Site icon ETHIO12.COM

ትግራይ – “ሰልፍ የለም፣ ህግ ጥሶ ያልታወቀና ያልተፈቀደ ጉዳይ (ሰልፍ) አካሂዳለሁ በሚል ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል”

” ከሌላ አከባቢ መጥቶ በከተማው ስልፍ አደርጋለሁ ማለት ህልም ነው ” ሲሉ የመቐለ ከተማ ምክትል ከንቲባ ተናገሩ። የመቐለ ከተማ አስተዳደር ፤ “ለእሁድ ታህሳስ 21/2016 ዓ.ም የተፈቀደ ይሁን የሚካሄድ የምናውቀው ሠልፍ የለም ” ሲል አስጠንቋል።

የመቐለ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ኤልያስ ካህሳይ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፤” “ለታህሳስ 21 /2016 ዓ.ም በከተማው የተፈቀደ ይሁን እንዲካሄድ የታቀደ የምናውቀው ሰልፍ የለም” ብለዋል። 

” ህዝብ እንደ ወትሮ በመበደኛ ስራውና ጉዳዩ መዋል አለበት ” ያሉት ምክትል ከንቲባው ፤ ” የከተማው አስተዳደር ቃል ጥሶ ያልታወቀና ያልተፈቀደ ጉዳይ (ሰልፍ) አካሂዳለሁ በሚል ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ” ሲሉ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ሃላፊውን ጠቅሶ ያስታወቀው ቲክቫህ ነው። አክለውም ” የተባለውን የማያከብር ማንኛውም አካል እንደማንታገስ ማሳወቅ እንፈልጋለን ” ብለዋል።

ውሳኔው የአስተዳደሩ ኮሚቴ መሆኑ የገለፁት አቶ ኤልያስ ፤ ከሌላ አከባቢ መጥቶ ሰልፍ የሚያደርገውን አካል ስምና ማንነቱ ባይጠቅሱም ” ከሌላ አከባቢ መጥቶ በከተማው ስልፍ አደርጋለሁ ማለት ህልም ነው ” ብለዋል።

” በተለያዩ ሚድያዎች እየቀረቡ የተዛቡ መረጃ ይሰጣሉ ” ላሏቸው አካላት ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ ያስጠነቀቁት ምክትል ከንቲባው ፤ ” ህዝቡ ካልተረጋገጡ አሉባልታ ወሬዎች በመራቅ ስራው ማከናወን አለበት ” ብለዋል። 

ሸገር በሚባል የዩቲዩብ አውድ አቶ የሺህ ዋስ አሰፋ ” በአዲስ አበባ የተከለክለው ሰልፍ በመቀለ ይደረጋል” ሲሉ ሰልፉ እውቅና እንዳለው ጠቅሰው አስታውቀዋል። የሰልፉ አስተባባሪ እንደሆኑ ያስታወቁት አቶ የሺህ ዋስ አሰፋ የሰልፉ ጥሪ በመቀለ እውቅና ማግኘቱን አመልክተው በኦሮሚያ፣ አማራና ጉራጌ ዞን ግን ይህ ጥሪ እንዳልተላለፈ ገልጸዋል።

” ህልም ነው” ሲሉ ሰልፉ ከሌሎች አካባቢ የመጡ ወገኖች ባሉዋቸው አካላት መቀለ እንደማይካሄድ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ይፋ አድርገዋል። ዕውቅና የተሰጠው ምንም ዓይነት የሚታወቅ ሰልፍም የለም ሲሉ በይፋ ለመገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል። ይህን መግለጫ ተከትሎ አቶ የሺህ ዋስ ይህ እስከተጻፈ ድረስ ተጨማሪ መረጃ ወይም ማሻሻያ አልሰጡም። “እውቅና አግኝቷል” ሲሉ ይፋ ያደረጉት የሰልፍ ቀጠሮ ይቀጥል አይቀጥል የታወቀ ነገር የለም።

Exit mobile version