በጎብኝዎች የተወደዱ ምርጥ ሀገራት

የተባበሩት መንግስታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት (UNWTO) ከሚሰራቸው ስራዎች ውስጥ አንዱ የቱሪዝም መረጃዎችን ይፋ ማድረግ ነው፡፡ በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ቱሪዝም ላይ ወቅታዊ ትንታኔዎችን ይሰጣል፡፡ በዓመት አራት ጊዜ የሚታተም የቱሪስት ፍሰት መረጃን ያወጣል፡፡ ተቋሙ በያዝነው የፈረንጆች 2023፤ ከጥር እስከ ሐምሌ ያለውን የሀገራትን የቱሪዝም ፍሰት እ.ኤ.አ.ከ 2019 ጋር በማነጻጸር ይፋ አድርጓል፡፡ ቀዳሚዎቹ ሀገራት የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. ኳታር

የተባበሩት መንግስታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት (UNWTO) ኳታር በርካታ ጎብኝዎችን በመሳብ 1ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል፡፡ ሃገሪቱ ቱሪስቶችን በመሳብ 95 በመቶ እድገት ማስመዝገቧንም ይፋ አድርጓል፡፡ ሀገሪቱ በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ በጣም ተመራጭ የቱሪስት እና የንግድ መዳረሻ ስትሆን፤ የበረሃ ባሕረ ገብ መሬትንም የታደለች ሀገር ነች፡፡

2. ሳዑዲ አረቢያ

ተቋሙ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያሰቀመጣት ሳዑዲ አረቢያን ነው፡፡ ሃገሪቱ 58 በመቶ የቱሪስት ፍሰት ዕድገት ያስመዘገበች ስትሆን፤ ሀገሪቱ በሃይማኖታዊ እና በታሪካዊ ቅርሶቿ በስፋት የምትታወቅ ሀገር ነች፡፡

3. አልባንያ

አልባንያ እ.አ.አ ከ2019 አንጻር 56 በመቶ የቱሪስት ፍሰት ዕድገት በማስመዝገብ ከ1 እስከ 3 ዝርዝር ውስጥ ተካታለች፡፡ በደቡብ ምስራቅ አውሮፓ የምትገኛው አልባንያ ጥንታዊ ታሪኮች፣ ቅርሶች፣ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ የቱሪስት መዳረሻዎችን የያዘች ሀገር ናት፡፡

4 ኤልሳቫዶር

ኤልሳቫዶር አራተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሀገር ናት፡፡ የቱሪስት ፍሰት ዕድገቷም 32 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በመካከለኛው አሜሪካ የምትገኛው ኤልሳቫዶር “የእሳተ ገሞራ ምድር” በመባልም ትታወቃለች። በየጊዜው የሚከሰተውን የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ትዕይንት ለመታደም በርካታ ቱሪስቶች ወደ ሃገሪቱ ያቀናሉ፡፡

5 አንዶራ

ከዓለም በ5ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው አንዶራ በቱሪዝም ዘርፉ 31 በመቶ እድገት አስመዝግባለች፡፡ አንዶራ በፒሬኒስ ተራሮች ተከባ በፈረንሳይ እና በስፔን መካከል የምትገኝ ትንሽ ራስ ገዝ አስተዳደር ስትሆን፤ ብዙ የበረዶ መንሸራተቻ ቦታዎች የሚገኙባትም ነች፡

6 አርሜንያ

ከዓለም ምርጥ የቱዝም መዳረሻዎች ውስጥ አንዷ የሆነችው አርሜንያ 30 በመቶ የቱሪስት ፍሰት እድገት አስመዝግባለች፡፡ አገሪቷ በተራራማ መልክዓ ምድሮቿ ትታወቃለች። ሀገሪቱ በዓለም ላይ እጅግ ጥንታዊ የሆኑትን ጨምሮ ከ4ሺህ በላይ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት አሏት፡፡ በዚህ አማካኝነትም “የአብያተ ክርስቲያናት ምድር” ተብላም ትጠራለች።

See also  ፓብሎ ሩይዝ ፒካሶ፤ ከ50 ዓመት በኋላ ሲታወስ

7. ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ከፈረንጆቹ 2019 አንጻር በያዝነው የፈረንጆች ዓመት በመጀመሪያዎቹ 7 ወራት የዓለም ቱሪዝምን በመሳብ 7ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን የዓለም አቀፉ ቱሪዝም ተቋም አስታውቋል፡፡ በተቋሙ መረጃ መሠረት ሀገሪቱ ከአውሮፓውያኑ 2019 አንጻር 28 በመቶ የቱሪዝም ፍሰት ዕድገት በማስመዝገብ ከዓለም 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ ኢትዮጵያ በርካታ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ሃብቶች የሚገኙባት ሀገር ናት፡፡

በቅርቡም የሌጲስ ኢኮ ቱሪዝም መንደር በዓለም ድንቅ የቱሪዝም መንደርነት የእውቅና ሽልማት ማግኘቱ የሚታወስ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ማእከላዊ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኘው የሌጲስ መንደር አስደናቂ መልክዓ ምድሮችን፣ ፏፏቴ፣ አእዋፋት እና የተለያዩ የዱር እንስሳት በውስጡ የያዘ እና በጎብኝዎች ዘንድም ተመራጭ ነው፡፡ ሀገሪቱ ከዚህ ቀደም በዓለም ድንቅ መንደርነት የጮቄ ተራራ እና የወንጪ የኢኮ ቱሪዝም መንደርን ያስመዘገበች ሲሆን፤ የሌጲስ መንደር ሶስተኛ ድንቅ የቱሪዝም መንደርነት ሆኖ መመዝገቡ ይታወቃል፡፡

ከታሪካዊ ቅርሶችና ሃብቶች በተጨማሪም እንደ ወንጪ፣ ኮይሻ ፣ጎርጎራ ጨምሮ በአዲስ አበባ የሚሰሩ ፓርኮች ለኢትዮጵያ የቱሪስት ፍሰት እድገት ትልቅ ሚና የሚጫወቱ ናቸው፡፡ የተባበሩት መንግስታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት (UNWTO) ይፋ ባደረገው ዝርዝር ውስጥ ከአፍሪካ ኢትዮጵያ እና ታንዛንያ ብቻ ተካተዋል፡፡ አፍሪካዊቷ ሃገር ታንዛንያ በቱሪስት ፍሰት እድገት 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። አፍሪካ እንደ አህጉር በዚህ የሰባት ወር ጊዜ ውስጥ 92 በመቶው የቱሪስት ፍሰት እድገት አሳይቷል፡፡

በጊዜው አማረ Addis zena


  • እጅግ ግዙፍ የበረዶ ግግር ተገምሶ ስፍራውን በመልቀቅ የሚያደርገው እንቅስቃሴ አስግቷል
    የለንደንን መጠነ-ሥፋት ከ2 እጥፍ በላይ የሚሆን የዓለማችን ትልቁ የበረዶ ግግር ተገምሶ እየሄደ ነው ተባለ፡፡ የበረዶ ግግሩ በፈረንጆቹ 1986 ላይ ከአንታርክቲክ ባሕር ዳርቻ ተቆርሶ በዌድል ባሕር አካባቢ የቆየ ሲሆን፥ ከመጠኑ ግዝፈት አንጻርም ‘የበረዶ ደሴት’ የሚል ስያሜን ይዞ በአካባቢው ከ30 አመታት በላይ ቆይታ አድርጓል። የበረዶ ግግሩ ‘የለንደን’ መጠነ ሥፋት ከሁለት እጥፍ በላይ … Read moreContinue Reading
  • በጎብኝዎች የተወደዱ ምርጥ ሀገራት
    የተባበሩት መንግስታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት (UNWTO) ከሚሰራቸው ስራዎች ውስጥ አንዱ የቱሪዝም መረጃዎችን ይፋ ማድረግ ነው፡፡ በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ቱሪዝም ላይ ወቅታዊ ትንታኔዎችን ይሰጣል፡፡ በዓመት አራት ጊዜ የሚታተም የቱሪስት ፍሰት መረጃን ያወጣል፡፡ ተቋሙ በያዝነው የፈረንጆች 2023፤ ከጥር እስከ ሐምሌ ያለውን የሀገራትን የቱሪዝም ፍሰት እ.ኤ.አ.ከ 2019 ጋር በማነጻጸር ይፋ አድርጓል፡፡ ቀዳሚዎቹ ሀገራት … Read moreContinue Reading
  • የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጂቢ ኒውስ በተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ በጋዜጠኛነት ተቀጠሩ
    ጆንሰን በቴሌቪዥን ጣቢያው የፕሮግራም አቅራቢ፣ አዘጋጅና ተንታኝ ይሆናሉ። በቀጣይ ዓመት የአሜሪካና የዩኬ ምርጫ በመዘገብ “ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ” ተብሏል። “የእንግሊዝን ኃይል የሚያሳይ መሰናዶ” ያቀርባሉም ብሏል ጂኒ ኒውስ። በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዩች ምልከታቸውን ለማጋራት ቃል ገብተዋል። በዴይሊ ሜይል ላይም አምደኛ የሆኑት ቦሪስ ጆንሰን ሥራቸውን በአውሮፓውያኑ አዲስ ዓመት ይጀምራሉ። ቦሪስ ጆንሰን በኤክስ ገጻቸው ላይ … Read moreContinue Reading
  • ባለቅኔና ሠዓሊ ገብረክርስቶስ ደስታ
    ከ92 ዓመታት በፊት ጥቅምት 5 ቀን 1924 ዓ.ም የሀገራችን ብርቅዬ ሁለገብ የጥበብ ሰው ሠዓሊና ባለቅኔ ገብረክርስቶስ ደስታ የተወለደበት ቀን ነው። በኢትዮጵያ ዘመናዊ የስነ ጥበብ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ የነበረው ሠዓሊና ባለቅኔ ገብረክርስቶስ ደስታ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የስነጥበብ ህዋ ላይ በተለይም አብስትራክት የተሰኘውን እና ዘመናዊ የስዕል አሰራር ስልት በስፋት ከማስተዋወቅ በላይ የራሱ … Read moreContinue Reading
  • የቀበሌ 14 ተጫዋቾችን 90 ደቂቃ ብቻ አጫውቶ የተበጫጨቀው ታኬታ አስገራሚው ሪፖርት
    ጥር 12 ቀን 1980 በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመ እንደሆነ ተገለጾ የታተመው መረጃ 3800 ብር የፈጀ የቀበሌ 14 እግር ኳስ ቡድን ተጨዋቾች ጫማ ከዘጠና ደቂቃ ጨዋታ በሁዋላ ሙሉ በሙሉ ነትቦ በመበጫጨቁ የቀረበው ሪፖርት ጉድ የሚያሰኝ ነው። የዛሬዎቹን የከነማና የመንግስት ተቋማት ክለቦች ዝርፊያ ላየ ጉዳይ አስቂኝ ሳይሆን አሳዛኝም ነው። ወይ ዘመን!! ይህን … Read moreContinue Reading

Leave a Reply