Site icon ETHIO12.COM

“ኢሳያስ አፉወርቂ ከአማራ ክልል ግጭት ጀርባ ተዋናይ ናቸው”

ኤርትራን በብቸኝነት እየመሩ ያሉት ኢሳያስ አፉወርቂ ከአማራ ክልል ጦርነት ጀርባ እንዳሉና በተቀነባበረ ዝግጅት እንደሚመሩት መረጃ ያላቸው አመለከቱ። ምንም እንኳን ውስጥ ውስጡን ጉዳዩ ቢሰማም ዜናውን የነገሩን እንዳሉት መንግስት ከውጥን እስከ መጨረሻው ጦርነት ያለውን ሂደት በበቂ መረጃ እንደሚያውቀው አመልክተዋል።

“ኢሳያስ አፉወርቂ ከአማራ ክልል ግጭት ጀርባ ተዋናይ ናቸው” ያሉት ወገኖች ኢሳያስ ወደዚህ ውሳኔ የደረሱት ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጦር በመገንባቷና የባህር ሃይል በማደረጃቷ ሳቢያ ስጋት ገብቷቸው እደሆነ አመልክተዋል። ሲያስረዱም ትህነግ ለኢሳያስ ከፍተኛ ስጋት በመሆኑና ቂምም ስላለባቸው ጦርነቱን ተንደርድረው የተቀላቀሉት ከራሳቸው ፍላጎት አንሳር እንደሆነ አስረድተዋል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ጦርነቱን እየመከተች ሰፊ ሃይል መገንባቷ ” ተረኛው እኔ ነኝ” የሚል ስጋት እንዳደረባቸው በተለያዩ አጋጣሚዎች በወታደራዊ መኮንኖች ስብሰባ ላይ መነሳቱን ገልጸዋል።

ኢሳያስ አፉወርቂ “ግዙፍ ሰራዊት አያስፈልጋችሁም” በሚል ኤርትራ በትብብርና በክፍያ ሰራዊት ለኢትዮጵያ ልታሰማራ የምትችልበትን አግባብ እንደ አሳብ አቅርበው እንደነበር ያመለከቱት የዜና ሰዎች፣ በኢትዮጵያ በኩል እሳቸው በፈለጉት ደረጃ ምላሽ አለማግኘታቸው ደስ አላሰኛቸውም። እንደውም በስለላ በኩል ሲሰሩ የነበሩትን በሙሉ መንግስት ” በቃችሁ” ብሎ ማሰናበቱ ኢሳያስን ክፉኛ አበሳችቷል።

በኤርትራና ትህነግ የተባበረ ሴራ የኢትዮጵያ ጦር፣ ባህር ሃይና አየርን ጨምሮ እንዲፈርስ መደረጉን በማስታወስ ” ኢትዮጵያ የጦር ሃይሏ ከፈራረሰ ወዲህ በዚህ መልኩ ስታደራጀው ከሶስት አስርት ዓመት በሁዋላ ይህ የአሁኑ ሲሆን ኢሳያስ አፉወርቂ ይህ ሃይል ዳግም እንዲፈርስ ፋልጎት እንዳላቸው አስመራ ደርሶ የተመለሰ ነግሮናል” ሲሉ ስምና አድራሻ ሳይገልጹ የዜናው ሰዎች ከሁነኛ የመረጃ ሰዎች መስማታቸውን አመልክተዋል። በዚሁ መነሻ በርካታ ወጣቶችን በሳዋ ማሰልጠኛ አብቅተው ማስታጠቃቸውን ገልጸዋል።

“መንግስት የቪዲዮና የሰው ማስረጃ አለው” የሚሉት ወገኖች ኢሳያስ አማራ ክልል ያለው ጦርነት ከጦፈና እሳቸው ባሰቡት መልኩ ከተካረረ ኢትዮጵያ ወደ እርስ በርስ ጦርነት ስለምትሸጋገር ስጋታቸው ሁሉ ዜሮ እንደሚሆን ማስላታቸውን ይገልጻሉ።

“መንግስት ከትህነግ ጋር በሰላም ጦርነቱን ማብቃቱን በይፋ የተቃወሙትና ከኢትዮጵያዊያን በላይ ኢትዮጵያዊ ተደርገው ባዘጋጇቸው ሚዲያዎች ቀድመው ቅሰቀሳ አድርገዋል” ሲሉ አካሄዱን የሚያስረዱት የዜናው ባለቤቶች፣ ” ከዚህ ከሳቸው መግለጫዎች ማግስት ጦር ሜዳ ዘምተው ለመከላከያ ድጋፍ ሲሰጡ የነበሩ በሚገርም ፍጥነት የሰላም ስምምነቱን በመቃወም ሌላ ኢሳያስ ሆነዋል። ይህ አካሄዳቸው ቀድሞም መከላከያን ሲያበረታቱ የነበሩት ሻዕቢያ ትህነግን ለማጥፋት ከነበረው የቆየ ፍላጎት መነሻ መሆኑንን ያሳያል” ብለዋል።

ሻዕቢያ በገሃድ ” ፋኖን እደግፋለሁ” በሚል በትህነግ ወረራ ወቅት ማስታወቁን የሚገልጹ እንዳሉት፣ ኢሳያስ በወቅቱ መከላከያ ሲከዳና ሲታረድ ያደረጉትን መልካም ድጋፍ አወድሰው፣ ” አሁን ጊዜው ተቀይሯል። እንደ ቀድሞው በሴራ ኢትዮጵያን ለማተራመስ መሞከር አይጠቅምም፤ ብዙ ረቀት አያስኬድም። ለኤርትራም ህዝብ አዋጪ አይደለም” ሲሉ ምክር ለግሰዋል።

ኢትዮጵያ ሰፊ መከላከያ፣ ዘመናዊ መሳሪያና ቴክኖሎጂ መታጠቋን የሚገልጹት ክፍሎች መንግስት በኤርትራ መሪዎች ዘንዳ እየተፈጸመ ያለውን ክህደትና ሴራ በመረጃ አስደግፎ ለኤርትራና ኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ማስታወቅ እንደሚገባው አሳስበዋል።

ሻዕቢያ ኢትዮጵያ ቀይ ባህር ፖለቲካ ላይ አቋሟን እንደምትቀይር አሰቅድሞ ያውቅ ስለነበር ኢትዮጵያን ለማተራመስ ሌት ተቀን እንደሚሰራ መረጃ እንዳለ ያመለከቱት ወገኖች፣ ኤርትራዊያንም ይህን አካሄድ በይፋ ሊቃወሙ እንደሚገባ ገልጸዋል። ለዚህም ይመስላል አስቀድመው መግለጫ ማውጣት የመረጡት።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በደፈናው ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ ተገላ መኖር እንደማይገባትና ከአሁን በሁዋላ እንደ ቀድሞው በተቆለፈ ቤት መኖር እንዳዛላት ጠቅሰው ስለ ባህር በር አስፈላጊነት ሰሞኑን በገሃድ ማስታወቃቸው ይታወሳል። አሰብን እንደ አንድ አማራጭ አቅርበው በሰጥቶ መቀበል መርህ “መተንፈሻ እንፈልጋለን” ላሉት “በውሃ፣ በባሕር በር እና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ. . . የሚደረጉ ውይይቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታና ከልክ ያለፉ ሆነዋል” ሲል ኤርትራ አጭር መግለጫ አቅጥታለች።

ኤርትራ፣ ጂቡቲና ሶማሊላንድ በመጥቀስ ያለ አንዳች ግጭት ኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎቷን ለማሳካት እንደምትሰራ አብይ አህመድ ማስታወቃቸውን ተከትሎ ግልጽ ያልሆነ መግለጫ ያወጣው የኤርትራ መንግሥት፣ “ለእንዲህ አይነቱ ነገር እንግዳ ነኝ” ብሏል። ከባሕር በር ጋር በተያያዘ በሚካሄዱ ማናቸውን ንግግሮች ውስጥ እንደሌለበትና እንደማይሳተፍ አመልክቷል።

አብይ አህመድ ” እኔ በሁሉም ወሃ ጉዳይ ያገባኛል፤ አንተ ግን አያገባህም፣ አልነጋገርም ማለት አይቻልም። ያጣላናል። በቅርቡ 150 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ ተቆልፎበት ሊኖር አይችልም” ሲሉ ታሪክ፣ ዘርና ወይም አሰፋፈርንና ጂኦግራፊን አጣቅሰው መናገራቸው ይታወሳል።

የኤርትራ መንግሥት ግልጽ ባልሆነው መግለጫው እንደ ሁልጊዜው ወደ እንደዚህ ያሉ መድረኮች ተስቦ እንደማይገባ አረጋግጦ ጉዳዩ የሚያገባቸው ሁሉም የኤርትራ ተቆርቋሪዎች በዚህ ሁኔታ ቁጣቸው እንዳይቀሰቀስ ጥሪ አቅርቧል።


Exit mobile version