Site icon ETHIO12.COM

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን የ7 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን የሰባት ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ያደረገው በምክንያት መሆኑን አስታወቀ። የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሮናልድ ኮቢያ “የአውሮፓ ህብረት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑን በአንክሮ ሲመለከተው የነበረና በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የሚያግዝ መሆኑን በመገንዘብ ድጋፍ አድርገናል” ሲሉ ተደምጠዋል።

ዘረኘትን የሚያበረታታውንና የአገሪቱን አንድነት አደጋ ላይ የጣለውን ህገ መንግስት እስከ ማሻሻል የሚደርስ ስልጣን የተሰጠው ይህ የምክክር ኮሚሽን ሲቋቋም ቀድሞ የተቃወመውና የማጥላላት ዘመቻ የከፈተበት ትህነግ እንደነበር ይታወሳል። ትህነግ ኮሚሽኑን አሃዳዊያንን ሊመልስ የተቋቋመ ሲለውም ነበር።

ትህነግን ተከትለው አሁን ድረስ ኮሚሽኑ ላይ ዘመቻ የሚያቀናብሩ የመኖራቸውን ያህል አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት ሙሉ ድጋፍ እንዳላቸው ሲያስታውቁ ይህ የመጀመሪያ አይድለም። ዛሬ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን የ7 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ያደረገው የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽኑን በአንክሮ ሲከታተል እንደቆየ ማስታወቁ ለኮሚሽኑንን ውሎ አድሮ ተቀባይነት ማደግ ማሳያ ሆኖ ተወስዷል።

የድጋፍ ስምምነቱ የተደረገው የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው በተገኙበት የኢትዮጵያ የብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) እና በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ መፈረሙን የመንግስት መገናኛዎች ናቸው ያመለከቱት።

ህብረቱ ድጋፉን ያደረገው ኮሚሽኑ እያከናወነ ያለው ብሔራዊ ምክክር በውጤት እንዲጠናቀቅ ለመደገፍ ነው።የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ሰመሪታ ሰዋሰው በስምምነቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር፥ የተደረገው ድጋፍ ኮሚሽኑ በቀጣይ ለሚሰራቸው ስራዎች ያግዛል ብለዋል፡፡ ኮሚሽኑ ወደፊት እንዲጓዝ ሌሎች የአውሮፓ አባል ሀገራት ድጋፋቸውን ሊያጠናክሩ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) በበኩላቸው፥ ኮሚሽኑ አስፈላጊ ስራዎችን አጠናቆ ምክክር ለማድረግ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

የኮሚሽኑ ስራ የተቃና እንዲሆን ከመንግስትና ከኢትዮጵያ ወዳጆች ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው የተደረገው ድጋፍ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንደሚያግዝ ጠቅሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሮናልድ ኮቢያ፥ የአውሮፓ ህብረት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑን በአንክሮ ሲመለከተው የነበረና በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የሚያግዝ መሆኑን በመገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አስረድተዋል። ስምምነቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራትና የዓለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮች በተገኙበት ነው የተፈረመው።

በቅድስት አባተ

Exit mobile version