ETHIO12.COM

ኤርትራ በገሃድ የኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤትነት ለማጨናገፍ ከሶማሊያ ጋር መቆሟን አረጋገጠች

የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ወደ ኤርትራ አቅንተው የሁለት ቀን የስራ ጉብኝት አድርገው ወደ ሞቃዲሾ ተመልሰዋል።

ፕሬዜዳንቱ ጉብኝታቸውን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። በማብራሪያቸውም ፤ ” ኤርትራን በተደጋጋሚ ጎብኝቻለሁ። ኤርትራ ለኛ እንደ ቤታችን ናት ” ብለዋል።

ወደ ኤርትራ የሄዱትበትን ምክንያት ቀንጭበው ሲያስረዱም 

ኤርትራ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገች ባለችበት በሶማሊያ ሽብርተኝነትን መዋጋት ዙሪያ ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ገለጻ ለማድረግ፤ ከሰሞኑ በቀጠናው እየተስተዋለ ስላለው ተለዋለዋጭ ሁኔታ ላይ ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ ገለጻ ለማድረግ፤ በአካባቢው ስለላለው ሁኔታ የሶማሊያን አቋም ለፕሬዜዳንት ኢሳያስ ለማስረዳት ነው ብለዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ ” ኤርትራ ሁልጊዜም ከሶማሊያ ጎን ናት፤ ለዚህም እናመሰግናለን ” ሲሉ ተደምጠዋል። ” ኤርትራ የሶማሊያን አንድነት፣ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ ስትደግፍ ቆይታለች ይህም የኤርትራ ዓለም አቀፍ አቋም ፤ አሁንም ይህንን አቋም ክቡር ፕሬዝዳንቱ ዛሬ ደግመውኛል፤ ለዚህም እናመሰግናለን ” ሲሉ ተናግረዋል።

የኤርትራ መንግሥት በበኩሉ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውንና ውስጥ ውስጡን ሲያራምድ የነበረውን አቋሙን ይፋ እንደሚያደርግ ማስታወቁ ተመልክቷል።

የኤርትራ መንግሥት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ባለፉት ሁለት ቀናት በሁለትዮሽ፣ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ እና ጥልቅ ውይይት አድርገዋል ሲል ያስታውቀው የኤርትራ መንግስት፣ ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ እንደሚሰሩ መስማማታቸውን እና በቅርቡ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ መግለጫ እንደሚያወጣ አስታውቋል። መግለጫው ሲብላላ የቆየውን ጉዳይ በግልጽ ይፋ ከማድረጉ ውጭ ብዙም አዲስ ጉዳይ እንደማይኖረው በርካቶች ተናግረዋል። ይልቁኑም የኢትዮጵያ መንግስት አፍኖት የቆየውን ሁሉ ይፋ ሊያደርግ እንደሚችል ተገምቷል። እናም ከኤርትራ ይልቅ የኢትዮጵያ መንግስት በምላሽ የሚሰጠው መግለጫ ይጠበቃል።

ኤርትራ፣ ሳዑዲ አረቢያና ግብጽ በይፋ ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻ የጀመሩ አገራት መሆናቸው ስምምነቱን ተከትሎ ይፋ መሆኑ አይነጋም።

የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ አስመራ ከኢሳያስ ጋር እየመከሩ ባለበት ሁኔታ፣ የግብፁ መሪ አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ግብፅን እንዲጎበኙ ግብዣ አድርገውላቸው መረጃዎች ወጥተዋል። የኢትዮጵያና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ከተፈረመ በኃላ ድብቅ የነበረው የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አቋም ይፋ ሆኗል።

ይህ በንዲህ እንዳለ በኤርትራ የሚደገፉ አማርኛ ተናጋሪ ሚዲያዎችና “አክቲቪስቶች” የኤርትራን መግለጫ እንዴት እንደሚያሰራጩና በመን መልኩ ከፍተኛ የሚዲያና የማህበራዊ አውዶች መጠቀሚያ ማድረግ እንደሚቻል ከወዲሁ ዝግጅት መደረጉ ተሰምቷል። በውስጥ ውይይት በከፍተኛ ደረጃ የኢትዮጵያን መንግስት የማጥላላት ዘመቻ ለመጀመርና ኢሳያስ አፉወርቂ የኢትዮጵያ አሳቢ አድርጎ ለማቅረብ መታቀዱ ታውቋል።

በትግራይ ሰላም መውረዱን ተከትሎ አቋማቸውን የቀየሩት ኢሳያስ አፉወርቂ ሰራዊታቸው በትግራይ ህዝብ፣ ንብረትና ክብር ላይ እጅግ ዘገናኝ ግፍ መፈጸሙ በወቅቱ ሲገለጽ መቆየቱ አይዘነጋም።




Add Your Heading Text Here

Exit mobile version