Site icon ETHIO12.COM

“በትግራይ በምግብ እጥረት ህጻናት እየሞቱ ነው፤ ረሃብ ተባብሷል

© UNICEF/Christine Nesbitt A woman brings her child to a clinic in Wajirat in Southern Tigray in Ethiopia to be checked for malnutrition.

በትግራይ በባለፉት አምስት ወራት በምግብ እጥረት 13 ህጻናት መሞታቸውን የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ለቢቢሲ ተናግሯል።

በመቀለ በሚገኘው የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ገብተው ህክምና ሲደረግላቸው ከነበሩት መካከል በግንቦት ወር ብቻ ሰባት ህጻናት ህይወታቸው ማለፉንም የህክምና ባለሙያዎች ገልጸዋል።

የሆስፒታሉ የህጻናት ህክምና ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ስምረት ንጉሴ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ባለፉት 12 ወራት ውስጥ በሆስፒታሉ ከመጡ ህጻናት መካከል ሶስቱ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ህይወታቸው ማለፉን ገልጸዋል።

በትግራይ ክልል በተራዘመ በምግብ እጦት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረና ረሃቡ በከፍኛ ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱ ተገለጸ፡፡ ከመቀሌ 40 ኪሎ ሜትር በስተደቡብ በምትገኘው ሳምር ወረዳ ብቻ ባለፉት አራት ወራት 25 ሰዎች የሞቱ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት 670 ሕፃናት በአሥጊ ሁኔታ ላይ መሆናቸውም ተጠቁሟል፡፡

ሪፖርተር

ነገር ግን ከጥር ወር ጀምሮ ሁኔታው ተባብሶ በምግብ ዕጥረት የሚሞቱ ህጻናት ቁጥር እየጨመረና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ለቢቢሲ ገልጸዋል።

“ከጥር ወር ጀምሮ 13 ህጻናት በምግብ ዕጥረት ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ከነዚህም መካከል ሰባቱ የሞቱት በግንቦት ወር ነው” ሲሉም ዶክተር ስምረት ይናገራሉ።

በተለይም ከሚያዝያ ወር ጀምሮ ወደ ሆስፒታሉ የሚገቡ ህጻናት ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ከሆስፒታሉ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ከነዚህም ውስጥ 32 ህጻናት በጣም አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን በጽኑ ህክምና እንክብካቤ ማዕከልም ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛሉ።

አብዛኛዎቹ ህሙማን ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ እና ከሁለት ዓመት በፊት የተከሰተውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ተከትሎ ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ህጻናት መሆናቸውንም የህክምና ባለሙያዋ ያስረዳሉ።

“በሆስፒታሉ ተኝተው እየታከሙ ያሉ ህጻናት የደከሙና ከሆስታሉ ውጭ በምግብ እርዳታ ማገገም የማይችሉ ታካሚዎች ናቸው” ብለዋል የህክምና ባለሙያዋ።

በትግራይ ያለው መሰረታዊ የመድኃኒት እና የህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ከሚያስፈልገው አንጻር እዚህ ግባ የሚባል እንዳልሆነና ለህፃናት የሚሆኑ አልሚ ምግቦችና መድኃኒትም እጥረት እንዳለም ያስረዳሉ።

በተለይም አለም አቀፍ የረድዔት ድርጅቶች በትግራይ ክልል የሚያደርጉትን የምግብ እርዳታ ማቆማቸውንም ተከትሎ ሁኔታው መክፋቱንም ነው ባለሙያዋ የሚያስረዱት።

“ረድዔት ድርጅቶቹ የህይወት አድን እርዳታቸውን ማቋረጣቸው በተለይም ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ህጻናት እና እናቶችን በእጅጉ ጎድቷል። የተቋረጠበት መንገድ ትክክል አይደለም” ሲሉም ለቢቢሲ አስረድተዋል።

የተባበሩት መንግስታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም እና የአሜሪካ መንግሥት የዓለም አቀፍ ልማት ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤአይዲ በጦርነቱ በከፋ ለተጎዳችው ትግራይ የሚያቀርቡትን እርዳታ ባለፈው ወር አቋርጠዋል። የረድዔት ድርጅቶቹ እርዳታው በትግራይ በረሃብ ለተጎዱ ሰዎች ሳይሆን ከታለመለት ዓላማ ውጭ ገበያ ላይ ሽያጭ መቅረቡን እንዲሁም ስርቆት ተፈጽሟል በሚል ለጊዜው አቋርጠዋል።

ጦርነቱ ከተቀሰቀበት ጊዜ አንስቶም በሺህ የሚቆጠሩ ህጻናት ለከፋ የምግብ እጥረት ተዳርገዋል።

ከሐምሌ 2013 እስከ ሐምሌ 2014 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ240 ሺህ በላይ የሚሆኑ የትግራይ ህጻናት በምግብ ዕጥረት እየተሰቃዩ እንደሆነ ከነዚህም ውስጥ 76 ሺህ ህጻናት በከፋ የምግብ ዕጥረት ምክንያት እየተሰቃዩ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ። አኃዞቹ በባለፉት ሁለት ዓመታት በምግብ እጥረት የሞቱ ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ጨቅላዎች ጦርነቱ ከመጀመሩ አራት ወራት በፊት ከነበረው በሚያስደነግጥ ሁኔታ በ1 ሺህ 533 በመቶ እንደጨመሩ ያሳያሉ።

ቢቢሲ ከትግራይ ትግራይ ጤና ቢሮ መረጃ ባገኘው መረጃ መሰረት ከሐምሌ 2013- ሐምሌ 2014 ዓ.ም ድረስ 2 ሺህ 450 ሕጻናት በሆስፒታል ውስጥ ሞተዋል።

አኃዙ መሬት ላይ ያለውን ዕውነተኛ ገጽታ በጭራሽ እንደማያሳይና ከዚህም የከፋ እንደሆነም ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት የረድዔት ድርጅቶች በክልሉ የሚያደርጉትን ዕርዳታ ማቋረጣቸውን ተከትሎም እርዳታ የሚሹ ሚሊዮኖችን ህይወት ስጋት ላይ ጥሎታል።

ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ወይም ኤምኤስኤፍ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ተቋም ሶስት አራተኛ በሚሆኑት በትግራይ ክልል በሚገኙ የሕክምና ተቋማት ላይ ሆን ተብሎ መጠነ ሰፊ ዘረፋ እና ውድመት መፈጸሙን በ2013 አጋማሽ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።

ከሁለት ዓመት በፊት ተከስቶ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎችን የቀጠፈውን ደም አፋሳሽ ጦርነት በሰላም ለመቋጨት በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል የሰላም ስምምነት ከሰባት ወራት በፊት መደረሱ ይታወቃል።

የሰላም ስምምነት መሠረት ለትግራይ ያልተገደበና ያልተቆራረጠ ሰብዓዊ እርዳታ፣ በትግራይ ለሁለት ዓመት የተቋረጠው መጀረታዊ አገልግሎት እንዲመለስ እንዲሁም የትግራይ ኃይሎች ትጥቃቸውን በመፍታት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት እንዲሰፍን ለማድረግ ያለመ ነው።

BBC Amharic

Exit mobile version