Site icon ETHIO12.COM

የአፍሪካ ልማት ባንክ ከአዲስ አበባ ያስወጣቸውን ሰራተኞቹን ዳግም እንደሚመልስ ይፋ አደረገ

የአፍሪካ ልማት ባንክ፤ ዳግም ሠራተኞቹን ወደ አዲስ አበባ እንደሚመለስ አስታወቀ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ “ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ያለን አጋርነት ለኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነት ጥረቶች ወሳኝ ነው” ብለዋል።

የአፍሪካ ለማት ባንክ ቀደም ሲል በሠራተኞቹ ላይ በተፈጸመ ድብደባና አግባብነት የጎደለው ተግባር ሳቢያ  የዲፕሎማሲያዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን ጠቅሶ ታኅሣሥ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ሠራተኞቹን ከአዲስ አበባ ማስወጣቱ ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንውሚ አዴሲና ጋር መወያየታቸውን ተከትሎ ነው ይህ ውሳኔ ይፋ የሆነው።

” ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ግንኙነታችንን በይበልጥ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረናል” ሲሉ የንግግሩን ፍሬ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው “ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ያለን አጋርነት ለኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነት ጥረቶች ወሳኝ ነው” ሲሉ በምግብ ምርት ራስን መቻልን ከ”ሏዓላዊነት” ጋር አያይዘው ገልጸዋል።

ባንኩ ዛሬ እንዳስታወቀው የቀድሞውን ውሳኔውን ያነሳው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባንኩን ቅር ባሰኘው ጉዳይ ላይ እርምት እንደሚወስዱ ማስተማመኛ እንደሚሰጡ ማረጋገጫ ከሰጡ በሁዋላ መሆኑን ጠቁሟል።

በዚሁ መነሻ የአፍሪካ ልማት ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ግንኙነት ወደ ቀድሞ መልኩ መመለሱን ዛሬ ባሰራጨው ኦፊሳላዊ መግለጫ አመልክቷል።

 ሁለት ሠራተኞቹ  በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጪ ታስረው አካላዊ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል በሚል ባንኩ ሰራተኞቹን ማስወጣቱና ማብራሪያ መጠየቁን፣ እንዲሁም በጥፋተኞች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጥያቄ አቅርቦ እንደበነበር በመግለጫው አውስቷል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አኪንውሚ አዴሲና አዲስ አበባ ተጉዘው እንደነበር በመግለጫው  አስታውሷልል።

የብንኩን ውሳኔ ተከትሎ በርካቶች ጉዳዩን ፖለቲካዊ ቅርጽ አሲዘው በከፍተኛ ደረጃ ዜናውን ከራሳቸው ፋልጎት አንጻር ሲያሰራጩት እንደነበር ይታወሳል።

በይቅርታ የተጠናቀቀውን ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ” ባንኩ ወጣ” ሲሉ የነበሩ ወገኖች ” ባንኩ ሰራተኞቹን መለሰ” ሲሉ በቀድሞው የዜና ክረት አልዘገቡም።

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የእርሻ ትራንስፎርሜሽን ከፍተኛ እገዛና ይፋዊ ምስክርነት በመስጠት የሚታወቅ ነው።

Exit mobile version