመት አጉልቶ ለመውቀስ ብዙም እድል አይሰጥም።

ታዋቂ ሚዲያዎች ” Mikel Arteta’s young side led the race for the title for the majority of the campaign, however, injuries and lack of squad depth influenced a spell of poor form, subsequently blowing their hopes of becoming champions.” ሲሉ እንደጻፉት።

ከዚሁ ካለፈው ጥፋት በመማር ይመስላል አርሰናል ስምንት የሚሆኑ ተጨዋቾችን ሊያስወግድ እየሰራ መሆኑ እይተገለጸ ነው። ክለቡን የማይመጥኑትን ጨመሮ በአግልግሎታቸው ብዙም ፍሬ ያልታየባቸውን ጨምሮ የማጽዳት ስራው ሲሰራ ጎን ለጎን አዲስ የሚገቡት ተጨዋቾች ዝርዝር እየተገለጸ ነው።

የሚታመነው የስፖርት መረጃ አቀባይ ቢቢሲን ጨምሮ በርካታ የስፖርት ታብሎይዶች አርሰናል የሌስተር ሲቲውን የ26 ዓመት አማካይ ካምስ ማዲሰንን፣ የዊስት ሃሙ ዴክለን ሪስ፣ የቀድሞ የቸልሲ አጥቂ ኩካኩ፣ ሌላው የቼልሲ ማሶን ማውንት፣ የብራይቶ ድንቅ አማካይ ሞይሲስ ካሴዶ እና በተከላካይ መስመር ተጨማሪ አርሰናልን እንደሚቀላቀሉና ንግግር መጀመሩ እየተሰማ ነው።

አምስት ተጨማሪ ዓመታትን በአርሰናል ለመቆየት የፈረመው ሳካ ” ቡድኑን እዩት ለጋዎች ነን። የማሸነፍ ፍላጎት አለን። ሻምፒዮንስ ሊግ ገብተናል። ከደጋፊዎቻችን ጋር በስሜት መግባባት ደረጃ ደርሰናል። ይህ ልዩ ስሜት ይሰጣል” ሲል የፈረመበትን ምክንያት ማስታወቁን ተከትሎ እየወጡ ያሉ መረጃዎች አርሰናል አዳዲስ ፊት ይዞ እንደሚመጣ ነው።

ዣካ ሊሰናበትና ወደ ሊቨርኩሰን እንደሚያቀና እርግጠኛ ቃሉን ከመጨረሻው የዎልቭስ ጨዋታ በሁዋላ ይፋ ያደርጋል። ቶማስ ፓርቲም በጣሊያን ቡድኖች እየተዋከበ ነው። ጋላስ እንዳለው ምንም ሆነ ምን አርሰናል ቃሉን ጠብቆ ልምድ ያላቸው ተከላከዮች ማከል ግድ ነው። ለዚህም ይመስላል አርቴታ የክሪስታል ፓላስ ሴንትራል ላይ አነጣጥሯል። የዜና ምንጮቹ ጭብጥ ትክክል ከሆኑ ያፓላሱ ዘሃ ነጻ በመሆኑ አርሰናል የመግባት ህልሙን እውን ያደርጋል እየተባለ ነው።

የጋላታሳራይ ቀኝ ተከላካይ ማናጀርና የክለቡ ቦርድ ሎንዶን ኮሎኒ በንግግር ላይ መሆናቸውም እየተሰማ ነው። ባለፈው የውድደር ዓመት ትልቅ ክፈተ የነበረበት የቀጭ ተከላካይ ችግርና ተደርቦ በክንፍ በኩል ሳካን የመርዳት ስራ ላይ የጋላታሳራዩ Boey ጥሩ ተጨዋች እንደሚሆን ዘገባዎች ይናገራሉ። Members of Galatasaray board are in UK for negotiations. Two English clubs are keen on signing Sacha Boey and Victor Nelsson.

ከዚሁ ተጨዋች ጎን ለጎን ሲቲ በውሰት ለባየር ሙኒክ የሰጠው ካንሴሎን በተጨዋች ልውውጥና ተጨማሪ ክፍያ አርቴታ እጁ ሊያስገባው ከባልደረባው ጋርዲዮላ ጋር መስማማታቸው ተሰምቷል። ካንሴሎ አርሰናል የመጀመሪያ ምርጫው እንዳልሆነ አንዳንድ ሚዲያዎች ቢጽፉም ሊሳካ እንደሚችል የሚናገሩት ይበዛሉ።

Exit mobile version