Site icon ETHIO12.COM

አዋራውን አራግፎ ዳግም ህይወት የዘራው አየር ሃይል – የኢትዮጵያ ውሃ ልክ ሆኖ ተሰርቷል

በ1983 ኢህአዴግና ሻእቢያ አዲስ አበባ ሲገቡ የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት ከሙሉ መዋቅሩ ጋር “የደረግ” በሚል አፍርሰውት እንደነበር ይታወሳል። ባህር ሃይልና አየር ሃይልን ጨምሮ መከላከያ ዳግም በሪፎርም እንዲደራጁ ከተደረገበት ከዛሬ አምስት ዓመት ጀመሮ በተሰራ ስራ ተቋማቱ ኢትዮጵያን በሚመጥን መልኩ መታነጻቸው እየተገለጸ ነው።

ሰሞኑንን 80ኛ የምስረታ በዓሉን እያከናወነ ያለው አየር ሃይል ” ጥቁር አንበሣ” ከአምስት ዓመት በፊት አዋራ የለበሰ፣ ሞቶ የተገነዘ፣ የተረሳና ምናምንቴ ሆኖ የተጣለ ተቋም ነበር። ለውጡን ተከትሎ አየር ሃይል አዋራው ተጠርጎ፣ ዳወው ተመንጥሮ ነብስ መዘራቱን አንደበት ብቻ ሳይሆን ተግባሩ የሚተርከለት ተቋም ሆኗል።

ዘመናዊ ትጥቅ መታጠቁ ብቻ ሳይሆን በብቃትና በሰው ሃይል፣ በጥራትና በጥልቀት የምርመር ተቋም ሆኖ ኢትዮጵያን በአየር ከሚመጣ ማናቸውም አደጋ ለመታደግ ችሏል። ራሱን በሰው ሃይና አደረጃጀት ያዘመነው አይር ሃይል ዛሬ የቀደመውን ውድቀቱን ለሚመኙ ሁሉ ራስ ምታት የሆነ፣ ለአገር ወዳዶች ደግሞ አለኝታ መሆን የቻለ ተቋም መሆኑ ሃላፊዎቹ ሰሞኑንንበተለያዩ መድረኮች ሲያረጋግጡ ሰንብተዋል።

የ”መከላከያ ዘርፍን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች እየተደረጉ ያሉ ማሻሻያዎች ኢትዮጵያን ለማጽናትና ለማስቀጠል ወሳኝ ናቸው ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተናገሩትም በዚሁ መነሻ ነው።

የመከላከያ ዘርፍን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች እየተደረጉ ያሉ ማሻሻያዎች ኢትዮጵያን ለማጽናትና ለማስቀጠል ወሳኝ ናቸው ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ ያስታወቁት በዚሁ በሰማንያ ስምንተኛው የምስረታ በዓለ ላይ ነው።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል 88ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት በቢሾፍቱ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በተካሄደበት ወቅት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላና ምክትላቸው ጀነራል አበባው ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አየር ኃይል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ኢብራሒም ናስር፣ ጄኔራል መኮንኖች፣ የአፍሪካ አየር ኃይል አዛዦች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ዝግጅቱ የተከበረበት አግባብ እጅግ ከፍተኛና አህጉርና ዓለም ዓቀፍ ይዘት የተላበሰ በመሆኑ ሰፊ የሚዲያ ሽፋንም አግኝቷል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል 88ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ታላቅ አገር ታላቅ ተቋም የመገንባትና የማጽናት ምልክት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልፀዋል። ኢትዮጵያ የአየር፣ ምድርና ባህርን ጨምሮ በሁሉም መስኮች ወታደራዊ አቅሟን እየገነባች እንደምትገኝ አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ የመከላከያ ዘርፍን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች እየተደረጉ ያሉ ማሻሻያዎች አገሪቷን ለማጽናትና ለማስቀጠል ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል።

ለቀጣዩ ትውልድ ታላቅ አገርና ታላቅ ተቋም ለማስተላለፍ መንግሥት አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

ወቅቱን የዋጀ ወታደራዊ ኃይል መገንባት በአዳዲስ ስልቶች የሚመጡ ጥቃቶችን ለመመከት ያስችላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለዚህም ሁሉም ወገን የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢፌዴሪ አየር ኃይል አቅሙ እንዲገነባ አስተዋጽዖ ላደረጉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።

የአየር ኃይሉ 88ኛ ዓመት የምስረታ በዓል “በመስዋዕትነት ሀገርን የዋጀ፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል” በሚል መሪ ኃሳብ ከኅዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲከበር ቆይቷል።

Exit mobile version