Site icon ETHIO12.COM

“ሶማሊላንድ ነጻ አገር መሆኗ የማይቀር ነው፤ አሜሪካ ጨዋታ ትችላለች”

በቅርቡ ከኢትዮጵያ ጋር የባህር በር የሊዝ ስምምነት ለማድረግ የመጀመሪያውን ቅድመ መግባባት የፈረመችው ሶማሊላንድ ነጻ አገር የመሆኗ ጉዳይ ያለቀለት መሆኑንን ተቀማጭነታቸው አውሮፓ የሆኑ ምሁር ገለጹ። አሜሪካና እንግሊዝ ቲያትር እየሰሩ መሆኑንንም አመልከቱ። ኢትዮጵያ ዘጠና ዘጠኝ ኪሎሜትር የባህር ጠርዝ የማግኘት ፍላጎት እንዳላት ተሰምቷል።

ጅቡቲ፣ አዲስ አበባና አሜሪካን አገር የተማሩትና በሚታወቅ ኮሌጅ ውስጥ በመምህርነት የሚሰሩት የሃርጌሳ ተወላጅ ለኢትዮ12 እንዳሉት ከሆነ ጉዳዩ ከባህር በር በላይ ነው።የሶማሌላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሂ አብዱ ስምምነቱን ፈጽመው ወደ አገራቸው ሲመለሱ ህዝብ አደባባይ በመውጣት ከፍተኛ አቀባበል እንዳደረገላቸው ዓለም አይቷል።

ፕሬዚዳንቱ ህዝብ መካከል ሆነው ” ጸሃይ ስትወጣ በእጅ መከልከል አይቻልም” የሚልም ብሂል ማንሳታቸውን ያስታወሱት የሃርጌሳው ተወላጅ ሶማሊያ ይህን ጉዞ ታደናቅፋለች፣ ወይም የማደናቀፍ አቅም አላት ብለው እንደማያምኑ መረጃ አጣቅሰው ተናግረዋል።ሶማሌ-ላንድ፣ ከሶማልያ ጋር የሶስት ዓመት የነጻነት ጦርነት ካካሄደች የዚያድባሬን መንግስት በማሸነፍ እ.አ.አ. ከ1991 ጀምሮ እራሷን “ነፃ አገር” ብላ መጥራቷን አስታውሰው ዛሬ ላይ ከ35 በላይ አገሮች ዕውቅና እንደሰጧት አመልክተዋል።

የሶማሌላንድ ን ነጻ አውጪ እንቅስቃሴ SLM የወቅቱ ታጋይና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት የአሁኑ የሶማሌላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሂ አብዱ ከስምምነቱ በፊት በርካታ ቀደም ሲል ከኢትዮጵያ ጋር በመሆን በሰሩት ስራ ማስተማመኛ ማግኘታቸውን እንደሚያውቁ የጠቆሙት እኚሁ ምሁር፣ ከሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ባገኙት መረጃ ይህንኑ ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል።

የዩናይትድ ስቴትስን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ድንገት ይህንኑ አስመልክቶ ለተጠየቁት “ዩናይትድ ስቴትስ የምታውቀው የሶማሊያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ በአውሮፓ አቆጣጠር በ1960 ዓ.ም. ወሰኖቿ ውስጥ ላለ ሉዓላዊነቷና የግዛቷ ጥብቅነት ነው” ማለታቸው እሳቸው ካላቸው መረጃ ጋር እንደሚጣረስ ለተጠየቁት ” ጉዳዩ የከረረ አቋም ቢሆን ኖሮ መግለጫ ይንጋጋ ነበር” ካሉ በሁዋላ ሁለት ማሳያዎች አንስተው አሜሪካ ጨዋታ መጫዋት እንደምትችል ገልጸዋል።
“በ26 ጁን 1960 ሶማሌ ላንድ ከእንግሊዝ ነጻ ወታች። ከአራት ቀን በሁዋላ በ1 ጁላይ


“የስማሌው ፕሬዚዳንት ዜያድባሬ ሃርጌሳን በጀት አውድሟል። ከሃምሳ ሺህ በላይ ሰዎች ሞተዋል። አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ወደ ኢትዮጵያ ተሰደው ሃርቲሼክ ተጠልለው ራሳቸውና ልጆቻቸውን አድነዋል። አርብቶ አደሮች ወደ ቻሉበት ቦታ ሸሽተው ራሳቸውን አትርፈዋል” ሲሉ ይህን ታሪክ የሶማሌላንድ ህዝብ እንደማይዘነጋው ይገልሳሉ። አያይዘውም በተቃራኒ ኢትዮጵያ እጇን ዘርግታ መጠለያ በመስጠት ህይወታቸውን መታደጓ በስማሌላንድ ህዝብ ልብ ውስጥ የታተመ አሻራ…. “


1960 ሶማሌያ ከጣሊያን ነጻ ወጣች። አሜሪካ የምታከብረው የትኛውን የድንበር ህግ ነው” ሲሉ ይጠይቁና ” ሶማሌላንድ በቅኝ ግዢ የተፈጠረች አገር ናት። አሜሪካ በጠቀሰችው ዘመን አፈጣጠሯ ያው ነው። የአሜሪካ ምላሽ ሲተነተን የቅኝ ግዢ ዘመኑን አፈታጠርሽን አውቃለሁ እንደማለት ነው። ውሎ አድሮ እንንናየዋለን” የሚል መደምደሚያ ያስቀምጣሉ። እንግሊዝም ስጋት በመግለጽ ያለችው ተመሳሳይ እንደሆነ ምሁሩ ጠቅሰው ድፍን አውሮፓ፣ ድፍን አፍሪካ ለምን ዝም አለ? በቅርቡ በሚካሄደው የአፍሪካ አገራት ስብሰባ ሶማሌላንድ መጋበዟም ሌላ የሚያሳብቀው ጉዳይ አለም ብለዋል።
እንግሊዝ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ አማካይነት ስልክ በመደወል “አታስቡ” የሚል ማስተማመኛ እንደሰጠች የሚጠቅሱት የሃርጌሳ ተወላጅ ነገሩ እርጋታን የሚጠይቅ እንጂ ከመሆን የሚያግደው ሃይል እንደሌለ አመላክተዋል።
እ አ አ 1988 በሶማሌላንድ ህዝብ የማይረሳ ጉዳት መድረሱን ያስታወሱት እኚሁ ምሁር፣ “የስማሌው ፕሬዚዳንት ዜያድባሬ ሃርጌሳን በጀት አውድሟል። ከሃምሳ ሺህ በላይ ሰዎች ሞተዋል። አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ወደ ኢትዮጵያ ተሰደው ሃርቲሼክ ተጠልለው ራሳቸውና ልጆቻቸውን አድነዋል። አርብቶ አደሮች ወደ ቻሉበት ቦታ ሸሽተው ራሳቸውን አትርፈዋል” ሲሉ ይህን ታሪክ የሶማሌላንድ ህዝብ እንደማይዘነጋው ይገልሳሉ። አያይዘውም በተቃራኒ ኢትዮጵያ እጇን ዘርግታ መጠለያ በመስጠት ህይወታቸውን መታደጓ በስማሌላንድ ህዝብ ልብ ውስጥ የታተመ አሻራ መሆኑንን ያስረዳሉ።
እሳቸውን ጨምሮ በርካታ የሶማሌ ምሁራን በኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ያለ አንዳች ልዩነት መማራቸውን በማንሳት ጉዳይ ከወደብ በላይ እንደሆነ ይገልጻሉ። በቀን በትንሹ እስከ 10 ሺህ ዶላር ምርት ወደ ሶማሌላንድ እንደሚገባና በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በሶማሌላንድ እንደሚኖሩ አመልክተዋል።
ትምህርት በአማርኛ እንደሚሰጥ አመልክተው፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ጉዳይ ላይ የተመሰረተው ግንኙነት አሁን ላይ በደህነት፣ በፖለቲካና በስትራቴጂክ ጉዳዮች ሲጠናከር የሞቃዲሾ መንግስት እንዴት ብሎ ስጋት ሊሆን እንደሚችል ለማሰብ እንደሚቸገሩ ገልጸው፣ ስጋትም ባይኖር ውጥረት መረገብ እንደሚገባው እምነታቸው መሆኑንን ያመለክታሉ።
ከሃያ ሺህ በላይ የኢትዮጵያ ወታደሮች በግዙፍ ሜካናይዝድ ሃይል የሚንከባከቡት የሶማሌ መንግስት አቅሙን እያወቀ ለምን ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት እንደሚያውጅ ተጠይቀው ” ሳኡዲ፣ ግብጽና ኤርትራ ናቸው የሚገፉት” ካሉ በሁዋላ የለውጡ ሰሞን የቀድሞው ፕሬዚዳንት ፈርማጆ የባህር በር ለመስጠት ተስማምተው እንደነበር በማንሳት ” የዕነ ሳዑዲና ግብጽ ግፊት እንዳለ ሆኖ ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ አቅም እንደሌላቸው እያወቁ በዚህ መተን ላይ ታች የሚሉት ለምን በኔ በኩል አላለፈም” ከሚል ቁጭትና የሚገኘውን ገቢም ከማስላት አንጻር እንደሆነ ገልጸዋል።
ሶማሌላንድ ከሽብርም ሆነ ከማንኛውም ሁከት ነሳ የሆነች፣ አምስት ጊዜ የተሳካ ምርጫ ያደረገች፣ ምርጫዋም እንደ ሶማሊያ እጅ በማውታት ሳይሆን በዲጂታል ድምጽ አሰባሰብ የሚካሄድ፣ የራሷ ገቢና ብር፣ እንዲሁም እጅግ ጦርነትና ረብሻን የማይፈልግ ህብረተሰብ የገነባች አገር በመሆኗ ያለ ምንም ድጋፍ የሶማሊያን መንግስት አደብ ማስገዛትም እንደምትችል ምሁሩ ተናግረዋል።
“ይልቁኑ” አሉ ምሁሩ፣ ” ይልቁኑ የሚያሳበኝ ኢትዮጵያ ሃይሏን ከሶማሊያ ከሳበች አሁን ያዙኝ ልቀቁኝ የሚሉት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ወይ ስደት አለያም አልሸባብ መዳፍ ውስጥ እንዳይወድቁ ነው”

ከባህር በር ስምምነቱ ጋር ተያይዞ ሶማሌላንድ የዓለም አጀንዳ መሆኗና የማያውቋት ሁሉ እንዲያውቋት እድል መስተቱ በራሱ ፖለቲካዊ ድል እንደሆነ አስተያየት ሰጪ አስታወቀው፣ ባለሃብቱ ኦክሰዴ ዘራቸው ከሶማሌላንድ እንደሆነ፣ የአቶ አብዱል መጅድ ሁሴን እናትም ድሬደዋ አርፈው ሃርጌሳ መቀበራቸውን በምሳሌ በመተቀስ ሰፊ የደም ግንኙነት መኖሩንም አመልክተዋል።

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያና ሶማሌላንድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ ውድቅ እንዲሆን የሚያዝ ህግ መፈራማቸውን አስታውቀው በኤክስ ገጻቸው ማስፈራቸው ታይቷል።

Exit mobile version