ኢሳያስ አፉወርቂ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ለሚተኩስ ማናቸውም ሃይል በራቸውን እንደዘጉ ማረጋገጫ ሰጡ

  • ኤርትራ ምድር ላይ ያሉ ኢመድበኛ ሃይሎች ጉዳይ ከዚህ ስምምነት በሁዋላ ያከትማል ተብሏል

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፉወርቂ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ቃታ ለሚስብም ሆነ ኢትዮጵያን ለሚያውክ ማናቸውም ሃይል ከለላም ሆነ ድጋፍ እንደማይሰጡ ሊታጠፍ በማይችል ደረጃ ማረጋገጫ መስጠታቸውን የኢትዮ12 የመረጃ መንጮች አመለከቱ። በውሳኔው በማረጋገጫው መሰረት ከኤርትራ የሚነሳ ማናቸውም ኢመደበኛ ሃይል በሩ ተዘግቶበታል።

ዜናውን ያጋሩን እንዳሉት ኤርትራን ከለላ ያደረጉና ቀደም ብለው እዛው ስልተና የወሰዱ ኢመድበኛ ሃይሎችን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የጦር አዛዦች ከኤርትራ የጦር አመራሮች ጋር ከተነጋገሩ በሁዋላ ዝርዝር ጉዳዮች ሲሰሩ ቆይተው መተማመን ላይ በመደረሱ እንደሆነ አመልክተዋል።

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በካይሮ ተገናኝተው ሲወያዩ በዚህ ጉዳይ ላይ ከመጨረሻ መግባባት ላይ መደረሱን የመረጃው ሰዎች አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ ኤርትራ ክስልል ዘልቀው የገቡት ሃይሎች ጉዳይና እጣ ፈንታ አስመልክቶ ዝርዝር አልተናገሩም።

በስም ያልጠቀሷቸው ኢመርደበኛ ሃይሎች ኤርትራ ምድር ላይ ሰልጥነውና ታጠቀው እንደሚንቀሳቀሱ የገለጹት እነዚህ ክፍሎች ” እዳልቸው በሰላማዊ መንገድ መንግስት ያቀረበውን አገራዊ ጥሪ መቀበል፣ ወይም ተላልፎ መሰጠት ነው” ብለዋል።

ከይፋዊ የመንግስት አካልም ሆነ መገናኛ ባይገለጽም ፣ኤርትራ ምድር ላይ ሆነው የተደራጁና የታጠቁ ሃይሎች ኢትዮጵያ ላይ ሲተኩሱ የፕሬዚዳንት ኢሳያስ መንግስት ዝምታ መምረጡ በሁለቱ ወዳጅ አገራት መካከል ግጭት ሊያስነሳ እንደሚችል ሲጠቆም ነበር።

መንግስትና የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በፕሪቶሪያ ያደረጉትን የሰላም አማራጭ ስምምነት አስመልክቶ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ቅሬታቸውንና ስጋታቸውን መግለጻቸው የሚታወስ ነው። ትህነግ ሙሉ በሙሉ መጥፋት እንዳለበት የሚያምኑት ኢሳያስ ከዚህ ውሳኔ በሁዋላ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የአካሄድ ልዩነት ማሳየታቸውም ሲሰማ ነበር።

መንግስት የልዩ ሃይልና የኢመደበኛ አደረጃጀትን ወደ ህጋዊ አግባብ ለመለስ ያደረገውን ጥሪና ተግባራዊ አፈጻጸም ተከትሎ አማራ ክልል ላይ “ሆነ ተብሎ የተፈጠረ ነው” በተባለ የመረጃ መዛባት የአላማራ ልዩ ሃይል ሙሉ በሙሉ ጥሪውን አልመቀበሉ መገለጹ ይታወሳል። ከካምፕ ወጥተውም መበተናቸው አይዘነጋም።

የአማራ ልዩ ሃይል ጥሪውን እንዳይቀበል ” መሳሪያ አስፈትተው ሊበትኑህ ነው” በሚል ሲቀሰቅሱ የነበሩና አሁን ድረስ ይህንኑ አቋም የሚያራምዱ ፕረኢዚዳንት ኢሳያስንና ኤርትራን ግልጽ ባልሆነ ጉዳይ ሲያሞግሱ መስማት የተለመደ ሆኖ ከርሟል። እንደውም አንዳንዶች ከኢትዮጵያ ይልቅ ኤርትራ ስጋት እንደገባት በመግለጽ ዜናና ማብራሪያ ሲሰጡ ይሰማል። በቃለ ምልልስ የኤርትራን የፖለቲካ አስፈጻሚዎች የኢትዮጵያን ሁኔታ ሲያስገመግሙ መስማት የእለት ተዕለት ጉዳይ ከሆነ ቆይቷል።

See also  አንዳንድ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ስለ ትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ያወጡት መረጃ የተዛባ ነው – ዶክተር ሙሉ

ይህ እየሆነ ባለበት ሁኔታ ነው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የኢትዮጵያ መከላከያ ላይ የሚተኩስና ኢትዮጵያን ለሚያውክ ሃይል ከአሁን በሁዋላ በራቸው ዝግ እንደሚሆን ማረጋገጫ የሰጡት። ፕሬዚዳንቱ በድንገት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱበት ዋና ምክንያት ምን እንደሆነ ለተጠየቁት ዜናውን የነገሩን ክፍሎች መልስ አልሰጡም።

በቅርቡ በኤርትራ ያሉ አፋሮች እጅግ ዘግናኝ ግፍ እንደሚፈጸምባቸው፣ ይህንንም ተከትሎ በጥምረት ትግላቸውን ለማስፋት መወሰናቸ፣ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ በሁዋላ ኤርትራ እንዴት ትቀጥላለች በሚል የአስተዳደር ቅርጿን የሚያበጅ ጉባኤ መካሄዱን የውጭ ሚዲያዎች መዘገባቸው አይዘነጋም።

የኤርትራ አፋሮች፣ ከኢትዮጵያና ጅቡቲ አፋሮች ጋር የተሳሰሩና ህብረት መፍጠር የሚፈልጉ የአሰብ ወደብም ንብረታቸው እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲያስታውቁ መቆየታቸው የሚታወስ ነው።

ክፉኛ የተመታውና ተሽመድምዶ ወደ ሰላም የመጣው ትህነግ መንግስት እስካልከለውና አማራጩን ካልዘጋበት በየትኛውም አጋጣሚ የኢሳያስ አፉወርቂን መንግስት ለመገልበጥ እንደማይተኛ አመራሩም ሆነ ደጋፊዎቹ በተደጋጋሚ የሚገልጹት ጉዳይ ነው።

በአዲስ አበባ ብቻ ከስምንት መቶ ሺህ የሚልቁ የኤርትራ ተወላጆች እንደሚኖሩ፣ ሲኖሩም እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በነጻነትና በእኩል የገበያ ድርሻ እንደሆነ ይታወቃል።

ዜናውን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ተባባሪያችን ስማቸው ይላተጠቀሰ ባለስልጣንን ጠይቆ ለጊዜው ምላሽ እንደማይሰጡ ገልጸውለታል።

ኢሳያስ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባርን፣ የአርበኞች ግንባር ሃይሎችን፣ የኦነግን ታጣቂዎች፣ የትግራይ ተቃዋሚ ሃይሎችን፣ የሶማሌ ሃይሎችን ሲያሰለጥን፣ ሲያስታጥቅና ሲያሰማራ መቆየቱ ይታወቃል።፣ ከትህነግ ወረራ ጋር ተያይዞ የተጀመረ ቢሆንም አሁን ድረርስ መንግስት በቅርቡ ኢመደበኛ ያላቸውን አካላት ከማሰለጥን ጀምሮ እገዛ እየደረገ እንደነበር ይታወሳል።

Leave a Reply