Site icon ETHIO12.COM

ትህነግ መከላከያ ላይ ክህደት ፈጽሞ የለኮሰው ጦርነት መከራ ከትግራይ እየተሰማ ነው

ራሱን “የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር” ሲል የሚጠራውና አሁን ድረስ ” የመገንጠል ዓላማችንን አልተውንም” የሚለው ድርጅት በክህደት የኢትዮጵያ መከላከያን አርዶ የለኮሰው ጦርነት ከሁለት ዓመት በሁዋላ መቆሙ ይታወሳል። ጦርነቱ ቢቆምም የጦርነቱ ጣጣና መከራ ተሸካሚ የሆኑት ድምጻቸውን በተለያዩ አጋጣሚዎች እየገለጹ ነው። ትህነግ የትግራይን ህዝብ ተገን አድርጎና ዙሪያውን ጠላት አበጅቶለት ያደረሰበት መከራ ውሎ አድሮ ይፋ እንደሚሆን ቀደም ሲል እንድተባለው የአሁኑ ገና ጅማሬ መሆኑ አመልካች ነው።

“በትግራይ ወጣቱን ቀስቅሰው ለጦርነት የማገዱ ለህግ መቅረብ አለባቸው” የሚሉ ወገኖች ” በትግራይ ምንም እንዳልተፈጠረ በማስመሰል በየቡናቤቱና ሆቴሎች ቢራ መጋት መጀመሩ አሳዛኝ ነው” ሲሉ የሞራል ጥያቄ የሚያነሱም አሉ። በጦርነቱ ወቅትና ከጦርነቱ በፊት ህዝቡን ሲያቀጣጥሉ የነበሩ፣ ዛሬ ተመስልሰው ያስፈጁትን ህዝብ ያለ አንዳች ሃፍረት መምርታቸውና ሚዲያ ላይ ወጥተው አፋቸውን ሞልተው ሌላ ሰው ሁነው መቅረባቸው አሳፋሪ እንደሆነ የሚናገሩት ክፍሎች ” ፍትህ ሊሰፍን፣ ህዝብ ያስጨረሱ ለፍርድ ሊቀርቡ ግድ ነው” የሚል አሳብ እያነሱ ነው።

በጦርነቱ ወቅት የፕሮፓጋንዳ አቀጣጣይ የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ መሪ የሆኑለት የትግራይ ሕዝብ ዛሬ ላይ የመከራና የስቃይ ድምጽ እያሰማ መሆኑንን የተለያዩ የማህበራዊ ገጾችና ድረገጾች እንዲሁም በውጭ መንግስታት የሚደጎሙና የተደራጁ ሚዲያዎች ነው እያስታወቁ ያሉት።

በትግራይ የከፋ ረሃብ መኖሩን ጨምሮ የመብት ጥሰት፣ የማህበራዊ ዋስትና ጥያቄ፣ የመለሶ መስፈር ተፈናቃዮች ሮሮና የተሃድሶ ጉዳይ በግንባር የሚጠቀሱ ጉዳዮች ሆነዋል። በተለይ የረሃብ አደጋን አስመልክቶ እየወጡ ያሉ መረጃዎች እርፈት የሚነሱ ናቸው። 1300 ሰዎች በረሃብ መሞታቸውን ሪፖርተር ያነጋገራቸው የስራ ሃላፊ አመልክተዋል።

በትግራይ ከተረጂዎች ጉሮሮ እየተነጠቀ የሚቸበቸበው የእርዳታ ዕህል ዝርፊያ ዜና ጎን ለጎን 1300 ሰዎች መሞታቸው ሲሰማ ” በትግራይ ምን እየሆነ ነው?” የሚል ጥያቄ እያስነሳ ነው። የሚዘርፉትም ሆነ የረሃብ ሞት ዜና የሚያሰሙት የትህነግ አመራሮች ናቸው። ወይም በትህነግ ስር ያሉ ናቸው። ይህ ሊጠራ የሚገባው ጉዳይ እንደሆነና የፌደራል መንግስት ጣልቅ ገብቶ ሊመረምረው፣ ኮሽ ባለበት ሁሉ እየሄዱ ለህገወጥ ጠብቃ የሚሆኑት የአገራችን የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ነን ባይ ተቋማትም እጅቻእውን በገሃድ ሊያስገቡበት የሚገባ ጉዳይ እንደሆነ በርካቶች አስተያየት እየሰጡ ነው። ከሁሉም በላይ ግን በትግራይ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ድርጅት አመራሮች አግባብ ያለው መረጃ ሊያቀርቡ እንደሚገባ የሚጠይቁ ጥቂት አይደሉም። በቂ ይሁን አይሁን ባይገለጽም የመንግስት መገናኛዎች ክልሉን ጠቅሰው የፌደራል መንግስት እርዳታ መጀመሩን ገልጸዋል።

የፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል አስቸኳይ የሰብዓዊ ዕርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የምግብ ድጋፍ እያቀረበ መሆኑን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ የቅድመ ዝግጅትና አስቸኳይ ግብረ-መልስ ዳይሬክተር ገ/እግዚአብሔር አረጋዊ እንዳሉት÷ ወደ ክልሉ የተላከው የምግብ እህል ድጋፉ ለሚያስፈልጋቸው በ17 ወረዳዎች ለሚገኙ ሰዎች ከትናንት ጀምሮ ተደራሽ እየተደረገ ነው፡፡ ድጋፉ ሩዝን ጨምሮ 28 ሺህ 132 ኩንታል የምግብ እህል እና 47 ሺህ 120 ሊትር የምግብ ዘይትን ያካተተ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡ እስከዚህ ወር መጨረሻም ድጋፉ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች መከፋፈሉ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡

ይህን ያህል የመረረ ጉዳይ እያለ፣ አዲሱ የትግራይ መሪ አቶ ጌታቸው “ትጥቅ አልፈታንም፣ መንግስት ወልቃይትን መልሶ ሊያስረክበን እየሰራ ነው፣ ሰፊ ወታደር እያደራጀን ነው…” የሚሉ መግለጫዎችን በትግርኛ መቀለብ ላይ አተኩረዋል። የንግግራቸውን ቅጂ በዋቢነት የሚያሰራጩ እንደሚሉት “አቶ ጌታቸው አሁንም እንደ ጦርነቱ ዘመን በፕሮፓጋንዳ መምራት የሚቻል መስሏቸዋል” ሲሉ እየተቿቸው ነው። ርሃብን ያክል ጉዳይ ታቅፈው “ለምን ትህነግ አሸንፎ ቤተመንግስት አልገባም” በሚል ላኮረፉ የትህነግ የውጭ ደጋፊዎችና ሰላማዊ ሰልፍ አድማቂዎች ደስታ የሚሰጥ ዜና ለማብሰር አቶ ጌታቸው መላላጣቸውን ብዙዎች አልወደዱላቸውም።

“በትግራይና አማራ ህዝብ መካከል ቀድሞውኑ ትህነግ የጀመረው ቆሻሻ ፖለቲካ እንዳከሰረው አውቆ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማዳበር፣ ታላቅ የይቅርታ ኮንፍረንስ በማዘጋጀት በገሃድ ያስፈጁትንና የፈጁትን የአማራ ህዝብ ይቅርታ በመጠየቅ ሰላም ማውረድ ቀዳሚ ተግባር መሆን ሲገባ፣ አቶ ጌታቸው በመንግስትና በአማራ ህዝብ መካከል ልዩነት ለመፍጠር የዶለዶመ የካድሬ ምላሳቸውን ስለው እዛና እዚህ የተለያየ ነገር መናገራቸው ለትግራይ ህዝብ የዛሬ ጥያቄ ምንም አይፈይድም” የሚሉ ወገኖች የትግራይ ተወላጆች በዚህ መልኩ ሊያስቡ እንደሚገባ ጠቁመዋል። ቅድሚያ ምን መሰራት እንደሚገባም ሊለዩ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ትህነግ የለኮሰውና በወረራ አፋርና አማራ ክልል ላይ ያሰፈረው ሃይሉ ለጊዜው ቁጥሩ ባይታወቅም ክፉኛ ተመቶበት፣ በሽንፈት ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ የሰላም ስምምነት ለመፈረም መገደዱ ይታወሳል። ይህ ስምምነት በአፍቃሪዎቹ ሳይቀር “ሽንፈት የወለውደው” በሚል ክፉኛ ስድብ እንዲወርድበት አድርጎታል።

ይህ በመርዛማ ፕሮፓጋንዳና በማይጨበጥ የስልጣን ጥማት ቅስቀሳ የታጀበ ደም አፋሳሽ ጦርነትን በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሠረት ሲቆጭ በተደረሰው ስምምነት መሰረት የትጥቅ የማስፈታትና የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ መጡበት ማኅበረሰብ የመመለስ ስራ ተጀምሯል። ይህንኑ አስመልክቶ የክልሉ ምክትል ሊቀመንበት የቀድሞ ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ሃምሳ ሺህ የሚሆኑ የትህነግ ምልምል ታጣቂዎች በመልሶ መቋቋም ሂደት ወደ በኤተሰቦቻቸው መቀላቀላቸውን አስታውቀዋል። በቀጣይ ስራው እንደሚቀጥልም አመልክተዋል። ይህን ተከትሎ “መልሶ የማቋቋም ሒደት ውስጥ አልተካተትንም” ያሉ አካል ጉዳተኛ ታጣቂዎች “እኛን ወደ በረንዳ፣ እናንተ ወደ ውስኪ ቤት” እያሉ የተቃውሞ ድምጽ ሲያሰሙ የሚያሳይ ቪዲዮ ይፋ ሆኗል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንትና የሰላምና ፀጥታ ካቢኔ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ሌተና ጄኔራል ታደሰ ወረደ፣ ከ50 ሺሕ በላይ ታጣቂዎች በመልሶ ማቋቋሙ ትግበራ መሰረት በክብር መሸኘታቸውን ለትግራይ ክልል ሚዲያ በገለጹ አንድ ቀን በሁዋላ ነው።

“ስንብቱን ተግባራዊ ያደረግነው ለሰላም ብለን ሲሆን፣ ይህም የሆነው በሠራዊቱ ውስጥ ከሚቀጥሉትና  ከሚሰናበቱት ጋር ተነጋግረን መግባባት ላይ ከደረስን በኋላ ነው፤” ማለታቸውን የትግራይ ሚዲያን ጠቅሰው በማህበራዊ ገጻቸው አስፍረዋል። እሳቸው ይህን ቢሉም ከዚህ በፊት ከሠራዊቱ የተቀነሱ አካል ጉዳተኞች “የተሰናበትነው በተገቢው መንገድ ሕጋዊ ወረቀት ሳይሰጠን ነው”  የሚል መቃወሚያ አቀበዋል።

ሌተና ጄኔራል ታደሰ፣ ከ50 ሺሕ በላይ ተዋጊዎችን በክብር የማሰናበት ሥራ እንጂ የመልሶ ማቋቋሙ ስራ ገና እንዳልተጀመረ አመልክተዋል። ይህንኑ ሂደት የሚመሩት አቶ ተሾመ ቶጋ ለጋሽ አገራት ድጋፍ እንዲያደርጉ መማጸናቸውም ይታወሳል። ትግራይ ከበጀት በላይ ከፍተኛ የሆነ የሰራዊት ሃይል መግነባቷን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስይትር አብይ ” በጀታችሁን ለሚሊሻ ቀለብ እያዋላችሁ ፌደራል መንግስቱ በጀት አሳነሰ አትበሉ” ሲል አስቀድመው ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

አካላቸው ላይ በደረሰ ጉዳት ከትግራይ በሰራዊት አባልነት መቀጠል እንደማይችሉ ተገልጾላቸው የተሰናበቱ ‹‹የታገልንበት መብታችን ይከበር፣ ድምፃችን ይሰማ፤…›› ብለዋል።” የታገልንበት መብታችን” ሲሉ የጠየቁት መብት ምን እንደሆነ ግን አልተብራራም። ወይም ምን የሚል ቃል አስቀድሞ እንደተገባላቸው ይፋ አላደረጉም። በደፈናው ግን ከፕሪቶሪያው ስምምነት ውጭ በመሆነ የመቋቋሚያ ሊያገኙ እንደማይችሉ ነው ያመልከቱት።

ይህንን ማስፈንጠሪያ ethio12news ተጭነው በቴሌግራም ገጻችን ይከተሉን

Exit mobile version