ETHIO12.COM

መለስና አብይ ለታሪክ – ኢትዮጵያ የታነቀችበትን ገመድ በጥሳ የባህር በር ባለቤት ሆነች፣ ስብራቷ ተጠገነ፤ ህዝብ ደስታውን እየገለጸ ነው

ሟቹ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ስልታን ሲይዙ ኢትዮጵያ ሁለት ወደብ ነበራት። ለኤርትራ እውቅና ሲሰጡ፣ ኢትዮጵያ ህጋዊ ሃብቷን አስረክባ የባህር በር አጣች። ታላቅ ህዝብ ባህር አልባ ሆነ። ይህ ከአቶ መለስ ሌጋሲዎች መካከል ቀዳሚው ነው። አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ መለስ በብሄር የበለቷት፣ የብሄርተኝነት ችግኝ አፍርቶ ሊበላ በደረሰበት፣ እንዴት እንደሰሯት ስለሚያውቁ “እኛ ከሌለን /ትህነግ ከሌለ” እንደ ሶማሌ ትሆናለች እያሉ ሲያሟርቱባት የነበረች፣ ወደብ አልባና ያላትን ለጅቡቲ እየገበረች የምትኖር እዳ የሰበራት አገር ነበር የተረከቡት። ዘረኝነት ያፈራውን የበሰለ ፍሬ እያጸዱ ኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤት አደረጉ። አብይ የእኛ ያልሆነችን አገር እውቅና ሰጥጠው የባህር ባር ባለቤት ሲያደርጉን፣ የራሳችንን የባህር በር ከልዩ እውቅና ጋር ለኢሳያስ በማሸከም ወደብ አልባ ያደረጉን መለስ ሁለቱም ኢትዮጵያ በታሪክ ትዘግባቸዋለች።

ኢትዮጵያ አሁን ለሃምሳ ዓመታት ውል የገባችበት የበርበራ ወደብ በኤደን ባህረ ሰላጤ ምዕራብ ዳርቻ፣ የበርበራን ወደብ ሲሆን ወደቡ የቀይ ባህር የሲዊዝ ካናል መግቢያ ማንቁርት ላይ እንደሆነ ታውቋል። ይህ እንዲሆንና ላለፉት ሰላሳ ዓመታት አገሪቱ ታንቃ የኖረችበት የሴራ ትብትብ እንዲበጣጠስ የሚያስችል ስምምነት ከተደረሰ በሁዋላ ” ሌላ ምን ይላባል? ፈጣሪ ይመስገን” በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህን አደረገ ላሉት ፈጣሪ ክብር ሰጥተዋል። አያዘውም ” የኢትዮጵያን ስብራት መጠገኛ ቀን እንኳን አደረሰን” ሲል አብይ አህመድ የቀኑንን ታሪካዊነት አብስረዋል። ይህ እንደተሰማ የጅግጅጋ ከተማ ህዝብ በተሽከርካሪ ጥሩምባ እያሰማ ደስታውን ገልጿል።

እ አ አ በ1993 ኢትዮጵያን እንመራለን በሚሉ ሃይሎች ወደብ አልባ እንድትሆን የተፈረደባት ኢትዮጵያ ቆዳና ሌጦ፣ ቡናና የእርሻ ውጤቶችን ወደ ውጭ በመላክ የምታገኘውን ሃብት ለጅቡቲ ስትገብር ሰላሳ ዓመት አስቆጥራለች። አዲሱን ስምምነት ተከትሎ ኤፒ እንደዘገበው የኢትዮጵያ የባህር በር አልባነት በኢንቨስትመንት ላይ ሳይቀር ከፍተኛ ጫና ያሰረፈ ነበር።

ትህነግ ውስጥ የአሰብ ወደብን መወሰድ የሚቃወሙ ቢኖሩም ሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ ” በሁዋላ ላይ አሰብን ከኢትዮጵያ ከመውሰድ ይልቅ ከኤርትራ ምንጠቅ ይቀላል” በሚል ሂሳብ ትግራይ አገር ስትሆንና ስትገነጠል አሰብን እንድትወስድ ህልም አልመው ውሳኔውን እንዳስወሰኑ የትህነግ አባላት መናገራቸው ይታወሳል።

ከታነቀችና የባህር በር አላባ ከሆነች ከሶስት አስርት ዓመታት በሁዋላ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” የተናገርነውን ፈጽመናል።ኢትዮጵያ ብዙ ስብራቶች አሉዋት ዋናውና ትልቁ ቀይ ባህር ላይ ተመልካች የሆነችው ኢትዮጵያ ይህን ስብራቷን መስበሯ እንደሆነ አመልክተዋል።

ለኢትዮጵያ የባህር በር የህልውናዋ መሰረት መሆኑንን ጠቅሰው ከወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በይፋ ስለ ቀይ ባህር ሲናገሩ “ለአጀንዳ ማስቀየሻ፣ ለትኩረት መቀልበሻ ወዘተ ነው” በሚል የቀይ ባህርን ጥያቄ በጥላቻ ሲያንቋሽሹ የነበሩ አካላት ይህን ዜና በምን መልኩ እንደሚያቀርቡት ለብዙዎች ግራ ሆኗል።

ይህ የተቃርኖ ጭፍን መንገድ እንዳለ ሆኖ ኢትዮጵያ የባህር በር የምታገኝበት ዜና ይፋ መሆኑንን ተከትሎ በጅግጅጋ፣ በሀረር፣ በድሬዳዋ፣ በወላይታ ዞንና በአዲስ አበባ ከተማ መተኑ ቢለያይም ህዝብ ደስታውን እየገለጸ ስለምሆኑ በምስልና በቪዲዮ የተደገፉ መረጃዎች እየወጡ ነው። ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ መፈረሟን ተከትሎ ሕዝቡ ደስታውን በምን ያህል ደረጃ እንደገለጸ ዘግይተን እንመለስበታለን።

“ኢትዮጵያ ኤርትራን ልትወር ነው” በሚል ከሚምሉባት አገራቸው ይልቅ ለሌላ ወግነው ሲያነቡና ኢትዮጵያ ጦርነት ልትጀምር በዝግጅት ላይ እንዳለች ሲገልጹ የነበሩ ወገኖች እንዳሉት ሳይሆን ቀድሞ በተባለው መንገድ ኢትዮጵያ አላማዋን አሳክታለች።

ጠቅላይ ሚኒስት ያር አብይ በኅዳር አራት ቀን 2016 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ የባሕር በርን በተመለከተ በቢዝነስ ሕግ ግን የማያወላዳ ምርጫ እንፈልጋለን” ሲሉ ባስታወቁት መሰረት የጦርነትም ሆን የጥይት ጉዳይ ሳይሰማ ኢትዮጵያ የ50 ዓመት የባህር በር ባለቤትነት ውል አስራለች።

በበርበራ ወደብ የሃያ ኪሎሜት እርዝመት ያለው የባህር በር ባለቤት እንድትሆን በሚያስችላት በዚህ ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ ወታደራዊ የጦር ሰፈር እንደምትገነባ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘገባ ይፋ አድርጓል። ኢትዮጵያ የባህር ሃይሏ አስቀድሞ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ እንደሆነና ይህም ታስቦበት የተደረገ ስለመሆኑ አብይ አህመድ መናገራቸው ይታወሳል።

የመግባቢያ ሰነዱን “አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚያመጣ” እና “[በአፍሪካ] ቀንድ ውስጥ ለክልላዊ ውህደት ትልቅ ጠቀሜታ አለው” በሚል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መግለጫ አጉልቶ አድንቆታል።

ወደ ስልጣን ከመጡ ከጥቂት ወራት በሁዋላ ተለይተው በተጠና ስልት በሚዲያ በደቦ ስማቸውና ተግብራቸው የሚብጠለጠለው ዐቢይ አሕመድ በቲውተር / ኤክስ ገጻቸው “ፈጣሪ ይመስገን እንጂ ሌላ ምን ሊባል ይችላል!” ሲሉ ክብሩን ለፈጣሪያቸው ሰጥተዋል። በወረራው ወቅት ኢትዮጵያ ከነበረችበት አሳሳቢ ደረጃ በድል አድራጊነት ስትጨርስ ” የተደረገልንን ስለማውቅ እኔ ፈጣሪን አመሰግናለሁ” ማለታቸው አይዘነጋም።

የሶማሊላንድ ቲቪ በቲውተር / ኤክስ ገጹ ኢትዮጵያ 20 ኪሜ የባህር በር እንድታገኝ ስምምነት ሲደረስ በተመሳሳይ ለሶማሊላንድ ዕውቅና በመስጠት የመጀመሪያ አገር እንደሆነች አስታውቋል። ይህ ዜና ኢትዮጵያ ለኤርትራ እውቅና በመስጠት ቀዳሚ አገር ሆና በተመሳሳይ ሁለቱንም ወደቦች አስረክባ ባዶ ስትቀር፣ ዛሬ አብይ አህመድ ለሶማሊ ላንድ እውቅና በመስጠት የባህር በር ባለቤት እንድትሆን አስችሏታል። ይህ ታሪካዊ ንፅፅር ለትውልድና የሚተላለፍም ሆኗል።

ከኢትዮጵያ ድንበር እስከ በርበራ ድረስ ያለው 241 ኪሎ ሜትር ርቀት ብቻ ነው ። የአውራ መንገዱ ሶማሌ ላንድ ከአውሮጳ ኅብረት ባገኘችው የገንዘብ ድጋፍ ተግንብቷል። ከኤደን ባህረ-ሰላጤ ደቡባዊ ጫፍ ላይ የምትገኘው ሶማሌላንድ እንደ አገር ለመቆም የሚያስፈልጋትን ቅድመ-ሁኔታዎች ሁሉ ታሟላለች። የመገበያያ ገንዘብ፣ በተግባር የሚሠራ የቢሮክራሲ ስርዓት፤ የሰለጠነ ፖሊስ እና የመከላከያ ሠራዊት አላት። መቀመጫውን ሐርጌሳ ላይ ያደረገው እና ዓለም አቀፍ እውቅና ለማግኘት የሚታትረው መንግሥት የሶማሌላንድን ድንበር ማስጠበቅ ችሏል። ከሞቅዲሾ መንግሥት ጋር የሚስነዘርበትን ማናቸውንም ጉዳዮች እንደ አመጣቱ የመመለስና የመደራደር አቅም አለው።

አሁን ይፋ በሆነው ዜና መሰረት ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የደህንነትና የኢኮኖሚና ስምምነትም አላቸው። ዝርዝሩ ይፋ ባይሆንም ኢትዮጵያ በኢጋድና አፍሪቃ ህብረት ውስጥ ባላት ተጽእኖ የሶማሊላንድን አገር በማድረግ ጥቅሟን ለማስከበር ስትነሳ ለሚነሱ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ምላሽ ለመስጠት ሁለቱም አካላት ተስማምተዋል። የጸጥታና ደህንነት ውሉ እዚህ ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን የኢኮኖሚ ውሉ ከኢትዮጵያ የሚጓዘውን የቀንድ ከብትን ጨምሮ ማናቸውንም ኮንትሮባንዶች ምናረቅ እንደሆነ ተሰምቷል። ከዚህ አንጻር ዜናው በዚሁ ባምጭበርበር ንግድ ለተሰማሩ መርዶ ሆኖባቸዋል። ከሁሉም በላይ ግን የሲዊዝ ካናልና የቀይ ባህር መግቢያ ማንቁርቱ ላይ ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘቷ የህዳሴው ግድብ ከፈጠረው የፖለቲካ ጡንቻ ጋር ተዳምሮ ኢትዮጵያን የቀይ ባህር ፖለቲካ ተዋናይ ያደርጋታል። በዚህና በበርካታ ተያያዥ ምክንያቶች ኢትዮጵያን የሚወዱ ሁሉ ደስታቸው ይልቃል። የፖለቲካ ልዩነትና አገር የተለያዩ ናቸውና። ይህ ዜና እስከተጻፈ ድረስ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች የተሰማ የንኳን ደስ አላችሁም መልዕክት የለም።

Exit mobile version