Site icon ETHIO12.COM

የአየር ሃይል የኢትዮጵያን ታላቅነት በሚመጥን ደረጃ እየተገነባ ነው፤ በህር ሃይል በቅርቡ በአፍሪካ ቀዳሚ ይሆናል

– ኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎቷን ስታውጅ በበቂ ቅድመ ሆኔታና የህዳሴን ግድብ ከቋጨች በሁዋላ መሆኑ ለሌሎች አሉባልታዎች መልስ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በሁዋላ ዳግም ትንሳዔ የተነሳው የኢትዮጵያ አየር ሃይል የኢትዮጵያ በሁሉም መስክ የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚመጥን አስተማማኝና ዘመናዊ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በሻዕቢያና ትህነግ ስምምነት የፈረሰው ባህር ሃይልም ዳግም ተወልዶ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም እንዲን ተደርጎ እየተገነባ መሆኑ ተመልክቷል። ዘመናዊ የጦር መርከቦችም ባለቤት ሆኗል።

ኢትዮጵያ በአየር ሃይል ታሪኳ ከአፍሪካ ቀዳሚና ዝናን ያተረፈ ሆኖ ሳለ ከ1983 በሁዋላ በሂደት ተመናምኖ ዳዋ በልቶት፣ ባለሙያዎቹም ተበትነው ነበር። ከአገር የወጡ በርክታ ባለሙያዎች እንደመሰከሩት በተቋሙ ላይ ታሪክ የማይረሳው ውድመት ተፈጽሞበታል። በህልውናው ጦርነት ወቅት አገራቸውን ለመታደግ ከውጭ የተመለሱ ኢትዮጵያዊ ባለሙያዎች እንዳሉት የኢትዮጵያ አየር ሃይል እንዲበተን ባይደረግ ኖሮ ዛሬ ላይ እጅግ ገናና ይሆን ነበር።

በቁጭት የቀደመውን ጥፋት ያወሱት ባለሙያዎች ከለውጡ በሁዋላ የተደረገውን ዝግጅትና ትኩረት እንዲሁም በአጭር ጊዜ ውስጥ የተሰራውን ሲመለከቱ መገረማቸውን በግልጽ ማስታወቃቸው አይዘነጋም። አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በሁዋላ በግንባር ቀደምትነት ትኩረት የሰጡት የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዘመናዊ የጦር አውሮፕላንና የድሮን ባለቤት አድርገውታል። ሃላፊዎቹ እንዳስታወቁት በአዲስ ሪፎርም ተቋሙ አዋራ እየጠረገ ያነሳቸውን አውሮፕላኖች በማዘመን፣ አደርፈጃጀቱን በማሳደግና የሰው ሃይሉን በማብቃት ደረጃውን ከፍ አድርጓል። በተለይም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ አየር ኃይሉ በሁሉም ረገድ በመዘመንና ስኬታማ በመሆን ሀገር የምትኮራበት ታላቅ ተቋም መሆኑንም ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል አሁን ላይ በውጊያ መሠረተ-ልማት፣ በሰው ኃይል ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራና አጠቃቀም በአጭር ጊዜ ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገቡን በተቋሙ የተለያዩ ዲፓርትመንት ኃላፊዎች ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል አስተማማኝ የሀገር መከታ በመሆን ለየትኛውም ግዳጅ አፈጻጸም ብቁና ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ አየር ኃይልን በሁሉም መስክ የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚመጥን ዘመናዊ ተቋም የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ሲሉ ለኢፕድ ባለሟዎቹ አረጋግጠዋል።

አየር ሃይል ዛሬ የውጊያ ሃይሉን ከማዝመኑና ዘመናዊ ትጥቅ ከመታጠቁ በተጨማሪ ራሱ የቴክኖሎጂ ፈጣሪ በመሆን አቅሙን ማሳደጉን ባለሙያዎቹ አመልክተዋል። አዛዡ ሌተናል ይልማ መርዳሳ ቀደም ሲል እንዳሉት የኢትዮጵያ አየር ሃይል ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ አለኝታና ኩራት በሚሆንበት ደረጃ ዳግም እንዲደራጅ መደረጉ ለወገን ኩራት ሲሆን ለጠላት ስጋት እንዲሁን አስችሎታል።

ትናንት ኢዜአ ያነጋገራቸው ከፍተኛ መኮንኖች በአየር ኃይል አቪዬሽን ከባድ ጥገና ማዕከል የሮተሪ ዲፓርትመንት ዊንግ መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ኢንጂነር ሙሉቀን ደርሶ፤ አየር ኃይሉ የኢትዮጵያን ታላቅነት በሚመጥን መልኩ በሁሉም መስክ በዘመናዊ መልኩ እየተገነባ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በአየር ኃይሉ ለውጊያ፣ መለማመጃና ለትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ አውሮፕላኖችን አስተማማኝ እድሳትና ጥገና በማድረግ ላይ ስለመሆኑም አንስተዋል። በአየር ኃይሉ ቀደም ሲል የነበሩ አውሮፕላኖችን ከአናሎግ ወደ ዲጂታል የማሻሻያ ሥራ በማከናወን የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ እየተደረገ መሆኑንም አብራርተዋል።

የአየር ኃይል የከባድ ጥገና ማዕከል የምርምር እና ልማት ክፍል ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ወንድማገኝ አርዓያ፤ በቴክኖሎጂ አጠቃቀምና በማሻሻያ ሥራዎች ስኬታማ መሆኑን ገልፀዋል።

በከባድ የጥገና ማዕከል አውሮፕላኖችን የማዘመን፣ የዕይታና ዒላማ አቅማቸውን የማጎልበት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በዚህም አየር ኃይሉ ያወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ማስቀረት መቻሉን ገልጸው፤ በቀጣይም ተጨማሪ ገቢዎችን ለማስገኘት እንሰራለን ብለዋል፡፡

በአየር ኃይል የአቪዬሽን ጥገና ማዕከል መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ደረጄ አስታጥቄ፤ አየር ኃይል የውጊያ መሠረተ-ልማቶችን በመገንባት ያከናወናቸው ተግባራት ግዳጆችን በአስተማማኝ ብቃት መወጣት የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በአየር ኃይሉ የትራንስፖርት ሄሊኮፕተር ጥገና ስኳድሮን ኃላፊ ሻለቃ አንድነት ብርሃኑ በበኩላቸው፤ አገራዊ ለውጡን ተከትሎ በአየር ኃይሉ በርካታ አመርቂ ሥራዎች ስለመከናወናቸው አብራርተዋል።

በአየር ኃይሉ የሄሊኮፕተር አብራሪዎቹ ሌተናል ኮሎኔል አየለ ዳዊት እና ሻለቃ ፀጋዬ አሰፋ ፤ አየር ኃይሉ አሁን ላይ በቴክኖሎጂ አጠቃቀምም ይሁን በግዳጅ አፈጻጸም አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል። በአስቸኳይ ተልዕኮና ግዳጅ በቀንም ይሁን በሌሊት በመብረር ያሰብነውን ማሳካት የሚያስችል ቁመና ላይ እንገኛለንም ነው ያሉት።

በተመሳሳይ ዜና “ባህር ሳይኖር ለመን ይቋቋማል” በሚል መንግስትን ሲተችበት የቆየው የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ብቅርቡ በአፍሪካ ታላቅ ሊሆን በሚያስችል ደረጃ እየተደራጀና አቅሙን በውጭና አገር ውስጥ እያበቃ መሆኑ ተሰምቷል። በባህር ሃይል ቲክኖሎጂና አቅም ከፊት ደረጃ ከሚቅመጡት መካከል ፈረንሳይና ሩሲያ የተማሩትን ጨምሮ በአገር ውስጥ በዩኒቨርስቲ ደረጃ የሰው ሃይሉን እያበቃ እንደሆነ የተነገረለት የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ዘመናዊ የጦር መርከብ ባለቤት መሆኑን ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ይናገራሉ።

አሁን ላይ መንግስት የባህር በርን አስፈላጊነት በይፋ ሲያውጅ “ዝግጅት እንዴት ይጠላል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ከዚህ ቀደም ሲሰነዘር ለነበረው ትችት ምላሽ ሰጥተዋል። በክህደት ተመቶ ዳግም እንዲፈርስ ሙከራ የተደረበትና በደምና አጥንቱ አገግሞ ዛሬ ግዙፍ ጦር የሆነው የአገር መከላከያ ሰራዊት በሃይል ከአየር ሃይልና ባህር ሃይሉ ጭምር ታላቅ እንደሆነ በውጭ ሃይሎች እየተመሰከረለት ነው።

“ከ፴ ዓመት ውርደት በኋላ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የውሃ አካል ላይ ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ ነው” ተብሎ የተነገረለት የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ባህርተኞችን በቅርቡ ሲያስመርቅ ” ሠራዊታችን እንደጠላት ፍላጎት ቢሆን ኖሮ ሀገራችን እና የህዝባችን ደህንነት አደጋ ላይ ይወደቅ ነበር ። ሠራዊታችን አላፊ አግዳሚ ሽፍታ የሚደመስሰው ሳይሆን በፕሮፌሽን የተገነባ የሀገራችን አለኝታ ሠራዊት ነው” ሲሉ ኢታማዦር ሹሙ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ መናገራቸው ይታወሳል።

ሰሞኑን ኢትዮጵያ የባህር በር በቀይ ባህር ላይ እንደምትሻ፣ ይህም ፍላጎት የህልውና እንደሆነ ማስታወቋን ተከትሎ አማራጭ የባህር በር ዜናዎች በይሁንታና አሉታዊ ጎኑ እየተሰማ ነው። ኢትዮጵያ ፋልጎቷን መግለጿን ተከትሎ ኤርትራ “በዚህ ጉዳይ መስሚያዬ ጥጥ ነው” ስትል ጁቡቲም ” በወደብ ኪራይ እያለብኳችሁ እኖራለሁ” በሚል ተመሳሳይ አሉታዊ ዜና አሰምታለች። ሶማሌም እንደዛው።

ከታማኝ ምንጮች እንደሚሰማው ከሆነ ኢትዮጵያ የባህር በር ባልቤት የመሆኗ ጉዳይ አልቆለታል። ኢትዮጵያ በቀጥታ ጥይቄ ሳታቀርብላቸው ምላሽ የሚሰጡት አገሮች ምን አልባትም ከጥቅምና ዋጋ ቢስ እንሆናለን ከሚል ስጋት የተነሳ እንደሆነ እየተገለጸ ነው። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ በቻይና ታላቁን ወደብ ሰፊ ጊዜ ወስደው መጎብኘታቸውና የባህር ሃይል ድምጹን አጥፍቶ ባለሙያዎችና ትጥቅ ማዘጋጀቱ የአንድ ማለዳ ሰበር ዜና ሊሆን እንደሚችል ምልክት መሆኑንን እነዚሁ ክፍሎች ይናገራሉ።


Exit mobile version