Site icon ETHIO12.COM

ኦርቶዶክስን ለሁለት ለመክፈል የተዝጋጀ ዕቅድ መኖሩን ፓርትሪያርኩ “ህዝብ ይስማ” ሲሉ ይፋ አደረጉ

” ሁሉም መንገድ ተሞክሮ ባለመሳካቱ በሃይማኖት የተሸሸገና በዕምነት ውስጥ በተቀመረ ሴራ አገሪቱን ለማበጣበጥ እየተሰራ ያለውን ደባ ያሳያል የሚል ዕምነት እንዳላቸው በመግልጽ ወዳጆች የላኩልኝን ማሰረጃ ልኬያለሁ። ይህን ይፋ ማድርጋቸው ነገ ፓትሪያርኩ ላይ ዘመቻና ውግዘት እንደሚጀመር ጥርጥር የለውም። ህዝብ ያስተውል ዘንድ ይህንን አሰራጩልኝ” በሚል በተላከልን መሰረት ቪዲዮው የተጭበረበር አለመሆኑንን አጣርተን አትመነዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቤተ ክርስቲያንን ለሁለት የመክፈል እቅድ የተዘጋጀበት ሰነድ መገኘቱን ” ባልናገር ሃላፊነቱ የኔ ብቻ ነው፣ ህዝብ እንዲያውቅ ተናግሬያለሁ። ሃላፊነቱ የሁላችንም ነው” ሲሉ ማህበረ ቅዱሳንን ተጠያቂ አደረጉ።

በቪዲዮ በተሰማው መልዕክታቸው ፓትሪያርኩ እንዳሉት አሳቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ባይሳካም በውጭ አገር ሌላ የኦርቶዶክስ ተውህዶ ቤተክርስቲያን ለማቋቋም ዕቅድ መያዙንም አመልክተዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው የፓትሪያርኩ ንግግር

“ህገወጥ ሃብት ይሰበስባሉ” ሲሉ የማህበረ ቅዱሳንን የከሰሱት ፓትሪያርኩ፣ ከቤተክርስቲያን ገንዘብ መልሰው ስጦታ በመስጠት ማስታወቂያ ያሰራሉ” ሲሉም አስረግጠው ወቅሰዋል።

አንድ ድርጅት ለአንድ ሚዲያ ማስታወቂያ እንዲሰራለት ሲልክ ገንዘብ እንደሚከፍልና በከፍለው ልክ ምርቱ እንደሚገንለት ያመለውከቱት ፓርቲያርኩ፣ ማህበረ ቅዱሳንም የራሳቸው ባለሆን፣ ግብርና ቀረጥ ከማይከፍሉበት፣ ህገወጥ ገቢያቸው ላይ ስጦታ የሚያበረከቱት ልክ እንደ ሚዲያው ማስታወቂያ ለመስራትና ለማሰራት እንደሆነ አመልክተዋል።

የቤተክርስቲያንን ሃብት መልሰው ለቤተ ክርስቲያን እንደሚመጸውቱ ያመልከቱት ብፁዕ አቡነ ማትያስ” እኔ የማውቀው አንድ ቤተክርስቲያን ነው” ሲሉ ድርጊቱን ለሲኖዶሱ ሲያቀርቡ ሲጨበጨብላቸው ከቪዲዮው ይሰማል። በዚህ ጉዳይ ላይ ማንህበረ ቅዱሳን ምን አቋም እንዳለው እስካሁን የሰጠው ማስተባበያ የለም።

ማህበረ ቅዱሳን ሰፊ አባላት ያሉትና ራሱን እንዴትና በምን መንፈሳዊ ሂሳብ ” የቅዱሳን ማህበር” ሲል ሊጠራው እንደቻለ በተደጋጋሚ ትችት የሚቀርበበት፣ ቤተ ክርስቲያን እያለች ተደራቡ ምን ዓይነት ሃዋሪያዊ ተልዕኮ እንደሚያራምድ የዕምነቱ ተከታዮች ጠንቀቀው የማይረዱት ተቋም እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚነገርበት ተቋም ነው። ሰፊ የሆነ የቤተ ክርስቲያኒሯን ሃብትም በምን አግባብ ሊያስተዳድርና ባለቤት ሊሆን እንደቻለ ለበርካቶች ግልጽ አይደለም።

Exit mobile version