Site icon ETHIO12.COM

በዓመት አምስት ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ የሚያመርተው ፋብሪካ ከመጋቢት በሁዋላ የሲሚንቶ ዋጋ ወደ ነበረበት የሚመልሰ ነው

በቀን 10 ሺህ ቶን ሲሚንቶ እንዲያመርት እቅድ ተይዞለት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ እየተገነባ ያለውን የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የግንባታ በመጋቢት ወር ይጠናቀቃል። ምርቱ በተባለው ወር ሲጀምር የሲሚንቶ ዋጋ አሁን ካለበት በግማሽ እንደሚወርድ ይጠበቃል። ከመጋቢት በሁዋላ ፋብሪካው በ50 በመቶ የሲሚንቶ እጥረቱን ያስወግዳል።

ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ኩባንያ ከቻይና ባለሀብቶች ጋር በመሆን እየገነቡት ያለው ይህ ፋብሪካ፤ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እንዲገነቡ እቅድ ከተያዘላቸው ስድስት ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ እንደሆነ መገለጹ ይታወሳል። ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ከቻይና ባለ ሀብቶች ጋር በመሆን ለመግንባት የያዛቸው ስድስቱ ፕሮጀክቶች፡-

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሚያዚያ 23 ቀን 2014 የግንባታው ጅምር በጎበኙበት ወቅት ስራው በአስራ አምስት ወር እንዲጠናቀቅና ባስቸኳይ ወደ ምርት እንዲገባ ልዩ ክትትል እንደሚደረግ በገለጹት መሰረት ነው ምረቃው በሚያዚያ እንደሚሆን ይፋ የሆነው።

በተያዘው ዕቅድ መሰረት ግንባታው በተጀመረ በአስራአንደኛው ወር ማለትም ዛሬ ፋብሪካው በቀን 10 ሺህ ቶን ሲሚንቶ ለማምረት የሚያስችለውን የፕሪ ሂተር የመገጣጠሚያ ሥነ ሥርዓት ማከናወኑ ተመልክቷል።

ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግስ ግሩፕ ቦርድ ሊቀመንበር ዶክተር ብዙአየሁ ታደለ እንደተናገሩት፤ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የክሊንከር ሲሚንቶ ማምረቻ የመጨረሻ ፍሎር የመገጣጠሚያ እና የሮተሪ መዝጊያ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ተካሄዷል።

የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ፕሮጀክት ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አበባው በቀል በበኩላቸው፤ በሀገሪቱ ውስጥ እያደገ ያለው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ያጋጠመውን ከፍተኛ የሆነ የሲሚንቶ እጥረት በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል ፋብሪካው በቀን ከአስር ሺ ቶን በላይ ክሊንከር ማምረት የሚችል ነው ብለዋል።

ፋብሪካው በመጀመሪያው ዙር በዓመት አምስት ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ ያመርታል ያሉት ኢንጂነር አበባው፤ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ስኬታማ ከሚያደርጉ የግል ዘርፎች መካከል የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ኢንደስትሪያል ኮምፕሌክስ አንዱ እንደሚሆን ታምኖበታልም ብለዋል።

በ18 ወራት ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተይዟል። ፍብሪካው ወደ ስራ ሲገባ በ50 በመቶ የሲሚንቶ እጥረቱን እንደሚሸፍን ገልፀው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በ15 ወር እንዲጠናቅ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት እየተሰራ መሆኑን ኢንጂነር አበባው ጠቁመዋል።

ፋብሪካው ስራውን ሲጀምር ሲሚንቶ በመደበቅና እጥረት በመፍጠር ዋጋ እንዲንር ለሚያደርጉ መድሃኒት እንደሚሆንና አቅርቦቱን ሃምሳ ከመቶ የሚያሳድግ በመሆኑ ልዩ ትርጉም ያለው የዋጋ ቅናሽ እንደሚኖር ተጠቁሟል።

በአዲስ አበባ የመሬትና የቤት ዋጋ መቀነስ እይሳየ ባለበት በአሁኑ ወቅት ከብረት ዋጋ መቀነስ ጋር ተያይዞ የሲሚንቶ ችግር ከተቀረፈ ቅናሹ ይበልጥ እንደሚሆን ከወዲሁ እየተገመተ ነው። በከፍተኛ ዝርፊያ ላይ የተሰማሩ የሪል እስቴት ነጋዴዎች የዋናው ግብ አታቸው ሲሚንቶና ብረት ቅናሽ ሲታይ ዋጋቸውን እንዲያሻሽሉ ቁጥጥር እነደሚደረግ እየተሰማ ነው። የቤቶች ኮርፖሬሽን በጥራት ከፍ አድርጎ የሚገነባቸው ቤቶች በዋጋ ከግል ሪል እስቴቶች ጋር ሊመጣጠኑ እንደማይችሉ የሚጠቁሙ ዝርፎያው ሊገታ እንደሚገባ እየጠቆሙ ነው።

በዶላር እያሰሉ ክፚቸውን የሚያንሩት ሪል እስቴቶች ፣ ግብይታቸውን የሚያከናውኑት አገር ቤት በብር ነው። ግብይት የሚፈጽሙትም ከአገር ውስጥ አምራቾች ነው። ይህን የሚያነሱ እንደሚሉት የመንግስት ሚዲያዎችም ሆኑ “የዩቲዩብ ነጋዴዎች” ፊታቸውን ወደ እነዚህ ዘራፊዎች እንዲያዞሩ በርካቶች እይወተወቱ ነው።

Exit mobile version