Site icon ETHIO12.COM

“የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ ጥያቄ በዋለ ባደረ ቁጥር ለሐሰት ፕሮፖጋንዳ እየተጋለጠ ነው”

“የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ ጥያቄ በዋለ ባደረ ቁጥር ለሐሰት ፕሮፖጋንዳ እየተጋለጠ ነው” በማለት ነዋሪዎች ጥያቄያቸውን በሰላማዊ ሰልፍ አስታወቁ። “የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ከፍ ሲል ኢትዮጵያዊ ዝቅ ሲል አማራ ነዉ” ሲሉ ኮኔሬል ደመቀ ዘዉዱ ተናገሩ። ላለፉት ሶስት ዓመታት ያለበጀት መኖራቸውን አንስተው ቅሬታቸውንም ገልጸዋል።

አሚኮ እንዳለው በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ሁመራ እና ማይካድራ ከተሞች ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል። ሰልፈኞቹ የወልቃይት እና የራያ አማራ ማንነት ጥያቄን የርእስት ማስመለስ ስም በመስጠት ወደ ኋላ መመለስ አይቻልም፣ ሀገር ርእስት ነዉ፣ ለርእስት መሞት ደግሞ ክብር ነዉ ብለዋል። በበጀት ክልከላ የሚጣል ማንነት፣ በፈተና ብዛት የሚዝል አማራነት የለም ሲሉም አስገንዝበዋል።

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ ማለፊያዉ ለሰልፈኞቹ ባስተላለፉት መልእክት የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ አሁናዊ ኹኔታዉ ፈተና ያለበት መኾኑን ተናግረዋል። በተለይም ለረጂም ጊዜ የማንነት ጥያቄው መልስ ያልተሰጠው፣ በጀት እስካሁን ያልተለቀቀለት እንዲሁም በአካባቢዉ የፍትሕ ሥርዓት ያልተዘረጋለት መኾኑን አንስተዋል። እነዚህን መሰል ችግሮች እንዲፈቱም ጠይቀዋል።

በሰልፉ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ እና የሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ከፍ ሲል ኢትዮጵያዊ ዝቅ ሲል አማራ ነዉ፤ የሕዝቡ የወሰን እና የማንነት ጥያቄም በተገቢዉ መልኩ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ ጥያቄ በዋለ ባደረ ቁጥር ለሐሰት ፕሮፖጋንዳ፣ ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት አድሏዊ ፍርድ እየተጋለጠ መሆኑንም አንስተዋል። እንደ ኢትዮጵያዊነታችን በጀት፣ እንደ አማራነታችን ደግሞ ማንነታዊ እውቅና እንዲሰጥ በዚህ ሰልፍ እጠይቃለሁ ብለዋል።
በሰልፉ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የከተማ አሥተዳደሮች እንዲሁም የዞን የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ:- አዲስ አለማየሁ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

“መንግሥት ለማንነት ጥያቄያችን መልስ ሊሰጠን ይገባል” የአደባይ ከተማ ነዋሪዎች

ሁመራ: ግንቦት 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ከተካሄደባቸው ከተሞች መካከል አንዷ የአደባይ ከተማ ናት።

የአደባይ ከተማ ነዋሪዎች በህወሃት የአገዛዝ ዘመን ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ የአካባቢያችንን ጸጋ ተጠቅመን እንዳናለማ፣ ሃብትና ንብረት እንዳናፈራ ከመደረጉም በላይ በአባቶቻችን ርስት እንደ ባይተዋር ተቆጥረን ተጨፍጭፈናል፤ ባህልና ወጋችን እንዲጠፋ ተደርጓል፤ ስደትና መፈናቀል ተፈጽሞብናል ብለዋል።

ከነጻነት ማግሥት የአካባቢያችንን መሠረተ ልማት ያለ መንግሥት በጀት ከራሳችን በማውጣት አካባቢያችን እያለማን ቆይተናል ብለዋል። የዞኑ ሕዝብ ለሦስት ዓመታት ያለ በጀት ተቀምጧል፤ የማንነት ጥያቄውም ምላሽ እንዳያገኝ በዝምታ ታልፏል፤ መንግሥት አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጠን ይገባል ሲሉ በሰልፉ ላይ ጠይቀዋል።

Exit mobile version